Get Mystery Box with random crypto!

#የካሌብ_ጽሑፎች ተሰውረሽ የሰወርሽን ሆይ: አንቺ ኢትዮጲያይቱ ሆይ: እስቲ ክንብንብሽን አውር | የካሌብ ጽሑፎች

#የካሌብ_ጽሑፎች

ተሰውረሽ የሰወርሽን ሆይ:
አንቺ ኢትዮጲያይቱ ሆይ: እስቲ ክንብንብሽን አውርጂ፤
እስቲ ዓይነ ርግብሽን ግለጪ::
ከልባችን ማድጋ የፈሰሰው ውኃሽ የሚነደውን ቀርቶ ሊነድ ያሰበን ሳይተው ያጠፋል እኮን::
ብትረቂባቸው ጊዜ: የሌለሽ የመሰላቸው እነርሱ ያሉ ያሉ መሰላቸውና መኖሪያ ነፈጉሽ፤ ማደሪያ ከለከሉሽ፤ መጠጊያ አሳጡሸ::
ግና ከሚታየው ሲያሳድዱሽ: ከሚዳሰሰው ሲያርቁሽ: ከመጽሐፉ፣ ከባሕሉ፣ ከአነዋወሩ ሲያባርሩሽ: ይባስ ከደማችን ተሸሸግሽና ላትለዪ ተዋሕድሽባቸው::
አስተሳሰብ ሆንሽና ባለመጥፋት ጸናሽባቸው:: የቀደመው አባት የተከተለሽ እናት ሆይ: እስቲ ከኛ ከተዋረዱት ሳለሽ ከፍታሽን ተናገሪ፤ እስቲ በተወነካከረ ድምፃችን ዝምታሽን ስበሪ:: ነገሩስ አንቺ መቼ ዝም አልሽ?.. ዝም ማለት አቅቶን ዝም ብለሽ የምታወሪን አልደመጥ አለን እንጂ::

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0