2020-06-16 09:18:51
ከረመዳኑ በኋላ ምን؟
ክፍል 3
ከረመዳን በኋላ ዋናው ቁም ነገር ፅናት ነው።
ሀ/ የፅናት ምንነት ትርጓሜ
ፅናት ማለት ባሉበት መልካም ነገር ላይ እስከ ዕለተ ሞት ድረስ በጎውን እየሠሩ ክፉውን እየራቁ ያለማቋረጥ መዘውተር ማለት ነው።
ለ/የፅናት አስፈላጊነት
1/የተፈጠርነው እላህን አዘውትረን እንድንገዛው ነው።
2/የአላሁ تعالى እና የመልዕ ክተኛው ﷺ ትዕዛዝ ነው።
አላህ تعالئ እንደተናገረው: "እርሱን ብቻ ተገዛው ለርሱም በመገዛትህ በፅናት ታገስ። "
ዓኢሻ رضي الله عنها እንደተናገሩት
"የአላህ መልዕክተኛ ሥራን ሲሰሩ ያፀኑት(ይዘወትሩበት) ነበር። "
ዘግበው ቡኻሪና ሙስሊም
መ/የሥራዎች ፍርያማነት/ ተቀባይነቱ ከጅምሩ ማማሩ ሳይሆን እስከመጨረሻው በመፅናት ድምዳሜው ላይ በማድረሱ ነው።
አላህ سبحانه وتعالى በክቡር ቁርኣን እንዲህ ይላል፦
وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
"እርግጠኛው (ሞት) እስኪመጣህ ጌታህን ተገዛ!"
አል ሒጅር: 99
ሠ/ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሥራን ተቀባይነት መሥፈርት ያደረጉት በመጨረሻዎቹ በድምዳሚያቸው ላይ ስለመሆኑ እንዲህ ብለዋል:-
"የሥራዎች ተቀባይነትና ትክክለኝነት በመጨረሻቸው ብቻ ነው። "
ረ/ ፅናት የመልካም ተግባር (የረመዳናችን)ተቀባይነት መስፈርቱ ነው
"የአንድ መልካም ሥራ ምንዳው (ጀዛእ) (የተቀባይነት ምልክቱ) ከዚያ (ከመልካሙ ሥራ በኋላ) ቀጣይነት ያለው ጥሩ ተግባር ማስከተሉ ነው።
"የመጥፎ ሥራ ቅጣቱ(ጀዛው) ክፉ አድራጎትን (መጥፎን ተግባር) ማስከተሉ ነው። "
ሐሰነል በስሪ رحمه الله
ልብ ያለው ልብ ይበል
ፅናት የሙእሚን ባህሪይ ሲሆን
ወረተኝነት የሙናፊቅ ባህሪ ነው።
ይህች ዓለም
የውጣ ውረድ
የመነሳትና የመውደቅ
የትግል ሜዳ ናት
መልካምን ወደራሳችን በማምጣት ማንነታችንን (ስብእናችንን) በኢማን ማጠንከሩ ባንዳፍታ የምናመጣው ሳይሆን ቀስ በቀስ በሂደት የሚመጣ ነው።
አንዴ ተነስተን በዚያው መውደቅ ሳይሆን ፦
አየተነሱ እየወደቁ
ተስፋ ሳይቆርጡ
በፅናት መቀጠል ነው።
ከረመዳን በኋላ ምን?
ክፍል 3
ከረመዳን በኋላ ዋናው ቁም ነገር ፅናት ነው።
1. የፅናት ምንነት ትርጓሜ
ፅናት ማለት ባሉበት መልካም ነገር ላይ እስከ ዕለተ ሞት ድረስ በጎውን እየሠሩ ክፉውን እየራቁ ያለማቋረጥ መዘውተር ማለት ነው።
ለ/የፅናት አስፈላጊነት
1/የተፈጠርነው እላህን አዘውትረን እንድንገዛው ነው።
2/የአላሁ تعالى እና የመልዕ ክተኛው ﷺ ትዕዛዝ ነው።
አላህ تعالئ እንደተናገረው: "እርሱን ብቻ ተገዛው ለርሱም በመገዛትህ በፅናት ታገስ። "
ዓኢሻ رضي الله عنها እንደተናገሩት
"የአላህ መልዕክተኛ ሥራን ሲሰሩ ያፀኑት(ይዘወትሩበት) ነበር። "
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
መ/የሥራዎች ፍርያማነት/ ተቀባይነቱ ከጅምሩ ማማሩ ሳይሆን እስከመጨረሻው በመፅናት ድምዳሜው ላይ በማድረሱ ነው።
አላህ سبحانه وتعالى በክቡር ቁርኣን እንዲህ ይላል፦
وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
"እርግጠኛው (ሞት) እስኪመጣህ ጌታህን ተገዛ!"
አል ሒጅር: 99
ሠ/ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሥራን ተቀባይነት መሥፈርት ያደረጉት በመጨረሻዎቹ በድምዳሚያቸው ላይ ስለመሆኑ እንዲህ ብለዋል:-
"የሥራዎች ተቀባይነትና ትክክለኝነት በመጨረሻቸው ብቻ ነው። "
ረ/ ፅናት የመልካም ተግባር (የረመዳናችን)ተቀባይነት መስፈርቱ ነው
"የአንድ መልካም ሥራ ምንዳው (ጀዛእ) (የተቀባይነት ምልክቱ) ከዚያ (ከመልካሙ ሥራ በኋላ) ቀጣይነት ያለው ጥሩ ተግባር ማስከተሉ ነው።
"የመጥፎ ሥራ ቅጣቱ(ጀዛው) ክፉ አድራጎትን (መጥፎን ተግባር) ማስከተሉ ነው። "
ሐሰነል በስሪ رحمه الله
ልብ ያለው ልብ ይበል
ፅናት የሙእሚን ባህሪይ ሲሆን
ወረተኝነት የሙናፊቅ ባህሪ ነው።
ይህች ዓለም
የውጣ ውረድ
የመነሳትና የመውደቅ
የትግል ሜዳ ናት
መልካምን ወደራሳችን በማምጣት ማንነታችንን (ስብእናችንን) በኢማን ማጠንከሩ ባንዳፍታ የምናመጣው ሳይሆን ቀስ በቀስ በሂደት የሚመጣ ነው።
አንዴ ተነስተን በዚያው መውደቅ ሳይሆን ፦
አየተነሱ እየወደቁ
ተስፋ ሳይቆርጡ
በፅናት መቀጠል ነው፡፡
وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ
እነዚያም በኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በርግጥ እንመራቸዋለን፡፡
በርግጥም አላህ ከመልካም ሰሪዎች ጋር ነው፡፡
አላህ ፅናትን ይስጠን
@tezkiraChannel
223 views06:18