Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል=አንድ ጽድቅ_ምንድነው? (መግቢያ) 'ጽድቅ' የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ግሪክ 'ዲካይሱኔ' | Tebazu Bekele Official

ክፍል=አንድ
ጽድቅ_ምንድነው? (መግቢያ)

"ጽድቅ" የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ግሪክ "ዲካይሱኔ" የሚባል ሲሆን ቃሉ "ዲኬ" ከሚለው ስርወ-ቃል (Root Word) የመጣ ነው። "ዲኬ" ማለት "ትክክል" (Right) ማለት ነው። እንዲሁም በዕብራይስጥ "ጸዴቅ" የሚል ሲሆን ትርጉሙ "ትክክል፣ ንጹሕ" ማለት ነው። እንግዲህ በቃሉ ትርጉም መሰረት አንድ ሰው ጸደቀ ማለት "ትክክል" ወይም "በደል-የለሽ" ሆነ ማለት ነው።

ሮሜ 3(አዲሱ መ.ት)
²¹ አሁን ግን ሕግና ነቢያት የመሰከሩለት፣ ከሕግ ውጭ የሆነ፣ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦአል።
²² ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው። ልዩነት የለም፤

ጽድቅ ማለት በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ መሆን ማለት ነው። (Righteousness is right standing with God.)

በሕግ እና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ የተገለጠ የእግዚአብሔር ማንነት ነው።
ጽድቅ የእግዚአብሔር ብቸኛው ማንነት ሲሆን በሰው ስራ እና ጥረት የማይገኝ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ነው።

የእግዚአብሔር ጽድቅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ መቀበል የሚቻለው በእምነት ብቻ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ነው።

የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በሙሴ ሕግ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገለጥ እምነት ነው።

የእግዚአብሔር ጽድቅ በሀይማኖታዊ ስርዓት ኖረን የምንቀበለው ሽልማት ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ባለው እምነት የሚገኝ ነው።

እውነተኛ የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኝ መሆኑን በግልጽ ይናገራል።

Tebazu Bekele Official
Join
https://t.me/tebazushows
https://t.me/tebazushows