Get Mystery Box with random crypto!

ታላቁ ዓሊም ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አልዑሠይሚን እንዲህ ይላሉ፦ . የሰው ልጅ ሩሁ በሰውነቱ እስካለች | ተዝኪራ - ትውስታ እና አደራ ስለ አኺራ - التذكرة فى الأمور الآخرة

ታላቁ ዓሊም ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አልዑሠይሚን እንዲህ ይላሉ፦
.
የሰው ልጅ ሩሁ በሰውነቱ እስካለች ድረስ ለፊትና የተጋለጠ ነው። ስለዚህ ራሴንና እናንተን አደራ የምለው ሁሌም አላህ ፅናት ይሰጠን ዘንድ መማፀንን ነው።
.
« መፍራት ይኖርብናል » ምክንያቱም እግሮች የቆሙት ሸርታታ (የሚያንሸራትት) ላይ ነው። አላህ ካላፀናን በቀር አንሸራቶን እንወድቃለን።
.
አላህ ለመልክተኛው ﷺ ፦
.
وَلَوْلَا أَنْ ثَبَّتْنَاكَ لَقَدْ كِدْتَ تَرْكَنُ إِلَيْهِمْ شَيْئًا قَلِيلًا
.
« ባላፀናንህም ኖሮ ወደነሱ ጥቂትን (ዝንባሌ) ልትዘነበል በእርግጥ በተቃረብክ ነበር።” ይህ ለመልክተኛው ﷺ ከሆነ ለኛስ ታዲያ.??
.
ኢማናችን ደካማ፣ ለእውነት የምናንገራግር፣ የአደናጋሪዎች ማደናገሪያ እና ስሜትን መከተል በቀላሉ ክፍተት የሚፈጥሩብን ሆኖ ሳለ አላህ እንዲያፀናን መለመን አይገባንምን.??
.
ከባድ አደጋ ላይ ነን በሀቅ ላይ ያፀናን ዘንድ ልንለምነው ይገባል። ልቦናችንን እንዳያዘነብልብንም መማፀን አለብን።
.
የአእምሮ ባለቤቶችም ዱዓ ይህ ነው፦
.
رَبَّنَا لَا تُزِغْ قُلُوبَنَا بَعْدَ إِذْ هَدَيْتَنَا
.
« ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን” ይላሉ።
.
[ ሸርሁል ሙምቲዕ - 5/388 ]
.
.
----------------------------------
ሁዳ መልቲሚዲያ- 🅗🅤🅓🅐
https://t.me/huda4eth