Get Mystery Box with random crypto!

እናየው ይሆን ይህን ቀን አልፈን?! (በእውቀቱ ስዩም) በጦር መርታት ነው፤ የሁሉም ተስፋው | Tesfaab Teshome

እናየው ይሆን ይህን ቀን አልፈን?!

(በእውቀቱ ስዩም)

በጦር መርታት ነው፤ የሁሉም ተስፋው
የሰላም ዋጋ መቸ ታሰበ?
አብሮ ለመኖር መላው የጠፋው
አብሮ ለመሞት ተሰባሰበ::

እንዳውሬ መኖር ፤እንደ ሰው ለብሶ
እብዱን ስንፈራው ፤ ጭምቱ ብሶ
“ውረድ እንውረድ” የሁሉም ዘፈን
እናየው ይሆን ፤ ይሕን ቀን አልፈን ?


የሞት ፈረስ ነው፥ አንደኛው ላንዱ
የሁሉም ክንዱ-
-ለማነቅ ተግቶ ፤ ለማቀፍ ዛለ
“ አንተኛው ታገስ፤ አንተም ተመለስ “
የሚል የታለ?
እንደ ጥጥ ሸክም ፤ ሽበት ቀለለ
መስቀል ጨረቃው አልተከበረ
ማርጀት ነው እንጂ መሸምገል ቀረ : :


@Tfanos