2020-05-28 07:20:55
****,,,**,,,****
ከረመዳን ቡኋላ ምን,,,,,,,,?
1/ደስተኛ መሆን
ረመዳንን ለማጠናቀቅ ስለተወፈቅን ይህን ታላቅ ፀጋ በማግኘታችንደስተኛ ልንሆን ይገባል።
አላህ سبحان وتعال ክቡር በሆነው ቃሉ እንዲህ አለ : -
"በአላህ ችሮታ(ትሩፋት)ና በእዝ ነቱ ይደሰቱ። በዚህም መክንያት ይደሰቱ ። ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው በላቸው"
አር ረዕድ:58
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
" ለፆመኛ ሁለት ደስታ አለው
አንደኛው ደስታ በሚያፈጥርበት (ፆሙን በሚያጠናቅቅበት) ጊዜ
ሌላኛው ደስታ ከአምላኩ ጋር በሚገናኝበት ጊዜ። "
1/በሚያፈጥርበት ጊዜ ያለው ደስታ
ሀ/ የረመዳንን ፆም የዕለቱን ቀኑን ሙሉ ዒባዳ እና ባጠቃላይ የወሩን ሙሉውን ሳይበላሽበት ወይም ችግር ሳይገጥመው ባግባቡ ሳይጎልበት በማጠናቀቅ ለማፍጠር በመብቃቱ
ለ/(እና) ከተከለከለው ምግብ መጠጥና ,,, ተፈቅዶለት ስለ በላና ስለ ጠጣ ።
ነፍስያ ከተከለከለችው ነገር ሲፈቀድላት ደስተኛ ትሆናለች
ይህ ደስታ አጅር የሚያስገኘው ፁሞ ለማፍጠር በመጓጓቱ ነው።
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"ሰዎች ፈጡርን እስካቻኮሉና ስሑርን እስካዘገዩ(መጨረሻ ወቅት ላይ ሲበሉ) በመልካሙ ይዘወትራሉ(በኸይር ላይ ሆነው ይቆያሉ) ።"
በቀኑ ክፍለ ጊዜ የከለከለውን ምሽቱ ክፍለ ጊዜ ተፈቀደለት እንዲያው ም በፍጥነት መፍጠራ ቸውን ወደደላቸው።
ፆመኛ ስው ምግብ መጠጡን ,,,, ,,, የተወው ለአላህ ብሎ እስከሆነና በተመገበ ቁጥር አላህን ካመሰገነ በማፍጠረም አጅር ያገኛል።
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"ባሪያው አንዲትን ጉርሻ ጎርሶ ሲያመሰግነው ፣ አንዲትን ጉንጭ ጠጥቶ ሲያመሰግነው አላህ ይወድለታል።"
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"ተመግቦ አመስጋኝ የፁሞ ታጋሽ (ሰብረኛ) ደረጃ አለው።"
በማፍጠሪያው ሰዓት ዱዓው ተቀባይነት አለው።
ረሱል - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፦
"አንድፆመኛ በማፍጠሪያው ወቅት ተመላሽ የማይሆን(ፍፁም ተቀባይየሆነ) ዱዓ አለው።"
በመብላቱ,,, በዒባዳ ላይ ለመጠናከር ብሎ ከሆነ አጅር አለው።
"እኔ ከአልጋዬ ላይ ተኝቼ አጅር የማገኝበት ዒባዳ(አምልኮት) ምንኛ ያማረ የሚያስደስት መገዛት ነው። "
(ሐፍሳ رضي الله عنها)
" ፆመኛ ሰው ዒባዳ ላይ ነው ምንም እንኳ በአልጋው ላይ ቢተኛም። "
( رحمه الله አቡል ዓሊያ)
ይህን የተረዳ በማፍጠሪያው ጊዜ ደስታው ከላይ በተገለፀው መልኩ ሲሆን:የደስታው ምንጭ ከአላህ ችሮታና እዝነት በመሆኑ ነው።
በመፆሙ እየተበሳጨ አያጉተ መተመ በማፍጠሩ የሚደሰት ሰው አጅር የለውም።
2/ከአላህ ጋር ሲገናኝ ያለው ደስታ
ለፆመኞች የተዘጋጀውን ስፍር ቁጥር የሌለውን ታላቅ ምንዳ በሚያገኝ ጊዜ,,, ይደሰታል
ፆመኞች እንጂ ሌሎች የማይገቡበትን የረያንን ጀነት በሚገባ ጊዜ ይደሰታል
3/የፆመኞች እርከን (ደረጃዎች)
ሁለት ደረጃዎች ናቸው
1ኛውከአላህ ዘንድ ያለውን ታላቅ አጅር ለማግኘት ከምግብ መጠጥና ስሜት ራሳቸውን አቅበው ከርሱ ምንዳን ሸምተው ትርፋማ የሆኑት ሲሆኑ
ሌሎቹ ፆመኞች በዚህ ዓለም ባዱንያ ላይ ስለ አላህ ብለው በርሱ መንገድ ላይ ሁነው ከሀራም ነገሮች ታቅበው በመፆም የአኼራ ዒድ ሲደርስ በጀነት አላህ سبحان وتعالى ባዘጋጀላቸው ዓይን አይቶ የማያውቀውን ፣ ጆሮም ሰምቶ ያላወቀውንና ከሰው ልቦና ውስጥ ውል ማይለውን ፀጋ በልዩ መስተንግዶ በማፍጠራቸው ይደሰታሉ።
ውድ ወንድሜ
ነገ በአኼራ የማፍጠሪያ ዒዳችን ቋሚና ዘላቂ የሆነ የዘላለም ደስታ ለማግኘት ዛሬ ከስሜት ዝንባሌያችን እንፁም
'ገና ነው ፤ እደርስበታለሁ' የሚለውን ከንቱ ምኞት ከራሳችን እናሽቀንጥር፡፡ ከቀኑ ቀሪው ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ ሰዓቱ ረፋፍዷል፡፡ ጊዜ የለንም ገና ነው እደርስበታለሁ የሚለውን ከንቱ ምኞት ትተን ከቀኑ የቀረን ጥቂቱን ብቻ መሆኑን እናስታውስ።
መቼ እንደምንሞት አናውቀውም።
በዚች አላፊ ጠፊና ረጋፊ የዱንያ ህይወታችን ፁመን በነገው ዘላለማዊ እውነተኛ ህይወት በአኼራው የማፍጠር አውነተኛ መስተንግዶ ደስተኞች እንሁን
አላህ ደስተኛ
ከሚሆኑት ያድርገን
ኣ,,ሚ,,,,,ን
t.me/tezkiraChannel
240 viewsedited 04:20