Get Mystery Box with random crypto!

⚀ ክፍል ሶስት ⚀ .....'እንዴ ምን እየሰራህ ነው ልጄ!? ደግሞ እሷ ማናት?'አለችኝ | የኔው ታሪክ 8315

⚀ ክፍል ሶስት ⚀




....."እንዴ ምን እየሰራህ ነው ልጄ!? ደግሞ እሷ ማናት?"አለችኝ ፊቷን ቅጭም አድርጋ የታዛውን ደረጃ ወርዳ ወደ እኛ እየተጠጋች።
እናቴ ደርብ ያለች የሴት ወይዘሮ ነች። እድሜዋ ወደ ሀምሳዎቹ እየሮጠ ነው።አባቴ ሲያገኛት ጠየም ያለች ወይዘሪት ስለነበረች አባቴ"ከአሳ የተቀዳ ውበት እያለ እንደሚያሞካሻት ሁሌም ይነግረን ነበር።
ግን አባቴ ይበልጥ ቀልቡን የሚስበው የጉንጮቿ ስርጉድ(ዲምፕሏ ) እና የጥርሷ ጉራማይሌ ነበር።
"እእ..ማ..ለት ውኃ .." ተንተባተብኩኝ እናቴ ልጅቷን ማናት ላለቻት ጥያቄ!
"ፍሌም እባላለሁ ሱቅ ተልኬ ጫማዬ አንሸራቶኝ ወድቄ ውኃ ስጠኝ ብዬው ነው ይቅርታ" አለች ልጅቷ ቅልጥፍናን በተላበሰ ትሁት አንደበት!!
ቅልጥፍናዋን እና ድፍረቷን ወደድኩት አንዳች ነገር እንደተናገረች ገምቻለሁ! ማለት ምንም የሰማው አልመሰለኝም። ፍሌም እባላለሁ ያለችውን ብቻ ነው በጥራት የሰማውት። ስሟ ውስጤ ቀረ እንደ ገደል ማሚቶ በጭንቅላቴ ውስጥ አስተጋባ! እናቴ ስትመጣ ደንግጬ እጇን ከለቀቅኩኝ ወዲህ ሙቀቷ ዘላለማዊ ይሆነኝ ዘንድ በእጄ ውስጥ የማሰርፀው ይመስል እጄን በእጄ አፋትጋለሁ።
....ዛሬ ግን ምን ነካኝ??
ለዚህች ልጅ ይህን ያህል መሆን ምን አስፈለገ ?
በዛ ላይ በዛሬ ያውም አሁን በአሁን!
ሆሆሆሆሆ ወይ ነዶ!
"ቲዲያ ምን ችግር አለው የኔ ልጅ ! የማነሽ ቆንጆ ደግሞ ነይ ሳሚኝ እስኪ " ብላ እናቴ ተጠጋቻት። ፍሌም ወደ ኃላ ሸሸት እያለች "ልብሴ ጭቃ ብቻ ነው እንዳላበላሽዎት "አለች። እናቴ ተጠግታት ግንባሯን ሳመቻት እና ወደ እኔ ዘወር ብላ"ግሩሜ እስኪ ከሚሚዬ ክፍል የሚሚዬን ቢጃማ አምጣላት! "አለችኝ እሩጬ ትርሃስ ክፍል ስገባ ከኮመዲኖ ላይ ተጣጥፎ የተቀመጠ ቢጃማ አግኝቼ ተመለስኩ።
እናቴ እና ፍሌም ቆመው ያወጋሉ። እናቴ እኔን ስታየኝ
" ጎሽ ግሩሜ ሻወር ቤቱን አሳያትና ሻወር ትውሰድ!"አለች
"አይ እንዲሁ እቤት ብሄድ ይሻላል ለሀገሩም አዲስ ስለሆንኩ አጎቴ ይሰጋል"አለች ፍሌም አንደበቷ ይጣፍጣል።የድምጿ ቅላፄ እንደ ወፍ ዜማ ለጆሮ ይስማማል!!
ከእናቴ ጋር አውግተው ሌላ ጊዜ መጥታ እንደምትጫወት ተነጋግረው ሸኛት ተብዬ ይዣት ከግቢው ወጣሁ።
የጅማ መድሃኒያለም ሰፈር በነጭ ጋቢ ተደርቶ የሚቆዝም ሽማግሌ ይመስል የጉም ጢስ ተከናንቦ ፀሀይ መውጣት፤ወገግ ማለትን ዳባ ልበስ ያለ ይመስላል።......Selam


ክፍል አራት ይቀጥላል........



▃▅▆█ 웃 ፍሌም 웃 █▆▅▃
ቶሎቶሎ እንዲለቀቅ ሼር አድርጉ !
https://t.me/teztash
https://t.me/teztash

@rediy21