Get Mystery Box with random crypto!

ደስ ብሎኛል! ልደቱ ልደቴ ነው። #day_2 ሰው ለመሆኑ ከዙፋኑ ለመውረድ ምክንያቱ እኔ ነኝ።  እ | Tesfa

ደስ ብሎኛል! ልደቱ ልደቴ ነው። #day_2
ሰው ለመሆኑ ከዙፋኑ ለመውረድ ምክንያቱ እኔ ነኝ።  እርሱ የሆነውን ሁሉ ማዳኑም፣ ክብሩም፣ ውርደቱም፣ የኖረው ኑሮ ፣የተጎሳቆለው፣  የሰራው ተአምር ፣ ሁሉ ለእኔ ነው። ስለዚህ ልደቱ ልደቴ ነው።   ጊዜ ማይገድበው ነገርግን በተገደበ ቦታ ክብር በሌለበት በበረት ስለተወለደልኝ ልደቱ ልደቴ ነው። ይሄን ሁሉ የሆነው እኔን እያሰበ በእኔ ምክንያት ነበር። እናም ልደቱ ልደቴ የሆነው ስለእኔ የተደረገልኝን በማሰብ ውስጥ ነው።  ልደቱን ከምንም ጋር አላያይዘውም። መድኃኒቴ፣ እረኛዬ ጌታዬ ስጋ የለበሰበት ያ! ጊዜ ለእኔም ልደቴ ነው። ለተቀበሉት በስሙ ላመኑት ለእነርሱ የልጅነት ስልጣን እንደሰጣቸው ሁሉ ዛሬም አንተ በስሙ ብታምን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ስልጣን ይኖርሀል። ልደቱንም በእሩቅ እንደ ባህል ከማክበር ይልቅ የልደቱን ጌታ በማወቅ እና ልደቱ ልደትህ እንደሆነ በመረዳት ትኖራለህ።
ደስ ብሎኛል!
#ደስብሎኛል #tesfa


ደስ ያለው ሰው ሼር በማድረግ ይሀን የደስታ ምክንያት ለሌሎች እናጋራ!
Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | Tiktok | Youtube