Get Mystery Box with random crypto!

#day_3 እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው የእግዚአብሄርን ፊት ማየት የሚቻለው በጽድቅ ነው። ጽድቅ ፊቱን | Tesfa

#day_3
እግዚአብሔር ጻዲቅ ነው የእግዚአብሄርን ፊት ማየት የሚቻለው በጽድቅ ነው። ጽድቅ ፊቱን ታያለች ከጽድቅ ውጪ የእግዚአብሔር ፊት አይታይም፤ የእግዚአብሔር የጽድቁ አካል መሆን አይቻልም። ነገር ግን የእግዚአብሔር ጽድቅ ደግሞ በልጁ በኢየሱስ ነው። “አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤” (ሮሜ 3:21-22)
ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ህግ ማሟላት፣ የእግዘብሔርን ፍላጎት ማሟላት ግድ ይላል፤ ያንን ሊያደርግ የሚችል ደሞ ንጹህ ኃጢአት የማያውቀው ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን ኃጢአተኛ ሳይሆን ኃጢአት ያደረገውን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ መሞት ነበረበት፤ “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።”(2ኛ ቆሮ 5፥21) ስለዚህ ይህንን ይሆን ዘንድ ግን ግዴታ በረት ውስጥ መወለድ ነበረበት። እናም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ ሆነናል። ስለዚህ የእሱ በበረት መወለድ የእኛን የእግዚአብሔር ጽድቅ የመሆናችን የምስራች ማብሰሪያ ቀን ነው።
ደስ ብሎኛል!
#ደስብሎኛል #tesfa


ደስ ያለው ሰው ሼር በማድረግ ይህን የደስታ ምክንያት ለሌሎች እናጋራ!
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube