Get Mystery Box with random crypto!

#ልደታ__ማርያም #ድንግል_ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐ | ✝ ማነው ማርያምን ተው የሚለኝ ✝

#ልደታ__ማርያም

#ድንግል_ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤
በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ) (አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም)
#ልደቷን_የጨለማችን መገፈፍ የዐይናችን ማየት የብርሃናችንም መዉጣት ነዉና በፍጹም ደስታ እናስበዋለን እናከብረዋለንም፡፡"
#እመቤታችን የተወለደች እለት አባቷ ኢያቄምና እናቷ ሀና ከመጠን በላይ ተደሰቱ:: የእመቤታችን ልደት #ዓለም ማየት የጀመረበት ዕለት ነዉ ማለት ነዉ፡፡ በጨለማ ሲያዩት የሚያስፈራዉና ሌላ የሚመስለዉ ጉቶ ቁጥቋጦዉ ድንጋዩ ጉብታዉ ሁሉ ተራ ነገር መሆኑ የተጋለጠባት ሰዎችም የሰገዱለት ሁሉ አምላክና ጌታ መሆኑ ቀርቶ ድንጋይ ጉብታ መሆኑን ማየት የጀመሩባት ከደገኛዉ ፀሐይ ክርስቶስ ከመውጣት በፊት ከረጅሙ ዘመን ጨለማ ጭንቀት የተገላገልንባት ጨረቃ ብርሂት የቀኝ ዐይን #እመቤታችን_ማርያም ናት ፡፡ ስለዚህም ልደቷን የጨለማችን መገፈፍ የዐይናችን ማየት የብርሃናችንም መዉጣት ነዉና በፍጹም ደስታ እናስበዋለን እናከብረዋለንም፡፡
#እመቤታችን_እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን ከልደቷ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን ።


#_ሰናይ_ቀን

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
•➢ ለማግኘት //

@Enatachn_mareyam
@Enatachn_mareyam