Get Mystery Box with random crypto!

#ተቀብሎናል!! በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁ ሁላችሁ ... እግዚአብሔር ተቀብሏችኋል!! የምስራች . | Tebazu Bekele Official

#ተቀብሎናል!!

በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁ ሁላችሁ ... እግዚአብሔር ተቀብሏችኋል!! የምስራች ...በፊቱ ሞገስ አግኝተናል!! በልጅነት ማዕረግ ተቀብሎናል!! ከክብር ጋር ተቀብሎናል!! ቅዱሳን ልጆቹ ሆይ ደስ እያላችሁ በፍቅሩ ተራመዱ!!

በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት አሁን የምንሠራው ሥራ የለም!! በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ተቀባይነት አግኝተናል!! ተቀብሎን ... በእርሱ ውስጥ እየኖርን ነው፤ ከክርስቶስ ውጭ አይደለንም!! ተቀብለነው ... በእኛ ውስጥ እየኖረ ነው!!

በአሮጌው ኪዳን ...ሊቀ ካህናቱ ስለሕዝቡ ስለራሱም ኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል። እርሱና መስዋዕቱ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ካገኘ ሕዝቡም ተቀባይነት ያገኛሉ!! እርሱን ባይቀበለው ወይም በሞት ቢቀጣ ለሕዝቡ የመከራ ዓመት ይሆናል። የሕዝቡ ተቀባይነት የተወሰነው በእነርሱ ሥራ ሳይሆን በሊቀካህናቱ ሁኔታ ነው!! (ዕብራውያን 5፥3፤ 9፥25)። ይህ ተቀባይነት እስከ ቀጣዩ የስርየት ቀን ለአንድ ዓመት ብቻ የሚቆይ ነው!!

የኛ ሊቀካህናት ኢየሱስ ድካም የለበትም፤ መስዋዕቱም (ራሱ) ነውር የለበትም። እርሱም መስዋዕቱም ለዘላለም ተቀባይነት አግኝቷል!! በእርሱ እኛም ተቀባይነት አግኝተናል!! በኢየሱስ ሥራ ስለመጣን አብ ያለ ፀፀት ተቀብሎናል!! የተቀበለን ልጁን አይቶ ነው!!

ራሳችንን መጠየቅ ያለብን፦ እግዚአብሔር የልጁን የኢየሱስን ሥራ ተቀብሎታል? ኢየሱስ ላንተ እንደሠራ ተቀብለሃል? ኢየሱስ ላንቺ እንደሠራ ተቀብለሻል? መልሳችን አዎን እና አሜን ከሆነ ኢየሱስን ስንቀበል እግዚአብሔር ተቀብሎናል!!

በፊቱ ለመቆም ድፍረት የሚሰጠንን ሥራ በክርስቶስ ሠርቷል!! በዚህ ሥራ ያለ ነቀፋ ያለ ኩነኔ በፊት መኖር ተሰጥቶናል!! የኛ ሥራ በፊቱ ሕያው መሆን አልቻለም ነበር። ለዚያ ነው እንዲቀበለን የሚያደርገውን ሥራ በልጁ የሠራው!! የተወደዳችሁ ልጆቹ ሆይ #የሠራችሁትን ሳይሆን #የተሠራላችሁን ተመልከቱ!!

❝እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።❞ —1ኛ ጴጥሮስ 2፥10።

ከመቀበል አልፎ የእግዚአብሔር ወገን ሆነናል!! ምሕረት አግኝተናል!! ኢየሱስ መስቀል ላይ እያለ ..ለምን ተውከኝ? ማለቱ ትዝ አላችሁ? እርሱን ሲተወዉ እኛ ተቀባይነት አገኘን፤ ከእርሱ ፊቱን ሲያዞር ...ዞሮ ያዬው እኛን ነው!! የያሕዌ ዓይኖች በእኛ ላይ ናቸው!! ኢየሱስ የተተወዉ በእኛ ስፍራ ሆኖ ነው፤ እኛም የተገኘነው በእርሱ ሆነን ነው!! ኢየሱስ ትኩረት የሚሰጠው አጥቶ ነበረ፥ ትውልድ ፊቱን አዙሮበታል፥ እግዚአብሔር ትቶታል!! ሰማይ ምድሩ ለእኛ ትኩረት የሰጠዉ፥ ተቀባይነት ያገኘነው በዚህ ምክንያት ነው!!

@tebazushows
@tebazushows