Get Mystery Box with random crypto!

Dr. Tesfaye Robele

የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfayerobele — Dr. Tesfaye Robele D
የቴሌግራም ቻናል አርማ tesfayerobele — Dr. Tesfaye Robele
የሰርጥ አድራሻ: @tesfayerobele
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.60K
የሰርጥ መግለጫ

ተስፋዬ ሮበሌ (ዶ/ር) ሥነ መለኮት እና ፍልስፍና ያጠና ባለ ጥልቅ እውቀት አቅብተ እምነት ነው። ሥነ መለኮትን እና ፍልስፍናን ለመማር ከፈለጉ ይቀላቀሉን።
ይህ ቻናል የራሱ (የዶክተር ተስፋዬ) አይደለም፤ ነገር ግን እኛ መውደዳችንን ለመግለፅና ሰው ሁሉ የእርሱን ጽሑፍ ወይም ቪድዮ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ካለን ፍላጎት የተከፈተ ነው።
Ethiopia No: 251923439161
@chereGC

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-04 16:47:20 major cult - ዐበይት መናፍቃን
ተስፋዬ ሮበሌ 1994 ዓ.ም
Tesfaye Robele 2001
1.5K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 14:46:26 Argument from silence! ሙስሊሞች በብዛት ይህንን ጥያቄ ይጠይቃሉ። ለዚህ ጥያቄያቸው ምላሽ የሚሆኑ ሌሎችም በዚህ የዩትዩብ ቻናል ላይ ተመልሰዋል። ይህንን ቪድዮ እስከ መጨረሻው ስትሰሙት በጽሁፍም የተብራራውን የተስፋዬ ሮበሌን መልስ ታገኛላችሁ። ስለዚ ክርስቲያኖችም ሁኑ ሙስሊሞች ከዚህ ቪድዮ በኋላ ጥያቄ እንደማታነሱ ተስፋ አደርጋለው። አይኔን ግንባር ያድርገው ጆሮዬንም በጥጥ ይድፈነው ካላላችሁና የህሊናችሁን ወቀሳ አልሰማም ካላላችሁ በቀር መረዳት ያለባችሁ የመጨረሻ ነገር ይህ ነው። ስላዳመጣችሁት ተባረኩ!!

ሙስሊሞች ለኡስታዞቻችሁ Share አድርጉላቸው። ክርስቲያኖች ደሞ ለክርስቲያኖች፣ እንዲሁም ሙስሊም ጓደኞች ያላችሁ ደሞ ለጓደኞቻችሁ Share አድርጉላቸው። ቻናሉንም SUBSCRIBE በማድረግ ይህንን የወንጌል ስርጭት አገልግሎት ደግፉ።



1.7K views11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 08:58:59
በዚህ ትምህርት ላይ የምትገኙ ወጣቶች የትምህርት ጊዜውን ሪከርድ በማድረግ እንድትልኩልን በትኅትና እንጠይቃለን!
2.8K viewsedited  05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 10:32:01 ክፍል 3
ከፓስተር ሱራጅ ሪቦ እብራሂምና ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ ጋር
የሥላሴ ትምህርት በ ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ 04/01/2022



3.3K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 10:30:37 ክፍል 2
ከፓስተር ሱራጅ ሪቦ እብራሂምና ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ ጋር ስለስላሴ ትምህርት የተደረገ አስገራሚ ዉይይት 03/25/2022



3.0K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-10 10:25:02 ክፍል 1
ፓስተር ሱራጅ ሪቦ እብራህም እና ዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ ጋር በአስተምሮተ-ስላሴ ላይ የተደረገ ድንቅ ዉይይት 03/18/2022



2.9K viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 10:07:38
በርግጥ ሰው መንፈስ፣ ሥጋም የመንፈስ ታዛ ነውን?
(አከርካሪ ስበር)
ከተስፋዬ ሮበሌ
ይህን ትምህርት ለሌሎች አካፍሉ! ከኑፋቄም አድኗቸው!
ክፍል 1
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3014847878839313&id=100009423928968
ክፍል 2
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3014853888838712&id=100009423928968
ክፍል 3
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3015999832057451&id=100009423928968
ክፍል 4
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3016000258724075&id=100009423928968
2.9K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 22:37:49 ነዳጅና ሥነ አመክንዮ
ኢትዮጵያ ውስጥ ሥነ አመክንዮና ነዳጅ እንደሌለ ይታወቃል!
አሜሪካን ያላችሁ ኢትዮጵያ ላሉ ወዳጆቻችሁ ይህን ጠቃሚ መጽሐፍ ብትወስዱላቸ ጥሩ አይደለምን?
ስለ ነዳጅ እንጸልያለን!
3.8K views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 18:24:59 አራት ጥራዝ መጻሕፍት!
ከተስፋዬ ሮበሌ
ፍልስፍናዊ ነገረ መለኮት ላይ አራት ቅጽ ተከታታይ መጻሕፍትን ማዘጋጀት ከጀመርሁ ቆየሁ! የመጀመሪያው ቅጽ፣ "የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የሰብአውያን ነጻ ፈቃድ!" በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው!
ምናልባት እስካሁን ካዘጋጀኋቸው መጻሕፍት ይልቅ፣ እነዚህ ሥራዎች በብዙ እርጋታና በትልቅ ትጋት የሚነበቡ መጻሕፍት ናቸው! "ከዚህ በፊት የጻፍኻቸው ከብደውኛል፣ ለመረዳት ተቸግሬአለሁ" የሚሉ ሰዎች፣ እነዚህን መጻሕፍት እንዳይገዙ እንዳያነቡም እመክራለሁ! "ጦሳችሁን ይውሰድ!"
ቢከብድም በትዕግሥትና በትጋት የተላለፈውን ትምህርት እመረምራለሁ፣ እውነትን ገንዘቤ አደርጋለሁ የሚሉ፣ "ልባም የቤርያ ሰዎች" ብዙ እንደሚጠቀሙ ቃሌን ልሰጣቸው እችላለሁ!
ለምሳሌ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቅድመ ምዳቤ ከሰብአውያን ነጻ ፈቃድ ጋር የሚታረቅ አይመስላቸውም! ወይም የሰብአውያን ነጻ ፈቃድ ከዘላለም ዋስትና ጋር የሚጣጣም አይመስላቸውም! ከዚህ የተነሣ አንዱን በመካድ ሌላውን ማመን ዕጣ ክፍላችን ሆኗል! በዚህ አግባብ አገሪቱ በሁለት ተከፍላለች--
ከዚህም የተነሣ ወይ በወንድም ካልቪን ወይ በወንድም አርሜኔዎስ አንጻር መሰለፍ የግድ ሆኖል! [የአምላክን የመጻኢ ዘመን ዕውቀት የማይቀበሉ፣ “ክፍት አማኒያን" (Open Theism) እንዳሉ በጭምጭምታ ሰምቻለሁ! አንድ ወይም ሁለት!]
ለሃያ ሰባት ዓመት የወንድም ካልቪን ዐስተሳሰብ ትክክል ይመስለኝ ነበር! ብዙዎች ይህን ነባቤ ቃል እንዲቀበሉ በብዙ ሞግቻለሁ! (ይህን በመሞገት ቁጥር አንድ ሳልሆን አልቀርም!) ለድኅረ ምረቃ ካልቪን የነገረ መለኮት ትምህርት ቤት ሲሄድ አርሜናውያን የሆኑ ብዙ ወዳጆቼ፣ "እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ!" ብለው ነበር!
ካልቪን በነበርሁበት ወቅት የትምህርት ቤቱ የበላይ ኀላፊ የስመ ጥሩ የሃይማኖት ፈላስፋ የአልቪን ፕላንቲንጋ (Alvin Plantinga) ታናሽ ወንድም ቆርኔሌዎስ (ኒል) ፕላንቲንጋ (Cornelius Plantinga Jr) ነበር! እርሱን ጨምሮ በርካታ የትምህርት ቤቱ ዕውቅ መምህራን "ካልቬኒዝም በግማሽ ተሳስቶአል" የሚል አቋም ያላቸው እንዲሁም "የመኻል ዕውቀት" (Middle Knowledge) ይህን ክፍተት ይሞላል የሚል ዐስተሳሰብ የሚያራምዱ ሆነው ተገኙ!
ኋላም ታይም መጽሔት (Time magazine) “America’s leading orthodox Protestant philosopher of God.” (1980 ዓ.ም) ሲል ያደነቀው አልቪን ፕላንቲንጋ፣ ከኖተርዳም ዩኒቨርስቲ ወደ ካልቪን "Harry Jellema " በሚባለው ወንበር ተሰይሞ መጣ! በዚህ ጊዜ ነው "Warranted Christian Belief" የተባለውን ኮርስ በራሱ በአልቪን ፕላንቲንጋ ሥር የመማር ዕድል ያገኘሁት!
በዚህ ጊዜ ነበር "የካልቬኒዝም" ዐስተሳሰቤ ትልቅ አደጋ የገጠመው! ከዚያ ኋላ ነገሩን በጥሙና መመርመር ጀመርሁ! አቋም ለመያዝ ግን ስድስት ዓመት ያህል ፈጀቶብኛል (በዚህ ረገድ ያሉ መጻሕፍት ውስብስብ እንዲሁም ብዙ ናቸው)! ከዚያም "የመኻል ዕውቀት" (Middle Knowledge) ዐስተሳሰብን ተቀበልሁ! ይሁን እንጂ ዛሬም ካልቪናዊነት ያሳዝነኛል! አንጀቴን ይበላዋል! (ዐፈር ልብላ!)
የዚህ ዐስተሳሰብ ባለቤት Alvin Planning ብቻ አይደለም! የካቶሊኩ ኢየሱሳዊ (Jesuit) ቄስ ልዊስ ሞሊና (Luis de Molina) ከ500 ዓመት በፊት ይህ ዐይነት ዐስተሳሰብ ያራምድ እንደ ነበር ይነገራል!
calculusን Isaac Newton እና Gottfried Leibniz በተለያየ ወቅትና መንገድ እንዳገኙት ሁሉ! "የመኻል ዕውቀትን" (Middle Knowledge) ያገኙት ፕላንቲንጋና ሞሊና ናቸው! ዐሳቡን በጥልቀት በመተንተን ብዙ ፈላስፎች እንዲቀበሉት ያደረገው ግን ፕላንቲንጋ ነው!
የኦክስፎርዱ የሃይማኖት ፈላስፋ Richard G. Swinburne
"በአልቪን ፕላንቲንጋ መጠን ትልቅ ተጽእኖ የፈጠረ ኀላዪ (thinker) እኔ አላውቅም" ያለለት ትልቅ ሰው ነው! በሕይወት እያለ ከ30 ሰዎች በላይ የዶክትሬት መመረቂያ ጽሑፋቸውን የጻፉበት አስደናቂ ሰው ነው! ዛሬ የዚህ ሰው ዐስተሳሰብ ብዙ ተከታይ እያገኘ ተቃዋሚዎቹን እየናጠ ነው! ብዙ የካልቬኒዝም አፈ ቀላጤዎች ለዚህ ዐስተሳሰብ እጃቸውን ሰጥተዋል! በቅርቡ እንኳ ታዋቂው የካልቬኒዝም ተሟጋችና የ"Southern Baptist Theological Seminary" የደርዛዌ መለኮት ፕሮፌሰር Bruce A. Ware ይህን አስተምህሮ ተቀብሏል! YouTube ላይ በብዛት የምታገኙት ግን ካልቬኒዝምን ወክሎ ሲሟገት ነው!
እርሜኒዮስ ከካልቪን ጋር ይታረቃል እያልህ ነው? ለምትሉኝ መልሴ እንዴታ ("ስነግርህ!")
እንደ ኒቆዲሞስ በስውር (በሌሊት) ልታወያዩኝ የምትፈልጉ የነገረ መለኮት ሰዎች በስውር ምክር ልሰጥ እችላለሁና አግኙኝ! ደግነቴ መቼ ነጥፎ ያውቃል!
ትሕትና የዕውቀት ቁልፍ ናት!
3.1K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 18:24:32
አራት ጥራዝ መጻሕፍት!
ከተስፋዬ ሮበሌ
2.2K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ