Get Mystery Box with random crypto!

' #አዎ_እመቤቴ_ነሽ ' ምን ነው ዛሬ ሊቁ ቅዱስ ያሬድን በሆንኩ፣ ኤፍሬምንም በተካሁ ሕርያቆስን | ✝ ማነው ማርያምን ተው የሚለኝ ✝

" #አዎ_እመቤቴ_ነሽ "

ምን ነው ዛሬ ሊቁ ቅዱስ ያሬድን በሆንኩ፣
ኤፍሬምንም በተካሁ ሕርያቆስን በመሰልኩ፣
ገብርኤልን በሆንኩኝ ሰላም ለኪን በዘመርኩ።
ንዒ ንዒ ባልኩሽ ቁሜ አባ ጊዮርጊስን ተክቼ፣
ሰቆቃሽንም በጻፍኩ ጽጌ ድንግልን ሰምቼ።
አንድም በራዕይ ሆኖ ወይንም ሌሊት በህልሜ፣
ከፊትሽ ላይ ሰግጄ እመቤቴ ባልኩሽ ቁሜ።

#አዎ_እመቤቴ_ነሽ.........!!!!

አባ ጊዮርጊስን አልሁን የያሬድም ይቅርብኝ፣
አባ ጽጌ ድንግልን አልሆን ኤፍሬምንም አታሳይኝ፣
ሕርያቆስን ሁኜ ባልቀኝም ቅዳሴ፣
#አመቤቴ ልበልሽ በምችለው በራሴ።

#አዎ_እመቤቴ_ነሽ.........!!!

ንግስት አለሽ ዳዊት ቀድሞ፣
ሙሽራ አለሽ ልጁ ቆሞ፣
የተነበየልሽ ነቢዩ በትንቢት እንቅልፍ አልሞ፣
የታደሰብሽ ስምዖን የበኩር ልጂሽን ስሞ።
ድንግልም እናትም ሆነሽ የረቀቀብሽ ምስጢሩ፣
ሰማይ መሬትን ሆነሽ የልዑል አምላክ ሀገሩ፣
አሁን ምንድን ነው ነውሩ ስለ ቅድስናሽ መንገሩ።
ስለ ማርያም ማውራቱ ስለ ጽዮን ማስተማሩ?

#አዎ_እመቤቴ_ነሽ..........!!!

ድምጽሽን የሠማሁት ከእናቴ ማህጸን ስወጣ፣
ሀኪም ቤት ሳይኖር ቀድሞ አምቡላስም ሳይመጣ፣
እኔ ለመውለድ በምጥ ስትጨናነቅ እናቴ፣
ጎረቤቶቹ ቁመው እያሉ ነበር " #እመቤቴ "!
የሰማሁትን ቀድሜ እኔም እላለሁ እንደናቴ
ይህን ታላቅ ስም እንቁዕ የሚባለውን " #እመቤቴ !"

#አዎ_እመቤቴ_ነሽ..........!!!

አቅሙ ኑሮኝ ባልደርስም አዲስ ቅኔና ዜማ፣
ባልሰማቼውም ምስጋናሽን መላእክቱንም ከራማ፣
የደረሱትን አባቶቼ የሚገባውን ከአንጄቴ፣
" ሰአሊ ለነ "ልበልሽ ፍቀጂልኝ እመቤቴ!!!

የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ ለማግኘት //
https://t.me/manew_maryamn_tewyemilegn