Get Mystery Box with random crypto!

#አልተሳሳትንም_ኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔር_ነው .......ብዙዎች በዘመናችን #የመጽሐፍ_ቅዱስን | ✥መ/ር ምህረተአብ አሰፋ ፔጅ✣

#አልተሳሳትንም_ኢየሱስ_ክርስቶስ_እግዚአብሔር_ነው .......ብዙዎች በዘመናችን #የመጽሐፍ_ቅዱስን ትምህርት ባለመረዳትና “ #እኔና_አብ_አንድ_ነን” ያለውን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነትን፣ ፈጣሪነት፣ ፍጹም ተዋሕዶውን ፈራጅነቱን በመካድ #ሎቱ_ስብሐት ከአብ አሳንሰው ርሱን #ለማኝ አብን #ተለማኝ ያደርጋሉ፤ ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከበፊት ጀምሮ እስካሁን ከመናፍቃን የሚደርስባት ፈተና ለምን ኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክ ነው? ለምን ከአባቱ ጋር የተካከለ ፈራጅ ነው? ብለሽ ታስተምሪያለሽ የሚል ነው፤
ይህም ዐዲስ አይደለም የባሕርይ አምላክነቱን፣ ተዋሕዶውን፣ ፈራጅነቱን ከካዱት ውስጥ ከቀድሞዎቹ እነ ጳውሎስ ሳምሳጢ፣ አርዮስ፣ ንስጥሮስ …. በ16ኛው መቶ ክ.ዘመን ወዲህ በየዘመናቱ የሚነሱ የእምነት ድርጅቶች ወ.ዘ.ተ ይገኛሉ፤ የእነዚኽን አስተምህሮ በምንማርበት የነገረ መለኮት ኮሌጅ ውስጥ ከደቀ መዛሙርት ጋር በክፍል ውይይት ጊዜ በጥልቀት የምዳስሰው ቢኾንም፤ ለ ፌስ ቡክ (face book) ጓደኞቼ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታስተምረውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈውን አስተምህሮ ጥቂቱን ከዚኽ በታች አስፍሬዋለኊ፡- ይኸውም በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰው እግዚአብሔር ከሦስቱ አካል አንዱ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመኾኑ የተጻፈውን የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን እውነት በማንበብ አረጋግጡ፡-

ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት እግዚአብሔር ነው እንላለን፡፡
►“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ”
➤(ዘፍ 1፡1) ╬ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው
➤” (ዕብ 1፡10)
►“እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። «ያለና የሚኖር» ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው”
➤ (ዘፀ 3፡14) ╬ “ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል”
➤ (ራእ 1፡8)
►“ለአንተ ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላክህም እግዚአብሔር ለዘላለም በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዝህን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቅ”
➤ (ዘዳ 4፡40) ╬ “እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን አዛችኋለሁ”
➤ (ዮሐ 15፡17)
►“አምላካችንን እግዚአብሔርን እናመልካለን፥ ድምፁንም እንሰማለን”
➤(ኢያ 24፡24) ╬ “ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና”
➤ (ቆላ 3፡24)
► “እግዚአብሔርን ብትፈሩ ብታመልኩትም፥ ቃሉንም ብትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ባታምፁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ፥ መልካም ይሆንላችኋል”
➤(1 ሳሙ 12፡14) ╬ “ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው”
➤(ዮሐ 8፡12)
► “አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው”
➤(1ነገ 8፡39) ╬ “ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክር አያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና”
➤ (ዮሐ 2፡25፤ 1ቆሮ 4፡5)
► “አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ”
➤(ነህ 9፡6) ╬ “ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ። የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ”
➤(ዕብ 1፡6) ╬ “ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ”
➤ (ፊልጵ 2፡10)
► “ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?”
➤(መዝ 17 (18)፡31 ╬ “እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው”
➤ (1ዮሐ 5፡20)
► “እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም”
➤(መዝ 22(23)፡1) ╬ “መልካም እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል”
➤(ዮሐ 10፡11)
► “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው?”
➤(መዝ 26(27)፡1) ╬ “ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው”
➤(ዮሐ 8፡12)
► “አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ”
(መዝ 46፡5) ╬ “ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ”
➤ (ሉቃ 24፡51)
► “ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል”
➤(መዝ 49፡2) ╬ “ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል”
➤(የሐዋ 1፡11)
► “ለስሙም ዘምሩ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ”
➤ (መዝ 65፡2)
“መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው”
➤(ፊልጵ 2፡11)

► “እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው”
➤ (መዝ 77፡65) ╬ “እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ”
➤(ማቴ 28፡6)

► “ይመጣልና በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል”
➤ (መዝ 95፡13) ╬ “ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም”
➤(ዮሐ 5፡22)

► “በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ በመከራቸውም አዳናቸው ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣቸው፥ እስራታቸውንም ሰበረ”
➤(መዝ 106፡13-14) ╬ “በጨለማ የተቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፥ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው”
➤(ማቴ 4፡16)

► “ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሕረት፥ በእርሱም ዘንድ ብዙ ማዳን ነውና እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን”

➤ (መዝ 129፡7) ╬ “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና
➤ (ቲቶ 2፡11)
► “እግዚአብሔር የወደደውን ይገሥጻልና፥ አባት የሚወድደውን ልጁን እንደሚገሥጽ”
➤ (ምሳ 3፡12) ╬ “እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና ንስሐም ግባ”
➤ (ራእ 3፡19)

► “ እነሆ፥ አምላክ መድኃኒቴ ነው ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ”
➤(ኢሳ 12፡2) ╬ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና”