Get Mystery Box with random crypto!

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው? የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽ | TeleDoc home based health care service

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ምንድን ነው?

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም ሞንኪፖክስ በተሰኘ ቫይረስ የሚከሰተው በሽታው 'ስሞልፎክስ' ተብሎ የሚጠራው የፈንጣጣ ዝርያ ውስጥ የሚካተት ነው።

ከሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት እና ቫይረሱ ካለባቸው ቁሶች ጋር በሚኖር ንክኪ የሚተላለፈው በሽታው ለምጀመሪያ ጊዜ እንደ አውሮፓውያኑ በ1958 በዝንጀሮ ላይ የተገኘ ነው።

በ1978 ደግሞ በዲሞክራቲክ ኮንንጎ በሰው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱ ተረጋግጧል። በገጠራማ የማዕከላዊ እና ምዕራባዊ አፍሪካ አገራት በፋት የሚያጠቃው የዝንጀሮ ፈንጣጣ እጅግ አሳሳቢ የሚባል አይደለም። በሽታውን 85 በመቶ መከላከል እንደሚችል የተረጋገጠ ክትባትም አለው።

አንዳንድ ጊዜ ያለምንም ህክምና በራሱ ጊዜ ሊጠፋ የሚችል ነው ። ሆኖም በምዕራብ አፍሪካ በበሽታው ምክንያት ህይወት አልፏል።

የበሽታው የሞት ምጣኔ ከ3 እስከ 6 በመቶ እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጀት ይፋ ያደረገው መረጃ ያመለክታል።

ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የሰውነት እብጠት፣ የጀርባ እና የጡንቻ ህመም ደግሞ የበሽታው ምልክቶች ናቸው። t.me/teledocc