Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ወቅት አንድ የማውቀው ሰው የተከራየው የንግድ ቤት አከራዮች ኑሮ እየተወደደ ስለሆነ ትንሽ | Tesfaab Teshome

በአንድ ወቅት አንድ የማውቀው ሰው የተከራየው የንግድ ቤት አከራዮች ኑሮ እየተወደደ ስለሆነ ትንሽ ብር እንዲጨምርላቸው ጠየቁት። እሱ ግን ውላችን አምስት አመት ስለሆነ አልጨምርም አለ።ሰዎቹ አምስት አመት ሲሞላ ጠብቀው ውጣ አሉት።ቤቱ ስራ ስለነበረው እጥፍ ልጨምር ቢልም ቤታችንን እንድትለቅ ነው የምንፈልገው አሉት።ቢለምን ቢያስለምን እምቢ አሉት። ቀጥሎ አይኑ እያየ እሱ ከሰጣቸው ዋጋ ባነሰ ብር ለሌላ ሰው አከራዩት።

እዚህ የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም የሚለውን የግለሰብን የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጥስ አዋጅ ደግፈህ ጮቤ የረገጥክ ከትንሽ ግዜ በኃላ ባለቤቱ ያገኝሀል። አንድ ሰው ጥሮ ግሮ የሰራውን ቤት ለማን ማከራየት እንዳለበት፣ በስንት ማከራየት እንዳለበት የሚወስነው እሱ እንጂ አዳነች አይደለችም። አዛኝ ከሆነች በራሷ ገንዘብ ቤት ሰርታ ማከራየት ነው።

ሲጀመር የቤት ኪራይ እየጨመረ ያለው አከራዩ አይደለም።እንደማንኛውም እቃ የቤት ኪራይ ዋጋ እና የወለድ ምጣኔም መንግስት አትሞ ከረጨው ብር ጋር እራሳቸውን adjust እያደረጉ ስለሆነ ነው። መንግስት የመብራት ታሪፍ በእጥፍ ልጨምር ነው ከሚለው ዜና ቀጥሎ ግለሰቦች የቤት ኪራይ መጨመር አይችሉም የሚባልባት ሀገር በጣም ታስቃለች።የቤት ኪራይን ጨምሮ የሁሉንም እቃ ዋጋ ጣርያ አስነክቶ የይስሙላ "የቤት ኪራይ አትጨምሩ" የሚል አዋጅ ያወጣውን መንግስት የምታመሰግኑ ሰዎች ደግሞ የበለጠ ታስቃላችሁ።

VIA Mekoya kebede

@Tfanos