2022-04-07 11:17:11
በየዕለቱ ስለምንበላው ጤፍ ያልተነገሩ ጥቅሞች
በርግጥ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ስለጤፍ ማስተዋወቅ ለቀባሪው እንደማርዳት ያህል ይቆጠራል፡፡
ይሁንና አገራችን ለዓለም ካበረከተቻቻው ድንቅ የእህል ዘሮች ውስጥ ስለጤፍ ጠቀሜታ ሳይንስን መሠረት አድርጎ መናገር ደግሞ ሌላ የጥናት መረጃዎችን ዋቤ ማደርግ ይጠይቃል፡፡
ስለሆነም ከታዋቂው organicfacts.net ያገኘነውን 10ሩን አስደናቂ የጤፍ የጤና ጥቅሞችን እናካፍላችሁ፡፡
1. እድገትን ያፋጥናል፡- ለሰውነታች ጠቃሚ የሆኑ 8 አይነት የአሚኖአሲድ የፕሮቲን ንጥረነገሮችን ይዟል፡፡
2. ሴሊያክ የተባለውን በሽታ ይከላከላል፡፡ ግሉቲን ስንዴና በገብስ በመሳሳሉት እህል አይነቶች ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን ሲሆን ይህም ትንሹ አንጀት ለብግነት የሚዳርገውን ሴሊያክ የተሰኘውን በሽታ የሚያባብሱ ሲሆን ጤፍ ግን ከዚህ የፕሮቲን አይነት ነፃ ነው፡፡
3. የአጥምታችንን ጤና ይጠብቃል፡፡ በውስጡ የያዘው በቂ ካልሲየም ለዚህ ደጀን ነው፡፡
4. ጠንካራ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅም እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም ካሉ የያዘው ቫይታሚን ሲ በሽታን በመከላከል ረገድ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማችንን በማጠናክር ረገድ ወሳኝ በመሆኑ ነው፡፡
5. የደም ዝውውርን ይጨምራል፡፡ ብዙዎቻችን አንደምናውቀው ጤፍ በብረት ማዕድን የበለፀገ ነው፡፡ ስለሆነም የደም ማነስ ላለባቸው ሰዎች በተለይ ቀዩ ጤፍ በብዛት እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ የደም ማነስ ያለባቸው ሰዎች መድከም፣ራስ ማዞር፣ የጡንቻ መዛልና የራስ ምታት የሚያጠቃቸው ሲሆን ከችግሩ ለመለቀቀቅ ጤፍ አብዝተው እንዲመገቡ ይመከራል፡፡
6. የደም ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል፡- ኢንሱሊን ቀስ ብሎ ወደ ደም ቧንቧ እንዲፈስ ይረዳል፡፡
7. በወር አባባ ጊዜ ለሚከሰት ሕመምና ችግር መፍትሔ ይሰጣል፡፡ጤፍ በውስጡ ፀረ- ማቃጠል ባህሪያትና የወር አበባን ሕመም የሚያስታግስ ኤጀንትም አለው፡፡
8. የምግብ መፈጨት ጤናማነትን ይጨምራል፡፡ በውስጡ የያዘው ፋይበር የአንጀት እንቅስቃሴን ጥራትን በመጨመር የሆድ መነፋትና ጭብጠትን እንዲሁም ድርቀት ያስወግዳል፡፡
9. በሰወነታችን ውስጥ የኃይል ምርትን ያግዛል፡፡ በውስጡ የያዘው ከፍተኛ መጠን የኮፐር ማዕድን ይህን ተግባር በበቂ ሁኔታ ይወጣል፡፡
10. ጤናማ ልብ እንዲኖረን ይረዳል፡- ዝቅተኛ የሶድየም መጠን ስላላው የደም ግፊት መጠንን በመቀነስ ፣ልብ ድካም እና ስትሮክን በመሳሰሉ በሽታዎች እንዳንጠቃ ይረዳናል፡፡
t.me/teledocc
823 views08:17