Get Mystery Box with random crypto!

የካሌብ ጽሑፎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ thehabesha0 — የካሌብ ጽሑፎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ thehabesha0 — የካሌብ ጽሑፎች
የሰርጥ አድራሻ: @thehabesha0
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይድረስ:-
ለኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያውያት!
በእግዚአብሔር ስም ሰላምታዬን አቀርብላችኋለው"
የኢትዮጵያ መካነ አእምሮ ወደሚገኝባት ወደ ኢትዮጵያዊነት የእውቀት መዲና ለመጓዝ ፈቃደኞች የሆናችሁ ሁሉ ኑ!
ወደዚያ የሚያደርሳችሁ በመንፈስ ቅዱስ የሚነዳ የውይይት ሠረገላ ይኧው ተዘጋጅቶ ቀዳማዊ ጉዞውን ሊጀምር ይጠብቃችኋልና ተሣተፉ!
---ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት---

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 21:15:57 ሰላም ለሁላችሁም ቤተሰቦች ከላይ በምስሉ እንደምትመለከቱት ዛሬ ትላንት በነገርኳችሁ መሰረት ስለ የጀርመኑ ናዚ አርማ እና ስዕለ ኪሩብ! ጥቂት ላውራችሁ..ተከተሉኝ..መልካም ንባብ...

የምስጢር ማህበረሰብ በመባል የሚጠሩት የስማዝያ ጭፍሮች በተለያየ ዘመን ወደሃገራችን በመግባት የተለያዩ ቅርሶችን መጽሀፍትን መንፈሳዊ አንድምታ ያላቸውን ጠልሰሞች ከሃገራችን መበዝበዛቸው አሁንም እየበዘበዙ እንዳሉ በተደጋጋሚ ለመግለጽ ሞክሬያለሁ፡፡ ታዲያ ለዚህ ስውር ደባ እንደ ማስረጃ ከማቅረባቸው ጠልሰማት አንዱ ስዕለ ኪሩብ የተሰኘውን ጠልሰም ነው፡፡ የምስጢር ማህበረሰቡ አንድ እጅ የሆነው የጀርመኑ የናዚን ቡድን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ አካላት ሰዋስቲካ ብለው የሰየሙትን ምልክት ለጦር ሃይላቸው አርማ ሲጠቀሙ በመመልከታችን የኛ እንዳልሆነ ለዘመናት ተቀብለን አምነናል እንዲሁም ተምረናል፡፡ እውነቱ ግን ይህ አይደለም የምስጢር ማህበረሰቡ መንፈሳዊ ጥበቦች እና ምስጢራቶችን ተቀራምቶ ዓለምን ለመግዛት ለዘረፋ ከተሰማራባቸው ሀገራት ቀደሚ ስፍራ የምትይዘው ኢትዮጵያ ስትሆን ከተወሰዱብን ጠልሰሞች መካከልም በነርሱ አጠራር ሰዋስቲካ የተሰኘው ጠልሰማችን ነው፡፡ ይህ ጠልሰም የስድስት ሺህ ዓመት ታሪክ ባላት በጥንቷ ኢትዮጵያና በጥንታዊ መጽሀፍቶቻችን ስዕለ ኪሩብ ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ኢዮር በተሰኘችው የእሳት ዓለም ውስጥ የሚገኙ የመላእክት ነገዶች ናቸው፡፡

፩. በመጀመሪያው ምስል እንደምትመለከቱት የውጭ አካላት በተለይም የጀርመኑ ናዚ ጦር እንደራሱ በማስመሰልና ስዋስቲካ ብሎ በመሰየም ተጠቅመውበታል።

፪. በሁለተኛውና ሶስተኛው እንደምትመለከቱት ግን ይህ ጠልሰም የእኛ የኢትዮጵያውያን ማለትም በላሊበላ ውቅር አብያተ ቤተክርስቲያን በግድግዳው ላይ በግልፅ ተቀምጦ እናገኘዋለን። ስሙም ስዕለ ኪሩብ ይባላል። ስለዚህ ጠልሰም ጠለቅ ያለ ማብራሪ በሌላ ክፍል የማቀርብላችሁ ይሆናል ለዛሬ በዙሁ አበቃሁ እኔ ዓጼ ካሌብ ነበርኩ ። ለማንኛውም አስተያየት እና ጥያቄ በ @kalebo19king ላይ አድርሱኝ ድህረገጹንም በቅንነት ለሌሎች ያጋሩ መልካም ምሽት።

ታድያ ይህ ጠልሰም የእኛ ነው ወይንስ የእነሱ? የሚለውን ለሁላችሁም አንባቢያን እተወዋለሁ

ፈጣሪ ቅድስት ሐገራችን በምህረቱ ይቅር ይበላት ከልጆቿም መከራና ስቃይ ይገላግላት!

ይህ #የካሌብ_ጽሑፎች የቴሌግራም ድህረገጽ ነው

ኢትዮጵያ ሁን 
አፍሪካ ሁን
ሰው ሁን

ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል

@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0

................................................
1.1K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:04:46
የኢትዮጵያን ኩራት ስዕለ ኪሩብ (ላሊበላ..አብያተክርስቲያን ለይ የሚገኘው ምስል/ምስለ ኪሩብ)

@TheHabesha0
..........................................
213 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:04:46
የጀርመኑ ጦር ናዚ አርማ

@TheHabesha0
........................................
218 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:29:23 #ትዝብት በ #ካሌብ_ጽሁፎች


.........ትውልድ እንታደግ


ሰላም ለሁላችሁም በያላችሁበት ይሁን!

የነገ ሀገርህ የዛሬውን ትውልድ ትመስላለች ....ኢትዮጽያዬ አወዳደቁዋ እንዳይሆን ሆንሳ ...የነገዋን ኢትዮጽያ አሻግሬ ስስል ምነው ልቤ ሰጋ... ትውልዱ ሱሰኝነት ፣ዘረኝነት እና ሴሰኝነት በሚባሉ ትብታቦች ተተብትቦ የክፋት ሸቀጥ ማራገፍያ ሆነሳ ??! ኧረ ሀገራችንን ከሞት ጉዞ ትውልዱን አንቅተን እንመልሳት ...ወደ እሱነቱ ጥግ ወደ ማንነቱ ከፈፍ እንጎትተው ......ተምሳሌት ወይም መምህር ከሚባሉትስ ምነው ትውልዱ ቁልቁል እንዲንደረደር እና ያለ እውቀትም የሞት ዛፍን እንዲመኝ፣ በድንቁርና በክፋት እንዲወድቅ ፣የክህደት የጥላቻ እና የሴራ ቃላትን አሰሙ፣አስተማሩ/ያለ እፍረትም ለቀቁብን ስንጠፋም ለ፩ ዓላማ ተሰልፈዋልና በደስታ አፌዙብን ?! .....ምንአለበት ትውልዱ ለሀገሩ ለባህሉ ተገዢ እንዲሆን ብንጥር?! ....በተራቆተ ገላ ላይክ ሽመታ ከምንጋልብ ...ምነው የጎጥ ግንብ ሰርተን ከምናባላ ፍቅርን ሀሁ ብንል....የነገር አተላ ድፍድፍ ከምንደፈድፍ ምናለ ትውልዱን ከራሱ ከእምነቱ ከባህሉ ለማስረቅ ደፋ ቀና ብንል ምናለ?.

የከበረው እና ድንቅ ፍጡር የሆነው የሰው ልጅ ያውም /የኢትኤል ልጅ/.....በጭስ ማግ ናላውን ከሚያዞር .....በጫት ደንዝዞ ከሚኖር በውሸትም ፍልስፍና ተለክፎ ኑሮውና ህይወቱ ከሚመነምን....እናም ይህ ሁሉ ሲሆን ቁጭ ብለን ከምናይ ለሐገራችን ነፃነትን ፥ ፍቅር ለመቸር ብንሯሯጥ ለችግረኛው እና እስረኛውስ በቂ እውቀት በመስጠትም ሆነ በምንችለው እየረዳን ከባርነት ነጻ የሚያወጣውን መንገድ ብንመራ....

እናም እኔ እላለሁ ሰው ሆነን ሰውን ሰው ብናደርገው በውስጣችን የገባውን ክፋት ገድለን?

ኧረ ምነው ሀገሬ ልባም ጠፋብሽ???!

መልካም ምሽት ይሁንላችሁ ይህንን ጦማር ስጽፍ ብዙ ፈጣሪ የሚያውቃቸው እና ከእኛ እጅግ ርቀው ራሳቸውን አግልለውም ሆነ ሰውረው ያሉ የሰው ልጅ ሰዎችም እንዳሉ ልብ ይሏል! በቀጣይ ስንገናኝ በጥያቄያችሁ መሰረት ስለ  የጀርመኑ ናዚ አርማ እና ስዕለ ኪሩብ ! ከኔፍሊሞች እና ፮፮፮ አባላት ጋር የሚያገናኘውን ነገርም አጠር ባለ መልኩ የማደርሳችሁ ይሆናል እኔ #ዓጼ_ካሌብ @Kalebo19King ነኝ ማንኛውም ሐሳብ፣ጥያቄም ይሁን አስተያየት በውስጥ መስመር ማቅረብ ትችላላችሁ አብነሮነታችሁ አይለየን።


ልብ ካለህ ቀድመህ ራስህን በኋላም ትውልዱን አድን!



ኢትዮጵያሁን 
አፍሪካሁን
ሰው ሁን

#ይሄ_የካሌብ_ጽሁፎች ነው

ይህንን ድህረ-ገጽ ለመቀላቀል

@TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0 @TheHabesha0
2.7K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:51:21 #ሆያ_ሆዬ #በካሌብ_ጽሑፎች
#Join & #Share Our channel

@TheHabesha0
@TheHabesha0
600 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:51:21 #ቡሄ_በሉ

@TheHabesha0
@TheHabesha0
@TheHabesha0
544 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:51:21
እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

#የካሌብ_ጽሑፎች
#Join & #Share Our channel

@TheHabesha0 @TheHabesha0

525 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 21:08:35
#የካሌብ_ጽሑፎች

ተሰውረሽ የሰወርሽን ሆይ:
አንቺ ኢትዮጲያይቱ ሆይ: እስቲ ክንብንብሽን አውርጂ፤
እስቲ ዓይነ ርግብሽን ግለጪ::
ከልባችን ማድጋ የፈሰሰው ውኃሽ የሚነደውን ቀርቶ ሊነድ ያሰበን ሳይተው ያጠፋል እኮን::
ብትረቂባቸው ጊዜ: የሌለሽ የመሰላቸው እነርሱ ያሉ ያሉ መሰላቸውና መኖሪያ ነፈጉሽ፤ ማደሪያ ከለከሉሽ፤ መጠጊያ አሳጡሸ::
ግና ከሚታየው ሲያሳድዱሽ: ከሚዳሰሰው ሲያርቁሽ: ከመጽሐፉ፣ ከባሕሉ፣ ከአነዋወሩ ሲያባርሩሽ: ይባስ ከደማችን ተሸሸግሽና ላትለዪ ተዋሕድሽባቸው::
አስተሳሰብ ሆንሽና ባለመጥፋት ጸናሽባቸው:: የቀደመው አባት የተከተለሽ እናት ሆይ: እስቲ ከኛ ከተዋረዱት ሳለሽ ከፍታሽን ተናገሪ፤ እስቲ በተወነካከረ ድምፃችን ዝምታሽን ስበሪ:: ነገሩስ አንቺ መቼ ዝም አልሽ?.. ዝም ማለት አቅቶን ዝም ብለሽ የምታወሪን አልደመጥ አለን እንጂ::

#ይህ_የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ነው

@TheHabesha0 @TheHabesha0
@TheHabesha0 @TheHabesha0
649 views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 21:22:22 ሰላም ለሁላችሁም እንደምን ቆያችሁ?እስኪ ለዛሬ ስለ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን አንዳንድ እዉነታዎችን ላካፍላችሁ...መቼም ነገሩ ባህርን በማንኪያ መሆኑ የታወቀ ነው.. መልካም ንባብ ይሁንላችሁ..

( ፩ )አንደኛ

➨ ሞትን ሳይቀምስ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደውና አዕምሮውን መቶ በመቶ(100%) የተጠቀመበት ብቸኛው የምድራችን ሰው #ሔኖክ /ኢትዮጵያዊ/ ነው። እስከዛሬ ድረስ አዕምሮውን ሙሉ በሙሉ የተጠቀመ ምድራዊ ሰው የለም። የሰው ልጅ የአእምሮው ልዕልና የሚለካው በምድራዊ እውቀት ሳይሆን በሰማያዊ ጥበብ ነው። ሰው የአዕምሮው ልዕልና (IQ) ሲያድግ ወደ ቅድስና ደረጃ ይሸጋገራል እንጅ ምዕራባዊያን እንደሚሉት በምድራዊ ጥበብና እውቀት አይመላም። ይሄን ደግሞ ያደረገ ብቸኛው ሰው አባታችን ቅዱስ ሔኖክ የተስፋይቷ ምድር ልጅ ብቻ ነው።

፪ ሁለተኛ

➨ሲዖልም ገነትም የሚገኙት በመላኩ 15 ክንድ ከምድር ከፍ ብለው ኢትዮጵያ (አፋር ኤርታሌ እና ጎጃም ጣና አካባቢ በቅደም ተከተል) ነው ይህን ስንል አለማትን ማለትም ሲዖል የሚባል ራሱን የቻለ አለም ሌላ ሰማይ ላይ እንዳለ ልብ ልትሉ ይገባል ምን አልባት በሚቀጥለው ስለ (፯) ሰባቱ ሰማያት እና (፻) መቶ አለማት የማቀርብላችሁ ከሆነ በይበልጥ ግልጽ የሚሆን ይመስለኛል ። እናም በድሮው ወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው አፋር ውስጥ የሚገኘው #ኤርታሌ የሚባለው ቦታ ግን ነገሩ የራሱ የሆነ ሰማያዊ ምስጢር አለው። እዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው እሳተ ገሞራ ወይም የእሳት ባህር #አዛዝኤል የታሰረበት ቦታ መሆኑን አንዳንድ መዛግብት ላይ ለማንበብ ችያለሁ። አዎ ይህ ቦታ የምድራዊው ወይም የኛ ሰማይ ሲኦል መገኛ እንደሆነና ጎጃም የሚባለው ሀገር ላይ በተለይም ደግሞ ጣና ዙሪያ የገነት መገኛ እንደሆኑ አንዳንድ የብራና መዛግብት ይጠቁማሉ።

( ፫ ) ሶስተኛ

➨ በዓለም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠለት የዘመን ስሌት ያለው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ (ኢትዮጵያ) ውስጥ ነው። ይህንንም ዓለም ሲመራበትና ምዕራባውያኑ እየተጠቀሙበት ያለው ወይም ደግሞ የማያውያን ካላንደር ትክክል እንዳልሆነ ይህንንም በ መጋቤ ሃዲስ ሮዳስ ታደሰ የቀመር ስሌትና እውቀት በመጠቀም በኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር ሰኔ 14/2012/ የታየው የፀሀይ ግርዶሽ ትንተና የዚህን ቀመር እውነታን ፍንትው አድርጎ የገለፀና ታእማኒነቱን ያረጋገጠ ሀቅ ነው፡፡

( ፬ )አራተኛ

➨ በነብያት እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተባለች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች። አዎ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መመኪያዋም አለኝታዋም እርሱ ነውና። ይች ሀገር ከፈጣሪዋ ጋር ልዩ ትስስር ያላት የዓለማችን ብቸኛ ሀገር ነች። ፈጣሪ በስጋ የተመላለሰባት ሀገር እስራኤል እንኳን የኢትዮጵያን ያህል ክብር በፈጣሪ ዘንድ የላትም ይህ ጽንፈኝነት ሳይሆን ሐቅ ነው እውነትን የሚወድ እና የሚፈልግ ቢኖር አስቀድሞ ሁሉን ይመርምር ። ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ነገር አለ። እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል እስራኤላዊያንን ሲገስጽ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊያን ልጆች አይደላችሁም ነበር ያለ። ልብ በሉ! እንደ ኢትዮጵያዊያን!

( ፭ ) አምስተኛ

➨ ታቦተ ጽዮን የሙሴ ጽላት የምትገኝባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች። በአምላክ ትዕዛዝና ቀመር የተሰራችው ይህቺ ጽላት በጠቢቡ ሰለሞን የንግሥና ጊዜ የደቡብ ንግስት (ንግስተ አዜብ) ወይም የሳባ ንግስት (ንግስተ ሳባ) ተብላ በምትጠራዋ ንግስት.. በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ነበር ወደ ሀገራችን የገባችው። ምዕራባዊያን ይህቺን መመኪያችንን ጽላት ዘሙሴ ለመውሰድ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ነገር ግን አልተሳካላቸውም። አይሳካላቸውምም። ምክንያቱም እነርሱን ትታ በእኛ ምድር በሀገራችን ትኖር ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቃድ መጥታለችና ሊወስዷት ቢኳትኑም አያገኟትም።

ይህ #የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ ነው

ስለመረጡን አክሮታችን ላቅ ያለ ነው! ይህንን ድህረገጻችንን ያልተቀላቀላችሁ ከታች አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለም ልብ ቅርጽ መሀል ያለውን ሰማያዊ ሊንክን በመንካት #Join ያድርጉ ድህረገጹ አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል ሆኖ ካገኙት ሌሎችም ይቀላቀሉን ዘንድ በቅንነት #Share #Forward በማድረግ አብረውን ይቀጥሉ


ለመ ላ ል

@TheHabesha0
@TheHabesha0
@TheHabesha0

እኔ #ዓጼ_ካሌብ ነበርኩ መልካም ምሽት ይሁንላችሁ እያልኩ ለዛሬ ያዘጋጀሁላችሁን ጦማርን በዚሁ አበቃለሁ!

.....................................................
4.3K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 21:58:54 ኔፍሊም እነማን ናቸው የሚለውን ምስል ወይም ማስታወቂያ አይታችሁ ወደድህረገጻችን ለገባችሁ ቤተሰቦች እና ሁላችሁም #የካሌብ_ጽሑፎች_የቴሌግራም_ድህረገጽ_ቤተሰቦች በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ እኛ የውሸት ማስታወቂያ አንሰራም ይህ አይነት አካሄድም አላማችን አይደለም..ይሄንን ያልኩበት ምክንያት አዳዲስ ቻናላችንን የምትቀላቀሉ ሰዎች ስለዚህ ድህረገጽ ብዙም ስለማታውቁ ነው። ነባር አባላት ግን ያው እንደተለመደው ጠይቁኝ አስተያየትም ስጡኝ በውስጥ መስመሬ። የወደዳችሁትን ጽሁፎችንም ለሌሎች ሰዎች አካፍሉ ቻናሉንም ጋብዙ

#ስለ ኔፍሊም (ራዕዮት) ፣ጃይንት ከዚህ በፊት ፅሁፍ ለቅቄ ነበር ያንን ለማንበብ ይሄንን #ኔፍሊም #ኔፍሊም ይጫኑና ከታች በስተግራ በኩል በሚመጣላችሁ የጠቋሚ ምልክት ወይም ዝርዝር ወደላይ ከፍ በማለት ሁሉንም እስከዛሬ ያስቀመጥኳቸውን መረጃዎች ማንበብ ይችላሉ። ተጨማሪ መፅሃፍ ቅዱስን እና ሌላ ዋቢ መፅሃፍቶች ጋር ያገኘኋቸውን አጋራችኋለው ከዚህ በፊት ያስቀመጥኳቸውም አሉ እነሱን ይመልከቱ። ይሄ የኔፍሊሞች ጉዳይ...

#የኖህ ዘመን ጥፋትን ያስመጣ

#አሁንም አለምን እያመሰ ያለ ችገር በመሆኑ

#እና ለብዙ ዘመናት ሳናውቅ ለምናወራላቸው ቅሪተ አካሎችንም ምስጢር የያዘ ነው..እንዴት መሰላችሁ...

ቆይ ለምንስ ውሸት አስፈለገ??? በእውነት እነሱም ሳያውቁ ቀርተው ነው ወይስ ከኛ እንዲደበቅ የተፈለገ ምስጢር ኖሮ የእነ #ሉሲ፣ድንቅነሽ....እና ስለመሳሰሉት ቅሪተ አካል ያንን ያክል በሚሊዮን የሚቆጠር ዘመን በፊት ይኖሩ ነበር እያሉ የሚነግሩን ደሞም አስተውሉ!!!! ከሃይማኖታዊ አስተምሮም ውጪ ነው እነሱ የሚሉት ዘመን ። ሌላው የማይዋጥ ነገር ደሞ የሰው ልጅ ናቸው የሚሉት አስተምሮአቸው ነው የዳርዊንን ቅዠት እውን ለማድረግ አስመሰለባቸው።

ማሳሰቢያ ከዚህ ቻናል እያወጣችሁ ሌላ የተለያዩ የራሳችሁ ቻናል ላይም የምትለቁ ሰዎች እንዳላችሁ አውቃለሁ... ምንጭ ጥቀሱ ምንጭን መጥቀስ የስልጣኔና የመልካም ስብዕና ምሳሌ እንጂ አላዋቂነት እና መበለጥ አይደለም ኑ በጋራ እንማማር ድብቅ ነገር የለም አይኑን ለገለጠ ሁሉም ቅልጽ ነው ይሆናልም!

➨እናም ውድ የድህረገጹ ቤተሰቦቻችን በመጨረሻ የምላችሁ ነገር ቢኖር ከማናውቀው እውነት በላይ የምናውቀው ሀሰት እና የጥፋት ህይወት በብዛት የጎዳን ያጠፋን ነን እና ራሳችንን እንመርምር ከሁሉም በፊት የሚቀድመውን ካስቀደምንና መልካም ስብዕናን ከተላበስን ያኔ ከላይ እንዳልኩት ሁሉም ግልጽ ይሆናል...

@Kalebo19king ነኝ መጠየቅ ያለባችሁን ወይሚ የሚገባችሁን ነገር ሁሉ በግልጽ መጠየቅ ትችላላችሁ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በቻልኩት እና ባወቅኩት መንገድ የምመልስላችሁ ይሆናል...ለአሁኑ አብቅቻለሁ መልካም ምሽት ይሁንላችሁ።


የቴሌግራም ድህረገጻችንን ላልተ ላ ላችሁ ይህንን በመጫን ቤተሰብ መሆን ትችላላችሁ ለሌሎችም በቅንነት ያጋሩ!

@TheHabesha0
@TheHabesha0
5.4K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ