Get Mystery Box with random crypto!

የምክር ቃል ❖ የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው፤ ከሰይጣን በቀር | ✝ ማነው ማርያምን ተው የሚለኝ ✝

የምክር ቃል

❖ የበደሉንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሳይሆን ፍቅርን ማስተማር ነው፤ ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡
❖ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህን ኃጢአት አትግለጥ፡፡
❖ የባልጀራህን ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፤ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡
❖ ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፤ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡
❖ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው።
❖ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱ ልክ በእሳት ፊት እንደ ወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡
❖ ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፤ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፤ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹሕ ይሁን፤ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደ ተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡❖ ቃላቶችህ የተመጠኑና ጤናማዎች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡
❖ የጓደኛህን ምሥጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፤ ወደ ጭቅጭቅና ንትርክ ከመግባት ራስህን ጠብቅ፤ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ ለማግኘት //

https://t.me/manew_maryamn_tewyemilegn