Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላቹ ከመሞትክ በፊት ቀድመክ አትሙት በድሮ ጊዜ ሁለት | Tebazu Bekele Official

ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዴት ዋላቹ

ከመሞትክ በፊት ቀድመክ አትሙት

በድሮ ጊዜ ሁለት አገልጋዮች ትልቅ ጥፋትን ያጠፉና ለፍርድ በንጉሱ ፊት ይቀርባሉ፡፡ ንጉሱም የጥፋታቸውን ከባድነት ከተረዳ በኀላ ሁለቱም በሞት እንዲቀጡ ይወስንባቸዋል፡፡ ለመሞትም ሁለቱም መርዝ እንዲጠጡ ያዛል፡፡ እናም ለሁለቱም በዋንጫ ተቀድቶ ይሰጣቸውና ግጥም አድርገው ይጠጡታል፡፡

ከሰከንዶች በኀላ አንደኛው አገልጋይ እዛው ተንፈራፍሮ ይሞታል፡፡ አንደኛው ግን ምንም ሳይሆን ይቀራል፡፡ ለካ ንጉሱ ምንም እንኳን አገልጋዮቹ ከባድ ጥፋት ቢያጠፉም በሞት ሊቀጣቸው አላሰበም ነበር፡፡ ይልቁንም ምን ያህል መንፈሰ ጠንካራ መሆናቸውን ለመፈተን ሲል ሁለቱንም መርዝ ጠጥታችሁ ትሞታላችሁ በማለት ንፁ ወይን በዋንጫ እንደሰጣቸውና እንዲጠጡ ነበር ያደረገው፡፡

ነገር ግን ምንም እንኳን የጠጡት ንፁ ወይን ቢሆንም አንደኛው አገልጋይ ገና መርዝ ጠጥቶ እንደሚሞት ሲነገረው ልቡ እና መንፈሱ ቀድሞ በመሞቱ ምንም መርዝ በሌለበት ወይን ጠጥቶ ሞቷል፡፡

ወደ እኛ ህይወትም ስንመጣ ተመሳሳይ ነው፡፡ ብዙዎቻችን በየቀኑ በሚገጥሙን ጥቃቅን ውጣውረዶች የተነሳ ምንም የሚገድል ነገር በሌለበት ቀድመን እንሞታለን፡፡ ችግሮቻችን የቱንም ያህል የገዘፉ ቢሆንም የፈጠረን እና የማይተወን አምላክ ክንዶች ደሞ ከችግሮቻችን ሺ እጥፍ የበረቱና የገዘፉ መሆናቸውን እናስብ፡፡

መልካም አዳር
@biblicaldoctrine
@biblicaldoctrine
@biblicaldoctrine