Get Mystery Box with random crypto!

change your profile with #ደስብሎኛል frame use https://t.me/ad | Tesfa

change your profile with #ደስብሎኛል frame
use https://t.me/add_frame_bot
share with ur friends!

ሰው ለመሆኑ ከዙፋኑ ለመውረድ ምክንያቱ እኔ ነኝ።  እርሱ የሆነውን ሁሉ ማዳኑም፣ ክብሩም፣ ውርደቱም፣ የኖረው ኑሮ ፣የተጎሳቆለው፣  የሰራው ተአምር ፣ ሁሉ ለእኔ ነው። ስለዚህ ልደቱ ልደቴ ነው።  ጊዜ ማይገድበው ነገርግን በተገደበ ቦታ ክብር በሌለበት በበረት ስለተወለደልኝ ልደቱ ልደቴ ነው። ይሄን ሁሉ የሆነው እኔን እያሰበ በእኔ ምክንያት ነበር። እናም ልደቱ ልደቴ የሆነው ስለእኔ የተደረገልኝን በማሰብ ውስጥ ነው።  ልደቱን ከምንም ጋር አላያይዘውም። መድኃኒቴ፣ እረኛዬ ጌታዬ ስጋ የለበሰበት ያ! ጊዜ ለእኔም ልደቴ ነው። ለተቀበሉት በስሙ ላመኑት ለእነርሱ የልጅነት ስልጣን እንደሰጣቸው ሁሉ ዛሬም አንተ በስሙ ብታምን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ስልጣን ይኖርሀል። ልደቱንም በእሩቅ እንደ ባህል ከማክበር ይልቅ የልደቱን ጌታ በማወቅ እና ልደቱ ልደትህ እንደሆነ በመረዳት ትኖራለህ።
ደስ ብሎኛል!

ደስ ያለው ሰው ሼር በማድረግ ይህን የደስታ ምክንያት ለሌሎች እናጋራ!
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube