Get Mystery Box with random crypto!

⚀ ክፍል ሁለት ⚀ .....የታዘዝኩትን ከሰል አስገብቼ ከቤት ወጥቼ ልውል ወስኜ ከአልጋዬ | የኔው ታሪክ 8315

⚀ ክፍል ሁለት ⚀



.....የታዘዝኩትን ከሰል አስገብቼ ከቤት ወጥቼ ልውል ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩና እንደነገሩ ለባብሼ ከክፍሌ ወጣሁ። በጣም እንደነጋ ያወቅኩት በሳሎኑ በኩል ወደ ውጪ እየወጣሁ የግድግዳ ሰዓታችንን ተመልክቼው ነበር። ቀኑ ድፍንፍን ያለ ነው። ማታ ዘንቦ ማደሩን የመሬቱ እርጥበት ያሳብቃል። የግቢውን በር ከፍቼ ስወጣ ጭራሽ ሰፈሩ በጉም ተከቧል።መጣ የተባለውን ከሰል ከዘበኛው ጋር አስገብተን ስንጨርስ የከሰሉን ማዳበሪያ የሸፈኑትን ቅጠሎች ከግቢ ውጪ ለመጣል ወጥቼ ጥዬ ወደ ቤት እየገባው የግቢያችን በር ላይ ስደርስ "ወንድም!" የሚል የሴት ድምፅ ሰማው።
ዞር ስል የሙስሊሞችን ሂጃብ የጠመጠመች ቀይ ባለሰልካካ አፍንጫ ፤ ውብ ፀዓዳ መሳይ አይኖችን የታደለች ፤ ቀይ ባለ ትንሽ ክብ ፊት ፤ ባለ ድንቡሽቡሽ ጉንጭ ሴት ቆማለች።
ድንግጥ አልኩኝ! ልቤ ትርክክ ፣ ስንጥቅ አለ። ድንገተኛ መባርቅ የመታኝ ያህል ክው አልኩኝ።
የማሪያምን ምስል የመሰለች ፤ የመላዕክታንን ውበት የታደለች ቆንጆ ልጅ ናት።
ልቤ የደም ዝውውሯን አፈጠነችው ትርታዬ ትር ትር ትል ጀመር።ቃል ሳላወጣ በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ አየዋት። እሷም ፍዝዝ ብላ ታየኝ ጀመር። ደፍሮ ቃል የሚያወጣ ጠፋ።
"ይቅርታ ሱቅ ተልኬ ጭቃ ነካኝ ውኃ..." አለች
እጇ በጭቃ ተበላሽቷል።ዝቅ ስል የለበሰችው ቢጃማም በጭቃ ደክርቷል። ለማየት የሚያሳሱ ውብ የአድማስ ዋልታ፣ የከዋክብት ፍንጣቂ የመሳሰሉ አይኖቿን አንከራተተችብኝ።
ውኃ ላመጣላት ተጣድፌ ወደ ቤት እየገባው ተገረምኩኝ 'ምን አይነት መሬት ቢሆን ነው እቺን ልዕልት የመሰለች ልጅ የጣላት? አይ የምድር ክፋት!' አልኩኝ በልቤ። ውኃውን በጆግ ቀድቼ ስመለስ ልጅቷ ግቢ ገብታ ነበር።
ውኃውን እያፈሰስኩላት እጇን እየታጠበች ልክ እጇ ጥርት ማለት ሲጀምር የቀኝ እጇ መሀከለኛው መዳፍ ላይ ትኩስ ትኩስ ቁስል አየሁኝ።
"እንዴ በእግዚአብሔር እየደማ እኮ ነው!" ብዬ ጆጉን ጣልኩና እጇን ለቀም አድርጌ ያዝኩት እጇን ስይዘው መላው ሰውነቴ በኤሌክትሪክ ሞገድ የተቀጣጠለ ይመስል አንዳች ሀይል መላው ሰውነቴን ነዘረኝ። እሷም ድንግጥ አለች!
ከአይኔ እየሸሸች "አ..ይ ....ትንሽ ነው ማለቴ..እእእ ዝም ብሎ ነው....ማለቴ አለ አይደል .. እእ" አለችና ቀና ብላ ውብ አይኗን አንከራተተችብኝ።
የሲኦል ፍም የመሰለው ፀዓዳ ከንፈሯ ይንቀጠቀጣል። ከገነት ቅርንጫፎች የተመዘዙ ጭራሮ የመሳሰሉት የውብ አይኗ ሽፋሎች በፍጥነት ይርገበገባሉ።በዚህ ሁነት ውስጥ እንዳለን "ግሩሜ"የሚል ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል እናቴ ናት። "እንዴ ምን እየሰራህ ነው ልጄ!? ደግሞ እሷ ማናት?" አለችኝ ፊቷን ኮስተር ቅጭም አድርጋ የታዛውን ደረጃ ወርዳ ወደ እኛ እየተጠጋች።.........


ክፍል ሶስት ይቀጥላል......



▃▅▆█ 웃 ፍሌም 웃 █▆▅▃

ቶሎቶሎ እንዲለቀቅ ሼር አድርጉ !
https://t.me/teztash

https://t.me/teztash