Get Mystery Box with random crypto!

የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

የቴሌግራም ቻናል አርማ uraman4u12 — የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ
የቴሌግራም ቻናል አርማ uraman4u12 — የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ
የሰርጥ አድራሻ: @uraman4u12
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.44K
የሰርጥ መግለጫ

በዚሕ ቻናል የእመቤታችን ዉዳሴዋ ንባቡና ትርጓሜዉ በአንድምታ ይቀረባል። ከኛ የሚጠበቀዉ መማር ብቻ ነዉ። አምላክ ከኛ ጋ ይሑን የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን።
ሐሳብ አስተያየት
👇👇👇👇👇👇
@woladite11

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 07:19:43 አፄ ዘርዓ ያዕቆብ በመልክአ ማርያም ድርሰታቸው እንዲህ ሲሉ ለእመቤታችን ምስጋናን አቀረቡ።

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ መካነ ፍሥሓ ምጡቀ፡ በአእባነ ባሕርይ ዘተነድቀ፡
ማርያም ድብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ፡
ጽሒፈ ውዳሴኪ እምኪ ኀልቀ ሶበ ኮነ ጥቀ፡ ዝናመ ክረምት ቀለመ ወሰማይ ረቀ።

እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። ይኸውም ኅብሩ ሊመረምሩት በማይቻል ዕንቁ የታነፀ ሕንፃ ይገኝበታል። ድንግል ሆይ የማቅና የጨርቅ ያይደለ የብርሃን ድንኳን ነሽ። የክረምት ዝናም ቀለም ሰማያት ወረቀት ቢሆኑ ምስጋናህ ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም።

ስብሐት ለኪ ማርያም በኁልቆ ኩሉ ሥዕርትየ
ስብሐት ለኪ ማርያም በኁልቆ ኩሉ አዕፅምትየ
ስብሐት ለኪ ማርያም በኁልቆ ኩሉ ዘተርእየ
ስብሐት ለኪ ንግሥትየ በኁልቆ ኩሉ ዘኢያስተርእየ
ስብሐተ ድንግልናኪ ዘልፈ ይነግር አፉየ

እመቤቴ ማርያም ሆይ በራስ ፀጉሬ ቁጥር አመሰግንሻለሁ። በአጥንቶቼ ቁጥር አመሰግንሻለሁ። ድንግል ሆይ በሚታየውና በሚዳሰሰው ሁሉ ቁጥር አመሰግንሻለሁ።
ንግሥት ሆይ በማይታየውና በማይዳሰሰው ሁሉ ቁጥር ሰላም እያልሁ የድንግልናሽን ምስጋና አፌ ሁል ጊዜ ይናገራል።

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ያካፍለን።
የአባቶቻችንን መንፈስ ያሳድርብን።
2.9K views@azy@, 04:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 16:32:30 ነሐሴ 16 እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
☞ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው፡፡
☞የዕረገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
☞ትንሻኤሽ እውነት ነው ሰበዝንሽ አይተናል
☞ሞትማ በሞት ተሸንፍል
☞በአንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ሆይ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል
የክርስቶስ የትንሣኤው ምሳሌ ለሆነ የሥጋሽ ትንሣኤ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ሕያው የሆነ ባሕርዩን በውስጧ
ሠውሮ ከሞት ለተነሣባት የክርስቶስ ትንሤኤ መንትያ ለሆነች ትንሣኤ ሥጋሽ
ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመብቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ አንቺን ለሚያመሰግኑ ቅዱሳን ሰዎች
ሁሉ የዕርገታቸው ምሳሌ ለሆነ ዕርገተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እመቤቴ
ማርያም ሆይ የካህናት አለቃ የተባለ የአሮን የሽቱ ጌጥ አንቺ ነሽ በአንደበታችን
የሚነገረው የምስጋናሽ ፍሬ ሁሉ በውስጥ በውጭ ባለው ልብስሽ ላይ በሥዕል
መልክ ተቀርጾ ይኑር፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ እግዚአብሔር ለተዋሐዳትና ሥነ
ሥርዓቷን ለተካፈላት ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ በፍለስትሽ ጊዜ በምድረ ይሁዳና በኢየሩሳሌም
አደባባይ የተርሴስና የደስያት ነገሥታት ስለ ክብርሽ መዓዛቸው የጣፈጠ ልዩ ልዩ
እጅ መንሻዎችን አቀረቡልሽ ሰገዱልሽም፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከሴሎ ነቢይ ከኤልያስ ፍልስት ይልቅ
እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ላደረገው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከዚህ በፊት የልጅሽ ሥጋ ወደ
ፈለሰበት ወደ አዲሱ የሕይወት ሕንፃ አዳራሽ ለተዛወረው የሥጋሽ ፍልሰት
ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ጥበበኛዋና ሐናፂዋ በሆነ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ አማረው ተድላ ደስታ ወደ አለበት ለፈለሰው ፍልሰተ
ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ እጅግ መሪር ከሆነ ከሞት አገዛዝ እኔን ልጅሽን ነፃ
አውጭኝ የሰማይ የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ አንቺ ከፈቀድሽ ኃጥኡን ጻድቅ
ማድረግ ይቻልሻልና፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ሕያዊት ከሆነች ነፍስሽ ጋር በፍጹም
ተዋህዶ ለተከናወነው ፍለሰተ ሥጋሽ ፈጽሞ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ፈጽሞ ኅዘንና ትካዜን ወደ ማያስቡበት
ደስታ ወደ አለበት ለተጓዘው ፍለሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በምስራቃዊ ተክለ ገነት መካከል
የብርሃን ድንኳኖች ወደ ተተከሉባት ለዐረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡ ድንግል
ማርያም ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ሰለሆነ በሰማይ ካሉ
መላእክትና በምድርም ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ሊቀርብልሽ
ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ከፀሐይ ከጨረቃ ስነ ጸዳል ይልቅ
ፈጽሞ ለሚያበራው ፍጹም ምስጋና ለተገባው ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባሻል፡፡
☞ድንግል ማርያም ሆይ ቀናንም የተባለ ሽቱ ነሽ የልዩ ሽቱ ዐይነትም መገኛነሽና
ስለዚህም ብርሃንን ለብሰው የብርሃን ነጸብራቅ ተገናጽፈው የፍልስትሽን በዓል
መላእክት ያከብራሉ፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የጌታ ወዳጅ ከሆነ ያዕቆብ ፍልሰት
ይልቅ ይክብርና ምስጋና ለተሰጠው ፍለሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ክብሩ ለማይጠፋ ባለሟልነቱ
ለማይጎድል የሰዎችን ልብ ደስ ለሚያሰኝ ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ የእግዚአብሔር የምስጋናው አዳራሽ ስለሆንሽ
በፍልስትሽ ጊዜ አንቺ የተቀበሉ መላእክት ሁሉ ማርያምስ በሰማይና በምድረ
የከበረች ነች ተባባሉ፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ለተመረጡት ለአዳምና ለሄዋን ልጆች
እናት ትሆናቸው ዘንድ ምጡቅ በሆነ በብርሃን ሠረገላ በክብር ተቀምጦ ለዓረገ
ፍልሰተ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በሥጋዊና በደማዊ አንደበት ሁሉ
ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ በመላእክት አንደበት ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡ እመቤቴ
ማርያም ሆይ የደብተራ ኦሪት ቃል ኪዳን የተጻፈብሽ የሕግ ታቦት ለአንቺ ምስጋና
ይገባል፡፡ የጌታ ባለሟል በሆኑ ቅዱሳን ጉባኤ ፊትም ለአንቺ ምስጋና ይገባል፡፡
አሜን፡፡
544 views@azy@, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 16:32:26
431 views@azy@, 13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 16:29:55
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።

[ ]#ድንግል_ድንግል[ ]

ድንግል [፪] ወላዲተ ቃል [፪]

አሟሟትሽ በጥር ነሀሴ መቃብር ---------ድንግል
ያንቺስ ለብቻ ነው ትንሳኤሽ ሲነገር ------ድንግል
ስጋሽ በምድር ላይ የታል እንደፍጡር ----ድንግል
አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር-- ድንግል

ስጋሽን ሲያሳርጉ መላዕክት ከሰማይ --- ድንግል
ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ --- ድንግል
መግነዝ ተረከበ ከሀዋርያት ሊያሳይ ---- ድንግል

ትንሣኤን ሽተው ግራ ሲገባቸው------ ድንግል
ሀዋርያት ጾመው ተገለጥሽላቸው -----ድንግል
ተቀብራ አልቀረችም በምድር ከደጇ --ድንግል
ወደላ አረገች እርሷም እንደ ልጇ-------ድንግል

ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሣኤ---- ድንግል
እርገቷን አወቁ በብዙ ሱባዔ ---------- ድንግል
እኛም እንፀልይ ደጃችንን እንዝጋ ----- ድንግል
ከወላዲት አምላክ እንድናገኝ ዋጋ -----ድንግል
928 views@azy@, 13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:09:21 ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን አእምሮውን ጥበቡን በልቦናችን ሳዪልን አሳድሪልን፡፡
#ቅድስት አለ ንጽሕት ጽንዕት ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡
#ንጽሕት አለ :- ሌሎች ሴቶች ቢነጹ ከነቢብ(ከቃል ከመናገር)፣ ከገቢር(ከሥራ ከድርጊት) ነው ፤ ከሐልዮ (ከሐሳብ) አይነጹም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ (ከቃል ከመናገር) ፣ ከገቢር(ከሥራ ከድርጊት) እና ከሐልዮ (ከሐሳብ) ንጽሕት ናትና፡፡
#ጽንዕትም አለ :- ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፡፡ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ጸኒስ(ከመጸነሷ በፊት)፣ ጊዜ ጸኒስ (በጸነሰች ጊዜ) ፣ ድኅረ ጸኒስ (ከጸነሰች በኋላ) ፣ ቅድመ ወሊድ (ከመውለዷ በፊት) ፣ ጊዜ ወሊድ (በወለደች ጊዜ) ፣ ድኅረ ወሊድ (ከወለደች በኋላ) ጽንዕት በድንግልና ናትና፡፡
#ክብርትም አለ:- ሌሎች ሴቶችን ብናከብራቸው ጻድቃን ሰማዕታትን፤ ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳትን፤ ቀሳውስት ዲያቆናትን፤ ነገሥታት መኳንንትን ወልዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ፣ እመ አምላክ፣ እመ ብርሃን ብለን ነውና፡፡
#ልዩም አለ:- እናትነት ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችም ወደፊትም አትኖርምና ፡፡
#ሰአሊ_ሠዓሊ ለነ አለ፡፡ ዐይኑ ‹ዓ› ነው ያሉ እንደሆነ (ሠዓሊ ለነ) አእመሮውን ለብዎውን ሳይብን አሳድሪብን ማለት ነው፡፡ አልፋው ‹አ› ያሉ እንደሆነ (ሰአሊ ለነ) ለምኚልን ማለት ነው፡፡
መልካም ሱባኤ ይሁንልን!!!
4.2K views@azy@, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:44:11 #እንካን ለጾመ ፍልሰታ አደረሳቹ አደረሰን !

ጾም በሐዲስ ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡
ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አብነት በማድረግ ጾምን በአዋጅ እንድንጾም በቀኖናዋ (በሥርዐቷ) ደንግጋለች፡፡
በቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-

ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ)

ጾመ ነነዌ

ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ)

ጾመ ጋድ

ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)

ጾመ ፍልሰታ

ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)

ጾመ ፍልሰታ

ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው።

እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅድስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር።

ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች አስከሬኗን ገንዘውና ከፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤ ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር።

‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር።

ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለእመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች።ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት በረከት ይክፈለን።
961 views@azy@, 11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:44:05
653 views@azy@, 11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 18:10:29 “ዮሐንስ በእናቱ ሆድ ውስጥ ሆኖ የድንግል ማርያምን ድምፅ ሲሰማ የተሰማውን ደስታ መናገር ባይችልም ፣ ‘የተባረክሽ ነሽ’ ብሎ ለማመስገን ባይታደልም እናቱ ኤልሳቤጥ ግን ልጅዋን ወክላ ‘በደስታ ዘለለ’ ብላ ተናገረችለት፡፡ እርሱ ቃል አውጥቶ ማመስገን ባይችልም እናቱ የጌታን እናት አመስግና የልቡን አደረሰችለት፡፡ እርሱ በመዝለልና በመስገድ እናቱ ደግሞ በታላቅ ድምፅ በማመስገን ድንግል ማርያምን ተቀበሏት፡፡

በእናቱ ሆድ ውስጥ ያለ ሕፃን ‘ኖር’ ብሎ እጅ ነሥቶ የሚቀበላት ክብርት እንግዳ ከድንግል ማርያም በቀር ወዴት አለች? ገና ያልተወለደ ልጅ ድምፅዋን ሰምቶ ከእናቱ ሆድ ለመውጣት ከጓጓላት ማርያም ስም በቀርስ ሴት ልጅ ምጥ ላይ በሆነች ጊዜ ልጁን ልውጣ ልውጣ ለማሰኘት ሊጠራ የሚገባው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስም ምን አለ? ዮሐንስ በእናቱ ሆድ ሳለ የድንግል ማርያምን ድምፅ ስለሰማ ከተወለደ በኋላ የዓለምን ድምፅ መስማት አስጠልቶት ወደ በረሃ ሸሸ፡፡

አረጋዊው ስምዖን ‘ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ’ እንዳለ ዮሐንስም ‘ጆሮዎቼ የእናትህን ድምፅ ሰምተዋልና ባሪያህን አሰናብተኝ’ ብሎ ለዓለም የሞተ ሆኖ በበረሃ ኖረ፡፡ ድንግሊቱን የሰሙ ሰዎች ልባቸው ወደ ምናኔ ሕይወት ያዘነብላል፡፡ ወደ ምድረ በዳ ሔደው ድንጋይ ተንተርሰው ሲተኙ ደግሞ እንደ ያዕቆብ እግዚአብሔር በላይዋ የተቀመጠባትን መሰላል ያያሉ፡፡

በማሕፀን የነበረውን ዮሐንስን በትኩረት ሳስበው በቤተ ክርስቲያን ያሉ የዋሀን ምእመናንን ይመስለኛል፡፡ በድንግል ማርያም ፍቅር ልባቸው እየነደደ ስምዋን ሲሰሙ ፣ ምስጋናዋን ሲያዩ የሚናገሩት የሚጠፋቸው ፣ እመብርሃንን እየወደዷት ቃላት አሳክተው ስለ እርስዋ ለመናገር ግን አንደበት የሚያጥራቸው ምእመናን ይታዩኛል፡፡ በቅኔ ማኅሌቱ ዳር ቆመው ማኅሌት ሲቆም ለጌታና ለእናቱ ምስጋና ሲቀርብ እንደ ዮሐንስ የሚይዙት የሚጨብጡትን አጥተው በደስታ የሚዘልሉ ፣ አንድም ቃል ከአፋቸው ሳይወጣ በሐሴት የሚሰግዱ ብዙ የዋሃን ምእመናን ትዝ ይሉኛል፡፡

ወዳጄ አንተም ድንግሊቱን ለማመስገን እንደ ዮሐንስ መናገር ካቃተህ ብዙ አትጨነቅ፡፡ መንፈስ ቅዱስን የተመላች እናትህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከኤልሳቤጥ በላይ ለድንግሊቱ የሚሆን ብዙ ምስጋና አላትና ለንግግርህ ሳትጨነቅ በደስታ እየዘለልህ አጅባት፡፡ በእናትህ ቤተ ክርስቲያን ሆድ ውስጥ እንደ ያዕቆብና ኤሳው ለብኵርና እየተጣላህ ሆድዋን መርገጥህን ትተህ እንደ ዮሐንስ ለምስጋናና ስግደት ከተጋህ ቤተ ክርስቲያን ፍቅርህን አይታ ምስጋናን ታስተምርህና እርስዋ ‘የጌታዬ እናት እንዴት ወደ እኔ ትመጣለች’ እንዳለች አንተም ነፍስ ስታውቅ እንደ ዮሐንስ ‘ጌታ ሆይ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?’ ብለህ ለመናገር ትበቃለህ”
216 views@azy@, 15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 07:47:07
#ጠላትን #ለምን #ከፋዉ

እኔዉ ጎንበስ ብዬ እኔዉ ቀና ላልኩት
እንዉ አመስግኜ እኔ ለሰገድኩት
ጠላት ምን ተነካ የሚያረዉ በቅናት
እመቤቴ ብዬ እኔዉ ለወደድኳት
ያንድዬ እናት ብዬ እኔዉ ከወደድኳት
ብወድቅ ብነሳ እኔዉ ካልደከመኝ
ሳወድሳት ብዉል እኔን ካልሰለቸኝ
ስማፀናት ባድር እኔዉ ካልታከተኝ
ጠላት ምን አገባዉ አትስገድ የሚለኝ
ፃድቃንን አይቼ እኔ ብማፀናት
ገብረኤልን አይቼ እኔ ባወድሳት
ሰማህታትን አይቼ እኔ ብሞትላት
አምላክን አይቼ እኔ እሷን ብመርጣት
ልጄ ስላለችኝ እናቴ እላልኳት
ጠላት ለምን ከፋዉ እኔ እሷን ብወዳት
አፅናንተሽኝ አይቻለዉ ሲከፋኝ እናቴ
ሚስጥረኛዬ ነሽ ገፀ በረከቴ
አልተዉሽም እስከ ለተ ሞቴ

የፍቅር እናት ፍቅር ታድለን
510 views@azy@, 04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 07:36:16 33ቱ የእመቤታችን በዓላት
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ሠላሳ ሦስቱ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት እነዚህ ናቸው፡-
ነሐሴ 7- እመቤታችን የተፀነሰችበት ዕለት፡፡
ነሐሴ 16- ሥጋዋ የፈለሰበት/በልጇ ኃይል ከሞት ተለይታ የተነሣችበትና ወደ ሰማይ ያረገችበት ዕለት፡፡
ከነሐሴ 17 እስከ ነሐሴ 21 ድረስ ለ5 ቀናት ትንሣኤዋ እንደልጇ ትንሣኤ ይከበራል፡፡ የጌታ ትንሣኤ አንድ እሑድ ቀን መኾኗ የታወቀ ቢሆንም የትንሳኤው መታሰቢያ እስከ 50 ቀናት ማክበራችንን እናስታውስ የእመቤታችንም እንደዚሁ ነው፡፡
ነሐሴ 18 የትንሳኤዋ መታሰቢያ
ነሓሴ 19 የትንሳኤዋ መታሰቢያ
ነሐሴ 20 የትንሳኤዋ መታሰቢያ
ነሓሴ 21 የትንሳኤዋ መታሰቢያ
መስከረም 10- ሥጋን የለበሰች የምትመስለውና ብዙ ተአምራት ታደርግ የነበረችው የእመቤታችን ሥዕል ፄዴንያ ወደተባለ አገር ገብታ የተቀመጠችበትን ዕለት፡፡
መስከረም 21 ትከብራለች፡፡ አርዮስን ለማውገዝ በ326 ዓ.ም በኒቅያ የተሰበሰቡት ቅዱሳን ከሚያዝያ እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ በመሆኑ የመስከረም ማርያም (ብዙኃን ማርያም) ተብሎ በዓሏ ይከበራል፡፡ እንዲሁም ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የክርስቶስን ቅዱስ መስቀል ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በመስከረም 21 ቀን ስላስገቡ ምእመናን በዓሉን በግሸን ማርያም ያከብሩታል፡፡
ጥቅምት 21- ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡
ኅዳር 6- ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል ሀገር ገብታ ያረፈችበት ዕለት፡፡
ኅዳር 21- ጽላተ ሙሴ አክሱም ቤተ መቅደስ ተሠርቶላት በክብር ያረፈችበት ዕለት፡፡ ዳግመኛም ካህኑ ዘካርያስ የእመቤታችን ምሳሌ የሆነውን የመቅረዝ ፋና ሲበራ ያየበት ዕለት ነው፡፡
ታኅሣሥ 3-በሦስት ዓመቷ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት፡፡
ታኅሣሥ 21 ትከብራለች፡፡ የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡
ታኅሣሥ 22- ብሥራተ ገብርኤል (ቅዱስ ደቅስዮስ እመቤታችን ጌታን የፀነሰችበትን የመጋቢት 29 ቀንን በዓል በዚህ ዕለት አከበረ)፡፡
ታኅሣሥ 28- ጌታችንን የወለደችበት የመታሰቢያ በዓል (በ4 ዓመት አንድ ጊዜ ወርሃ ጳጉሜን 6 ቀን ስትሆን ልደት በ28 ይውላል)፡፡
ታኅሣሥ 29- ጌታችንን በድንግልና የወለደችበት የመታሰቢያ በዓል፡፡
ጥር 21- እመቤታችን በ64 ዓመቷ ያረፈችበት ዕለት፡፡
የካቲት 16- ከልጇ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበለችበት ዕለት፡፡
የካቲት 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡
መጋቢት 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡
መጋቢት 29 ትከብራለች/ጌታችንን የፀነሰበት ጥንተ በዓል፡፡
ሚያዝያ 21 ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡
ግንቦት 1- እመቤታችን የተወለደችበት ዕለት፡፡
ግንቦት 21- በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡
ግንቦት- 22- በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡
ግንቦት- 23- በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡
ግንቦት 24- እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡
ግንቦት 25- ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡
ሰኔ 8- ተወዳጅ ልጇ ከደረቅ ዓለት ላይ ውኃ ያፈለቀበት፡፡
ሰኔ 20- ጌታችን ተገልጦ ሐዋርያቱን ሰብስቦ በስሟ ቤተ ክርስቲያን ሠራላት
ሰኔ 21- ቅዳሴ ቤቷን ያከበረበት ዕለት ነው፡፡
ሐምሌ 21- ትከብራለች/የምትታሰብበት የግዝት በዓል ነው፡፡
4.4K views@azy@, 04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ