Get Mystery Box with random crypto!

ጥበብ በእርስው

የቴሌግራም ቻናል አርማ tebabbeafetary — ጥበብ በእርስው
የቴሌግራም ቻናል አርማ tebabbeafetary — ጥበብ በእርስው
የሰርጥ አድራሻ: @tebabbeafetary
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 165

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-19 20:51:00 ዮሐንስ የተመኛት ጥምቀት ልጅነትን የምታስገኘዋን በክርስቶስ አምነን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የምንጠመቃትን የክርስትና ጥምቀት ነበር፡፡ የእርሱ ጥምቀት የማያጸዳው የሰው ልጅ መርገም አለና እርሱን ሊታጠብ ሽቶ መጠመቅ ፈለገ፡፡ አፈወርቅ ‘ልጠመቅ ያስፈልገኛል’  የሚለውን ንግግር ሲያብራራ እንዲህ ማለቱ ነው ብሏል ፦   ‘ጌታ ሆይ ለዓለም ሁሉ የምትሠጠውን ጥምቀትህን ሥጠኝ፡፡ በሰው ሁሉ ላይ ያለውን የመርገም ሸክም ተሸክሜያለሁና  ፣ በዕባቡም መርዝ ተመርዤአለሁና እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል’’  

መጥምቁ ዮሐንስ የተመኛትን ጥምቀት ተጠምቆ ይሆን? ከተጠመቀስ መቼ በማን ተጠመቀ? በሚለው ላይ አንድ በቃኝ መልስ መሥጠት ቢከብድም በዚህም አለ በዚህ ዮሐንስ ጥምቀትን ተመኝቷት እንዳልቀረ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ብዙ ሊቃውንትና ቅዱሳን የዮሐንስ ጥምቀት የትኛው ነው በሚለው ላይ የተለያዩ ሃሳቦች አስቀምጠዋል፡፡

  የመጀመሪያው የቅዱስ ያሬድ ዝማሬ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ስለ ዮሐንስ ጥምቀት ሲናገር ‘አጥመቀ ወተጠመቀ ለሊከ’’ ይላል ፤ ‘አጠመቅህ አንተም ተጠመቅህ’ ማለት ነው፡፡ በሌላ ሥፍራ ደግሞ ‘አጥመቆ ዮሐንስ ለኢየሱስ በፈለገ ዮርዳኖስ እምድኅረ አጥመቀ ለሊሁ ተጠምቀ’ ‘ዮሐንስ ኢየሱስን በዮርዳኖስ ወንዝ አጠመቀው ካጠመቀ በኋላም እርሱም ተጠመቀ’’ ብሏል፡፡ በአጭሩ ቅዱስ ያሬድ የመጥምቁ ዮሐንስ የጥምቀት ቀን ጌታን ያጠመቀበት ቀን ነው ባይ ነው፡፡
 
በእውነትም ልብ ብለን ስናየው ለዮሐንስ ጥምቀት ከዚያች ቀን የተሻለ ቀን የሚመጣ አይመስልም፡፡ ያለበት ውኃ በጌታ በራሱ የተቀደሰው የዮርዳኖስ ወንዝ ነው፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‘‘ተቀደሰት ማይ በጥምቀቱ’’ /ውኃ በጥምቀቱ ተቀደሰች/ ብሎ የዘመረው ስለ ዮርዳኖስ ነበር ፤ በጌታና በዮሐንስ መካከል የነበረውን የአጥምቀኝ ውይይት በዘመረበት ሥፍራም ‘ዮሐንስም ኢየሱስን እንደምን አንተን ማጥመቅ እችላለሁ? ጌታ ሆይ ውኃ ይሸከምሃልን? አለው፡፡ ኢየሱስም ለዮሐንስ እኔ ካልጠመቅሁ ውኃ አትቀደስም አለው’’ /‘ወይቤሎ ዮሐንስ ለኢየሱስ እፎኑ እክል አጥምቆትከ ዓይኑ ማይ እግዚኦ ይፀውረከ  ፤ ይቤሎ ኢየሱስ ለዮሐንስ ኢትትቀደስ ማይ ለእመ ኢተጠመቁ አነ’’/ ብሎአል፡፡  

በጌታ መጠመቅ ከተቀደሰችው ከዚህች ቅድስት ውኃ በቀር ለዮሐንስ ጥምቀት ምን የተሻለ ውኃ ሊመጣ ነው? ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እንኳን የመንገድ ዳር ውኃ አይቶ ‘እነሆ ውኃ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ማን ነው?’’ ካለ መጥምቁ ዮርዳኖስ መካከል ሆኖ እንዳይጠመቅ የሚከለክለው ምንድር ነው? ከውኃውም አልፎ ሊቀ ካህናት ክርስቶስ አብሮት በባሕር መካከል ቆሞ  ፣ አብ በደመና ድምፁን አሰምቶት ፣ መንፈስ ቅዱስ በርግ አምሳል ወርዶ ታይቶት ከዚህ የተሻለ ቀን ለዮሐንስ ጥምቀት ከየት ሊመጣ ነው? ስለዚህ ‘አጠመቅህ አንተም ተጠመቅህ’ የሚለው የቅዱስ ያሬድ ዝማሬ ስለ ዮሐንስ ጥምቀት እጅግ ትርጉም ያለው ምላሽ ነው፡፡ 
 
የዮሐንስን በዮርዳኖስ መጠመቅ የበረከት እንጂ የልጅነት ጥምቀት አይደለም ፤ የልጅነት ጥምቀት ገና አልተሠጠችም የሚሉ ሊቃውንትም አሉ፡፡ በእናቱ ማኅፀን ሳለ ተጠምቋል ፤ ገብርኤልም ‘’በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል’ ብሎአል ብለው ዮሐንስን በማኅፀን ተጠመቀ የሚሉ አሉ፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ ግን ዮሐንስ ‘ልጠመቅ ያስፈልገኛል’ ብሎ አለመጠመቁን ስለተናገረ በማኅፀን የልጅነትን ጥምቀት አለማግኘቱ ግልጽ ነው፡፡ ሌላው በሊቃውንት ዮሐንስ ተጠመቀ የሚባልበት ክስተት በሰማዕትነት መሞቱ ነው፡፡ እርሱ በክርስቶስ አምኖ እና ስለ ክርስቶስ ዞሮ አስተምሮ ተጋድሎ በግፍ ሰማዕት የሆነ ነው፡፡ በክርስቶስ አምነው ሳይጠመቁ የሚሞቱ ደግሞ በውኃ ሳይሆን በደም ጥምቀት ተጠምቀዋል፡፡ ይህንንም የዮሐንስ ጥምቀት ነው የሚሉት አሉ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ጥምቀትን አላገኛትም የሚል ቢኖር ግን ሠላሳ ሦስት ዓመታትን በምድር የነበረው ክርስቶስ ወደ ሲኦል ወርዶ ለሠላሳ ሦስት ሰዓታት ለነፍሳት ነጻነትን በሰበከበት ዕለት ‘ወመጠውኩዎሙ ዕዴየ ዘየማን ወኮነቶሙ ጥምቀተ’ /የቀኝ እጄን ሠጠኋቸው ጥምቀትም ሆነቻቸው/ የተባለላት ጥምቀት መጥምቁን ልታልፈው አትችልም፡፡ እንግዲህ ከእነዚህ በአንዱ የመጥምቁ ዮሐንስ ‘በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል’ የሚል ምኞቱ ተሳክቷል፡፡    
 
ይህ ትሑት አጥማቂ ክብሩ እንዴት ከፍ ያለ ነው? ቅዱስ ያሬድ ‘ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ዘመላእክት ይስግዱ ሎቱ’’ እንዳለ  ቅዱሳን መላእክት ሳይቀሩ ለክብሩ የሚሰግዱለት ፤ የሙሽራው ክርስቶስ ሚዜ ፣ ለፀሐይ ክርስቶስ ጨረቃው ፣ ለንጉሥ ክርስቶስ አዋጅ ነጋሪው ፣ ለቃል ክርስቶስ ድምፁ ፣ ጌታ በምድር ከመስበኩ በፊት ቀድሞት የሰበከ መንገድ ጠራጊው ፣ በሲኦል ላሉ ነፍሳትም ቀድሞ ከጌታ መምጣት በፊት ያወጀ የሰማይ መንገድ ጠራጊው ፣ ክርስቶስ ሞቱን ሲሰማ በምድረ በዳ ብቻውን ያዘነለት ወዳጁ ፣ ድርሳነ አማኑኤል እንደሚል ከሞተ በኋላ በኖረባት ምድረ በዳ ተዝካሩን ዓሣና እንጀራ አበርክቶ ያወጣለት የቅርብ ዘመዱ ፣ ገብርኤል አስቀድሞ ሳይወለድ የዘመረለት ታላቅ ነቢይ ፣ የአባቱን የተዘጋ ልሳን ከተዘጋ ማኅፀን ተወልዶ የከፈተ ድምፅ ፣የጌታን መወለድ ስናስብ ወላዲተ አምላክ የተባለች የድንግልን መውለድ እንደምናደንቅ የጌታን መጠመቅ ስናስብ የሱን ማጥመቅ የምናደንቅለት መጥምቀ መለኮት እጅግ ታላቅ ነው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥምቀት 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ
52 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 20:51:00 ፍኖተ ሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ መራሔ ጽድቅ ሰንበት ት/ቤት:
+ መጥምቁ ዮሐንስን ማን አጠመቀው? +

ታላቁ ነቢይ ካህን ሐዋርያና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የጌታ ጥምቀት በዓል በደረሰ ቁጥር የሚታሰብ የጥምቀቱ ዋነኛ ተሳታፊ ነው፡፡ የጌታን መጠመቅ ስናስብ ሁሌም በተፈጸሙት ታላላቅ ድንቅ ነገሮች ተማርከን የምንዘነጋው ርእሰ ጉዳይ ቢኖር የአጥማቂውን መጠመቅ ጉዳይ  ነው፡፡

የሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ልጅ እንደመሆኑ በሊቀ ካህናትነት የማገልገል ሙሉ መብት ቢኖረውም ወደ ሰሎሞን መቅደስ በመሔድ ፈንታ ወደ በረሃ የመነነው ይህ ባሕታዊ አገልግሎቱን የጀመረው  "ንስሓ ግቡ" ብሎ እንደ ምድረ በዳ የደረቀ ልብ ባላቸው አይሁድ መካከል ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ጌታችን ሊጠመቅ ወደ እርሱ መጣ፡፡

ዮሐንስ ክርስቶስን ያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ አልነበረም፡፡ ከሠላሳ ዓተታት በፊት ሁለቱም በእናቶቻቸው ሆድ ውስጥ ሆነው ተገናኝተዋል፡፡ ‘’በእናትህ ሆድ ሳለህ አውቄሃለሁ’’ ብሎ የተናገረውን ፈጣሪውን እኔም ‘’በእናትህ ሆድ ሳለህ አውቄሃለሁ’’ ብሎ ማነጋገር የሚችል ከመጥምቁ ዮሐንስ በቀር ማን አለ? ‘ከማኅፀን ጀምሮ ባንተ ታመንሁ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ‘’ ብሎ የዳዊትን መዝሙር ለመዘመር የሚችል እንደ መጥምቁ ያለ ማን አለ? ቅዱስ ያሬድ ‘እምከርሠ እሙ አእመረ ሰገደ ወአንፈራዓፀ’’ ‘በእናቱ ማኅፀን አወቀ ሰገደ ዘለለም’ ብሎ በድጓው የዘመረለት ዮሐንስ ለጌታው ለመስገድ ከእናቱ ማኅፀን እስኪወጣም አልታገሠም፡፡ ጉልበቱ ሳይጸና መስገድ የጀመረ ፣ በዓይኑ ማየት ሳይፈልግ አምልኮ የጀመረ ከዮሐንስ በቀር ማንም የለም፡፡

አሁን በእናቱ ማኅፀን ያገኘውን ጌታ ሁላችንን ወደምትወልደው ወደ ማኅፀነ ዮርዳኖስ  ሲመጣ አየው፡፡ ዮሐንስና ጌታ ከሠላሳ ዓመት በፊት ተገናኝተዋል ግን አልተያዩም ነበር ፣ መልእክት ተለዋውጠዋል ነገር ግን አልተነጋገሩም፡፡ ለዚህ ነው ዮሐንስ ስለ ጌታ ‘’አላውቀውም ነበር‘’ ያለው፡፡ /ዮሐ 1፡31/ አሁን ግን  ጌታውን አየው፡፡ ወደ እርሱ ሊጠመቅ መምጣቱን ተመለከተ፡፡

ወደ ዮሐንስ ሊጠመቁ የሚመጡ ሁሉ ኃጢአት ያለባቸው ስርየትንና በውኃው መንጻትን የሚፈልጉ ናቸው፡፡ አሁን ግን  ሊጠመቅ የመጣው ጌታ ንጹሐ ባሕርይ ነው፡፡  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው ‘ክርስቶስ ከራስዋ ከጥምቀት የበለጠ ንጹሕ ነው‘’ የእርሱ መምጣት ዮሐንስን የሚያስደንቅ ነበር፡፡ ዮሐንስ እንዲህ ሲል አሰበ ይላል ሊቁ ፦

‘’ጌታ ሆይ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ አንተ ‘’ክፋትን አላደረገም ፤ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም‘’ ብሎ ሳለ [ኃጢአተኞች ተጠምቀው ወደሚነጹባት] ወደ እኔ ጥምቀት ስለምን መጣህ? ሁሉን የምታነጻ ሆይ መንጻትን ትሻለህን? በልማድ በእኔ ዘንድ የሚጠመቁ ሁሉ ኃጢአታቸውን ይናዘዛሉ፡፡ አንዳች በደል የሌለብህ ሆይ አንተ ምን ብለህ ትናዘዛለህ?’’

ዮሐንስ የጌታን ሊጠመቅ መምጣት አይተው እንደ ኃጢአተኛ እንዳይቆጥሩበት ፈርቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል ጮኸ፦

‘የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ!’’ አለ፡፡ ወደ እኔ ጥምቀት ሲመጣ እርሱ በደል ያለበት እንዳይመስላችሁ! እርሱ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ነው ብሎ በሕዝቡ ፊት መሰከረ፡፡ ይህ አዋጅ በዙሪያው ካሉት በላይ ለሁላችን የሚሠዋውን በግ ተስፋ ላደረግን ለሁላችን ታላቅ ብሥራት ነበር፡፡ አባቱን ‘የመሥዋዕቱ በግ ወዴት አለ?’’ እያለ በጥያቄ ሲያስጨንቅ እንደነበረው እንደ ይስሐቅ በጉን ልናይ ለናፈቅን ለሁላችን ደስ የተሰኘንበት መልስ ይህ የመጥምቁ ዮሐንስ ‘የእግዚአብሔር በግ እነሆ’ የሚል አዋጅ  ነበር፡፡  

ጌታችን ሊጠመቅ ወደ ዮሐንስ ሲመጣ ዮሐንስ ተጨነቀ፡፡ እናቱ ለድንግል ማርያም አንቺ እንዴት ወደ እኔ ትመጫለሽ? እንዳለች እርሱም ለጌታው እንዴት ልትጠመቅ ወደ እኔ መጣህ? አለ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‘ወገሠሦ እንተ ኢትትገሠሥ ርእሶ’ /የማትዳሰስ ራሱን ዳሰሰው/ እንዲል ጫማውን ተጎንብሼ ልፈታና ልሸከም አይገባኝም ብሎ ሲሰብክለት የቆየው ጌታ እጅህን ከራሴ በላይ ከፍ አድርገህ አጥምቀኝ ሲለው ትሑቱ ዮሐንስ እጅግ ተጨነቀ፡፡

  ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል ‘ዮሐንስን በመደነቅ ተሞልቶ አየሁት ፤ በዙሪያው ያሉትም እንዲሁ፡፡ የከበረው ሙሽራ በመካኒቱ ልጅ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ አጎነበሰ፡፡ የሁሉ አጥማቂ ሊጠመቅ መጣ’’ ዮሐንስ ለጌታው አጥምቀኝ የሚል ጥያቄ እንዲህ ሲል በጭንቀት መለሰ ፦ ‘‘እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል ፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን ብሎ ይከለክለው ነበር?/ማቴ 3፡14/

  ቅዱስ ያሬድ  ጌታ በባሪያው መሪነት ወደ ባሕር መውረዱን ያደንቃል ፤ ‘‘ሰማያዊው በመሬታዊው እጅ ተጠመቀ’’ /መሬታዊ አጥመቆ ለሰማያዊ/ እያለም ሰውን ከአፈር ያበጀው ፈጣሪ በፈጠረው አፈር እጅ ሊጠመቅ ማጎንበሱን ያደንቃል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደግሞ ስለ አምላክ መገለጥ በሰበከው ስብከት /Homily on the Theophany/  ጌታ በባሪያው እጅ ሊጠመቅ በወደደ ጊዜ የተፈጠረውን ክስተት እንዲህ ይተርከዋል ፦

‘‘ጌታ በባሪያው ፊት ቆሟል፡፡ በወታደሩ ፊት የሚያጎነብስን ንጉሥ አይቶ የሚያውቅ ማን ነው? እረኛስ በጉን መንገድ ምራኝ እያለ ሲጠይቅ የተመለከተ ሰው ማን ነው?  
ዮሐንስ እንዲህ አለ ፦ የማደርገው ግራ ገብቶኛል በቀን ብርሃን ላይ የብርሃን ጭረሮችን ማብራት እንዴት ይቻላል?  
የጠራ ወርቅን እንዴት በጭቃ አጥቦ ማጥራት ይቻላል? ባሕር በምንጭ ላይ ይችላልን? ወንዝስ በውኃ ጠብታ ይሞላልን? ንጽሕና ራሱ በአዳፋው እጅ እንዴት ይታጠባል? ዳኛው በተፈረደበት ሰው እጅ ነጻነትን ይቀበል ዘንድ የተለመደ አይደለም፡፡ ‘እኔ በአንተ ልጠመቅ ይገባኛል!’’
የሞተው ሕያዉን ሊያስነሣ ይችላልን? የታመመውስ ሐኪሙን ሊፈውስ ይችላልን? የባሕርዬን መጎስቆል አውቀዋለሁ፡፡ ደቀመዝሙር ከመምህሩ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም፡፡ /ማቴ 10/ ኪሩቤል ወደ እኔ የሚቀርቡት በፍርሃት አይደለም ፣ ሱራፌልም ለእኔ ቅዱስ ቅዱስ ብለው አይዘምሩም ፣ ሰማይ ዙፋኔ አይደለም ፣ ኮከብም ልደቴን ለጥበብ ሰዎች አላሳየም ፣ ከደመናም ስለእኔ የሚጮህ ድምፅ የለም፡፡ ወዳጅህ ሙሴ እንኳን ጀርባህን ያያል ተብሎ ነበር፡፡  እጅግ ንጹሕ የሆነውን የራስህን አክሊል እነካ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል? ከእኔ ኃይል በላይ የሆነን ነገር ስለምን ትጠይቀኛለህ?  ፈጣሪዬን ለማጥመቅ የምችልበት እጅ የለኝም ይልቅስ ‘እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል’ ያም ሆነ ይህ ጌታ ፈቅዷልና ‘’ጽድቅን እንፈጽም ዘንድ ይገባናል’’ ብሎ የጽድቅ /ሕገ ኦሪት/ ፍጻሜ የሆነችውን የዮሐንስን ጥምቀት ሊጠመቅ ፈቀደ፡፡

ወደ ተነሣንበት ነገር ስንመለስ ዮሐንስ ጌታ አጥምቀኝ ሲለው ‘እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል’ ብሎ ጥምቀት እንደሚያስፈልገው ተናግሮ ነበር ፡፡ ይህ ቃል ምንኛ ድንቅ ነው? መጠመቅ የሚፈልግ አጥማቂ እንዴት ያለ ነው? ሌሎች በእርሱ ለመጠመቅና ለመንጻት ተሰልፈው ሳለ እርሱ ‘መጠመቅ ያስፈልገኛል’ እያለ ሌላ ጥምቀት የሚመኝ አጥማቂ እንደምን ያለ ነው? ወደ እርሱ ሊጠመቅ የመጣን ተጠማቂ አጥምቀኝ እያለ የሚማጸን አጥማቂ ማን  አይቶ ያውቃል? አዎ ዮሐንስ ግን አድርጎታል፡፡
49 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 20:48:33
44 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-06 20:39:43 + ጌታ የተወለደው የት ነው? +

የገና ዋዜማ የት ልትሔድ አሰብህ? ምሽቱንስ የት ልታሳልፍ ነው? የትኛው ሆቴል? የትኛው የሙዚቃ ድግስ? "የገናን በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ ልዩ የሙዚቃ ድግስ" ላይ ጌታ የለም:: ባለ ልደቱ ጌታ የት ነው ያለው? አድራሻው ከጠፋብህ የተወለደ ዕለት የሆነውን ልንገርህ!

የተወለደውን ክርስቶስ ለማየት ብዙ ሀገራትን አልፈው ተጉዘው የመጡት ሰብአ ሰገል በኮከብ ተመርተው ነበር::
ለእስራኤላውያን እረኞች በታሪካቸው ውስጥ በሚያውቁአቸውና በለመዱአቸው መላእክት ልደቱን የገለጠው አምላክ ኮከብ ሲቆጥሩና ሲጠነቁሉ ለኖሩት ሰብአ ሰገል ደግሞ በሚያውቁት ኮከብ መራቸው::
ሕጻኑ ክርስቶስ ገና ከመወለዱ ብዙ እንደ ጣዖት የሚመለኩ ነገሮችን ድል አድራጊ መሆኑን አሳየ::

በሲና በረሃ እስራኤል ጥጃን አምላክ ብለው በወርቅ ጣዖት ሠርተው ነበር:: በቤተልሔም ጥጃ  ትንፋሹን ለክርስቶስ በመገበር አምላኬ እርሱ ነው ሲል መሰከረለት:: በሬም ገዢውን አወቀ ሕዝቤ ግን አላወቀኝም የሚለው ተፈጸመ:: ከዋክብትንና ፀሐይን ያመልኩ የነበሩን የዞረዳሸት (ዞራስትራኒዝም) ፍልስፍናን የሚያምኑ ሰብአ ሰገልም በሚያመልኩት ኮከብ ፈጣሪያቸውን አገኙ:: ቅዱስ ኤፍሬም እንዳለው "የሚያመልኳት ፀሐይም በሰብአ ሰገል ጉልበት ለፈጣሪዋ ሰገደች"

ኮከብ የሚወጣበት ጊዜ በዚያን ቀን የሰውን ዕጣ ፈንታ ይወስናል ብለው የሚያምኑም ብዙዎች ናቸው:: ይህ የሆነው በኮከቤ ምክንያት ነው! ኮከባችን አይገጥምም የሚባባሉ ብዙዎች ናቸው:: ይህ ሁሉ ባዕድ አምልኮ ነው::  ኤሳውና ያዕቆብ መንትዮች ናቸው:: የተወለዱት በአንድ ቀን ነው:: እነርሱ በተወለዱ ቀን የወጣው ኮከብም አንድ ነው:: "ኮከባቸው" አንድ ሆኖ ሳለ ምነው ነገራቸው ሁሉ አልገጥም አለ? ኮከባቸው ይገጥማል ምነው እነርሱ አልገጠሙም? ስለዚህ ሐሰት ነው::

የተወለደው ንጉሥ ግን ኮከቡ ዕጣ ፈንታውን የሚወስነው ሳይሆን ከዋክብትን በየስማቸው የሚጠራቸው በቁጥር የሚያውቃቸው ጌታ ነው:: እንደ ዮሴፍ 11 ከዋክብት ሐዋርያቱ ከይሁዳ በቀር የሰገዱለት እናቱ ማርያምም እንደ ያዕቆብ በልብዋ እያሰበች የተደነቀችበት የከዋክብት ጌታ የጨረቃ ንጉሥ የፀሐዮች ሁሉ ፀሐይ ነው እርሱ::

ሰብአ ሰገል መሪያቸው የነበረውን ኮከብ ሲያጡት ወደ ሔሮድስ መጡና "የተወለደው ንጉሥ ወዴት ነው?" አሉ::
እውነትም ጠቢባን ናቸው:: መንገድ ከጠፋብን : መሪ ኮከብ ካጣን ልደቱን የፈለግንበት እናክብር አላሉም:: የተወለደው ወዴት ነው? ብለው ቤተ መንግሥት ሔደው ጠየቁ:: ጥሩ በዓል ለማክበር ከቤተ መንግሥት የተሻለ ሥፍራ የለም:: በቤተ መንግሥት ራት እየበሉ ጮማ እየቆረጡ በዘፈን ታጅበው በዓሉን ማክበር ይችላሉ:: እነርሱ ግን የትም ቢሆን ንጉሡን ሳናገኝ አንቆይም:: እሱ የሌለበት ቦታ ቤተ መንግሥትም ቢሆን ልደቱን አናከብርም:: አይ ሰብአ ሰገል! ይህንን ዘመን መጥተው ቢያዩ ምን ይላሉ?

ወዳጄ አንተ የጌታን ልደት የት ታከብራለህ? መቼም
ልደት የሚከበረው ባለ ልደቱ ባለበት ሥፍራ ነው:: በእውነት የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በጭፈራ ቤት ነውን? በመጠጥ ቤት ነውን? የት ነው ያለው ብለህ ጠይቀሃል?

"የሚመራኝ ኮከብ የለም" ትል ይሆናል:: ምንም ቢሆን ግን ሕፃኑ በሌለበት ልደቱን ለማክበር መወሰን የለብህም:: ምንም ያሸበረቁ ሥፍራዎች ቢኖሩም እንዳትታለል:: የሔሮድስ ቤተመንግሥት ውበት የግብዣው ስፋት አታልሎህ የተወለደውን ንጉሥ እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ:: እሱ ከሌለበት ያማረ ሥፍራ ይልቅ እሱ ያለበት በረት ይሻልሃል:: እሱ ያልመረጠውን ሥፍራ መርጠህ ከመንገድ አትቅር:: "የተወለደው የአይሁድ ወዴት ነው" ብለህ ጠይቅ::

እሱ ደሃ ሆኖ ባለጠጋ የሚያደርግህን ንጉሥ በሚያልፍ ደስታ አትጣው:: በስካር በዝሙት በጭፈራ በሔሮድስ ቤተ መንግሥት ቀልጠህ ቀርተህ የተወለደውን ሕፃን ሳታየው አትቅር:: እሱ በተወለደባት ሌሊት አንተ ስትሞት አትደር:: እመነኝ የተወለደው ይሻልሃል ከሞቱት ጋር ጊዜህን አታጥፋ::

ሰብአ ሰገል "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?" ብለው ለአይሁድ ንጉሥ ሔሮድስ ጠየቁት:: የአህያ ውኃ ጠጪው ሔሮድስ ክው ብሎ ቢደነግጥም ፈገግ ብሎ ላጣራላችሁ ቆይ ብሎ አቆያቸው:: መጽሐፍ አዋቂዎቹን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠሩ:: እነ ሊቄ መለሱ:: "እንደተነገረው ትንቢት ከሆነማ" አሉ ኩፍፍፍስ ብለው
"በይሁዳ ቤተልሔም ነው" ብለው የተወለደውን ንጉሥ አድራሻ ተናገሩ:: ሔሮድስ ከነተንኮሉ ለሰብአ ሰገል መልእክቱን አደረሰ:: ሰብአ ሰገልም ሔደው ለንጉሡ ሰግደው እጅ መንሻ አቀረቡ::

ሔሮድስን ትተን እስቲ የጸሐፍቱን ነገር ትንሽ እናስተውለው:: የተወለደውን ጌታ አድራሻ ጠቁመው ለሰብአ ሰገል መንገድ የመሩ እነርሱ ግን መንገድና እውነት ሕይወትም የሆነው ጌታ የተሰወረባቸውን የታወሩ መሪዎች   በሽተኛ ሐኪሞች የተራቡ መጋቢዎችን እስቲ ልብ እንበላቸው:: "ጥሩምባ ነፊ ቀብር አይገኝም" ማለትስ አይሁድ ናቸው::

ሌላውን ወደ ጌታ እየመራ እርሱ ከጌታው የራቀ : የእርሱን ቃል ሰምተው ሰዎች ሲድኑ እርሱ በኃጢአት ቁስል የተወረሰ ስንት አይሁድ እለ? ቅዱስ አምብሮስ እንዳለው የኖህ መርከብ ሲሠራ ሚስማርና መዶሻ እያቀበለ የሠራ ነገር ግን ከጥፋት ውኃ ያልዳነ ስንት በየቤቱ አለ::

እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል ማለት ቀላል ነው:: እንደተጻፈው መኖር ግን ከባድ ነው:: ከመጽሐፍ ጥቅስ ማውጣት ቀላል ነው የሚጠቀስ ሕይወት መኖር ግን ከባድ ነው:: ወዳጄ ለብዙ ሰብአ ሰገሎች ስለተወለደው ንጉሥ ነግረሃል:: በአንተ ሕይወት ውስጥስ "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?" ወይስ በአንተ ሕይወት ገና አልተወለደም? ወይስ እንደ እንግዶች ማደሪያ ቦታ የለም ብለህ መልሰኸዋል? ኸረ እኔ እንኩዋን የቆሸሸ ሕይወት ነው ያለኝ እሱ በእኔ አያድርም አትበል? እንደ በረት ብትሸት እንደ እንስሳ እየኖርህ ቢሆንም አትፍራ እርሱ አይጠየፍህም? ወደ ልብህ መለስ ብለህ እንዲህ ብለህ ራስህን ጠይቅ "በእኔ ሕይወት ውስጥ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 27 2012 ዓ ም
79 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 19:20:37 ✥✥✥ ቅድስት አርሴማ ✥✥✥

ጥር 6 ልደቷ፣ መስከረም 29 እረፍቷ፣ ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ይታሰባል

✥     “  ድንግል እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው ። መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና ።" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል ። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት ። ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት ። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት ። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት ። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት ። ” ( ገድለ ቅድስት አርሴማ )

✥   “ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት ኣርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው)  /ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን/

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነት፤ ቃል ኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን።
29 views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 19:27:31 #እንኳን_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ!

ታህሳስ -3 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ባዕታ ለእግዝትነ ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው።

ባዕታ ማርያም ማለት ማርያም በ3 አመቷ ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የተሰጠችበት ቀን መታሰቢያ ነው። እመቤታችን 3 ዓመት ሲሆናት ቅድስት ሐና ለባሏ ለቅዱስ ኢያቄም ጌታዬ ልጃችን ለቤተ እግዚአብሔር ነዉ እንጂ እኛን ልታገለግል እንዳልተሳልን እወቅ በተሳልነው መሰረት ለቤተ እግዚያብሔር እንስጣት አለችው፤
ይዘዋት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄዱ ካህኑ ዘካርያስ እመቤታችንን እንደ ፀሐይ ስታበራ አይቷት ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን ልንመግባት ነው ብለው ሲጨነቁ፤
በዚህ ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ህብስት ሰማያዊ ጽዋ ሰማያዊ ይዞ ተገለጾ አንድ ክንፉን ጋርዶ አንድ ክንፉን አጎናጽፎ ከመሬት ሦስት ክንድ ከስንዝር ከመሬት ከፍ አድርጎ ህብስቱን መግቧት ወይኑን አጠጥቶት አርጓል እና ይቺን ቀን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት አመታዊ ክብረ በዓል ነዉ።
የእናታችን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤት፣በረከትና ምልጃዋ አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን!
39 views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 08:52:01
79 views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 08:50:39 እንኳን አደረሰን - አደረሳችሁ

ኅዳር 17 የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ፍልሰተ ዓፅሙ ነው።

ይህ ታላቅና ክቡር፣ የዓለሙ ኹሉ መምህር፣ የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ የኾነው አባት ያረፈው በ407 ዓ.ም. በስደት እያለ ነው፡፡ ወደ ስደት ያጋዘችውም በመንግሥት ይደረጉ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችን እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ፊት አይቶ ሳያዳላ ይገሥጽ ስለ ነበር፥ አውዶክስያ የተባለች የንጉሥ አርቃድዮስ ሚስት ነች፡፡ ፍልሰተ ዓፅሙ የተከናወነው በንግሥቲቱ ልጅ በቴዎዶስዮስ ዘይንእስ ዘመነ መንግሥት በ438 ዓ.ም. ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሕዝቡ ዘንድ እጅግ ይወደድና ይከበር የነበረ አባት ስለ ነበር ገና በስድሳ ዓመቱ ማረፉ ለሕዝቡ እጅግ መራር ኀዘን ነበር፡፡ ይህም ዘወትር በልቡናቸው ሰሌዳ በሕሊናቸው ጓዳ ይኖር ነበር፡፡

በ434 ዓ.ም. የቊስጥንጥንያ ፓትሪያርክ የኾነውና የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ደቀ መዝሙር የነበረው ቅዱስ ኤራቅሊስ አንድ ቀን በሃጊያ ሶፊያ እያስተማረ ሳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን እያመሰገነ ሰበከ፡፡ እንዲህም ይል ጀመር፡- “ዮሐንስ ሆይ! መላ ዘመንህን በኀዘን በመከራ አሳለፍህ፤ ዕረፍትህ ግን የተወደደች የተከበረች ኾነች፡፡ ቅዱሱ ሰውነትህ ያረፈባት መካን ንዕድ ክብርት ናት፡፡ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረትና ቸርነትም የጊዜንና የቦታን አጥር ወሰን ድል አደረግህ፡፡ ፍቅርህ የቦታን ወሰን አለፈ፤ መታወስህ መዘከርህ ይህን አጥርና ድንበር አፈረሰ፡፡...”

ቅዱስ ፓትሪያርኩ ኤራቅሊስ ይህን እየተናገረ ሳለ ቃሉን ያደምጡ የነበሩት ኹሉ ማልቀስ ጀመሩ፤ ስብከቱን እንኳን ሊያስፈጽሙት አልተቻላቸውም፡፡ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በፓትሪያሪኩ እግር ሥር ወድቀው ወደ ንጉሡ ኼዶ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ዓፅም ወደ ቊስጥንጥንያ ተመልሶ ይመጣ ዘንድ እንዲማልደው ተማጸኑት፡፡

ቅዱስ ኤራቅሊስም ወደ ንጉሡ ኼደ፤ የምእመናኑን ተማጽኖም ነገረው፡፡ ንጉሡም ይኹን ይደረግ ብሎ ፈቀደ፡፡ የቅዱሱን ሰውነት የሚያመጡ መልእክተኞችንም አዘዘ፡፡

ኾኖም መልእክተኞቹ የቅዱሱን ሰውነት ማንሣት አቃታቸው፤ እጅግ ከበዳቸው፡፡ ይህንንም ለንጉሡ ነገሩት፡፡ ንጉሡም የጻፈው ትእዛዝ እንደ ነበረ በማስታወስ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተማጽኖ ደብዳቤ ላከ፡፡ ይቅርታን እንዲያደርግለትና ወደ ቊስጥንጥንያ ይመጣ ዘንድ ፈቃዱ እንዲኾን የሚማጸን ደብዳቤ ነበር፡፡ ደብዳቤው በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መካነ መቃብር ላይ ተነበበ። መዝሙር ተዘመረ። ምስጋና ደረሰ። ከዚያም መልእክተኞቹ የቅዱሱን ሰውነት ማንሣት ተቻላቸው፡፡ የዕንቊ ፈርጦች ባሉት የእብነ በረድ ሳጥን ውስጥ አድርገውም በታላቅ ክብር ወደ ቊስጥንጥንያ አፍልሰው አመጡት፡፡

የቅዱሱ ሰውነት መጀመሪያ ያረፈው በሃጊያ ኤሬነ ነበር፡፡ ቅዱስ ኤራቅሊስ ሳጥኑን በከፈተው ጊዜም የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሰውነት ሳይፈርስ ሳይበሰብስ ተመለከተ፡፡ ንጉሡም እጅግ እያነባ ስለ አሳደደችው እናቱም ይቅርታን እየለመነ ወደ ቅዱሱ ሰውነት ቀረበ፡፡ ሕዝቡም ቀኑን ሙሉና ሌሊቱን ኹሉ የቅዱሱ ሰውነት ካለበት ሳጥን ሳይርቁ ውለው አደሩ፡፡

ጠዋት ሲኾንም የቅዱሱ ሰውነት ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ተወሰደ፡፡ በዚህ ጊዜ ሕዝቡ፡- “አባ አባ መንበርህን ተረከብ” እያሉ አሰምተው ተናገሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ከቅዱሱ ሰውነት አጠገብ የነበሩት ቅዱስ ኤራቅሊስና ካህናት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “ሰላም ለኵልክሙ - ሰላም ለእናንተ ይኹን” ሲል ሰሙት፡፡ ብዙ ሕሙማንም ተፈወሱ፡፡
------------
የቅዱሱ በረከትና ረድኤት አይለየን!
------------
67 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 20:31:03 ☞ወር በገባ በ16 ርዕሰ ገዳማውያን የአባ ጳውሊ ወርሀዊ መታሰቢያው ነው፡፡
☞የአባ ጳውሊ አባታቸው የገንዘብ መጠን እንኳን የማያውቁት እጅግ ባለጸጋ
ነበሩ፡፡ አባታቸው ከሞቱ በኃላ ወንድማቸው ጴጥሮስ ንብረታቸውን በትክክል
አላከፍላቸው ሰላል ተጣልተው ወደ ዳኛ ሄዱ፡፡
☞በመንገድ ላይ ሳሉ አንድ ሰው ሞቶ ሊቀብርቱ ሲወስዱት አይተው አባ ጳውሊ
አገኟቸው፡፡ የሞተው ማን እንደሆነም ሲጠይቁ የሞተው ሰው እጅግ ባለጸጋ
እንደነበረ በኃጢአት ውስጥ ሆኖ እንደሞተ ተነገራቸው፡፡
☞ከዚህም በኃላ አባ ጳውሊ የዚህ የኃላፊ ዓለም ገንዘብ ለእኔ ምኔ ነው ?
ብለው ወደ ወንድማቸው ዞረው ወደ ዳኛ መሄዳቸውን ትተው ወደ ቤት
እንዲመለሱ ለመኑት፡፡ የአባታቸውንም የተትረፈረፈ ሀብትና ንብረት
እንደማይፈልጉት ነገሩት፡፡
☞ከወንድማቸው ተደብቀውና ሸሽተው በመውጣት በአንዲት መቃብር ቤት
ገብተው መጸለይ ጀመሩ፡፡ በ4ተኛው ቀናቸው የታዘዘ መልክ መጥቶ ነጥቆ ወስዶ
ከአንድ በረሃ ውስጥ አደረሳቸው፡፡
☞አባ ጳውሊ ወደ አንዲት ኩርፍታ ገብተው ተጋድሎአቸውን ጀመሩ፡፡ በዚያች
ዋሻ ውስጥም የሰው ፊት ሳያዩ በጾም በፀሎት ብቻ ተወስነው 80 ዓመት ኖሩ፡፡
☞ልብሳቸውም ከሰሌን ቅጠል የተሠራ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንደ ነቢዩ ኤልያስ
ቁራን እየላከ ምግባቸውን ይሰጣቸው ነበር፡፡
☞ከዚያ በኃላ ጌታችን የጳውሊን ክብር ይገለጥ ዘንድ መልአኩን ወደ አባ እንጦስ
ዘንድ ላከው፡፡ አባ እንጦስም በበረሃው ውስጥ በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኃላ
በበረሃ መኖር የጀመሩት እሳቸው እንደሆኑ በልባቸው ማሰብ ጀምረው ነበር፡፡
☞መልአኩም ተገልጦላቸው እንጦስ ሆይ ከአንተ የሁለት ቀን ጎዳና ርቆ በበረሃ
ውስጥ የሚኖር ሰው አለ፤ የዓለም ሰዎች ከሚረግጥባቸው የእግሩ ጫማዎች
አንደ አንዲቱ ሊሆኑ የማይገባቸው ስለ እርሱም ጸሎት ዓለም ተጠብቆ የሚኖር
ነው እያለ የአባ ጳውሊን ክብር ነገራቸው፡፡
☞አባ እንጦስም የአባ ጳውሊ በዓት ፈልገው አግኝተው ሄደው በብዙ ምልጃ
በሩን ከፍተውላቸው ተገናኝተው ሁለቱም አብረው ከጸለዩ በኃላ ስለ
ተጋድሎአቸው ስለ አኗኗራቸው ተወያዩ፡፡
☞የታዘዘው ቁራ ሌላ ጊዜ የጳውሊን ምግብ የሚያመጣው ግማሽ እንጀራ ነበረ
ዛሬ ግን ሙሉ እንጀራ ሰላመጣለቸው ሁለቱም ቅዱሳን ደስ ተሰኝተው
እግዚአብሔር አመሰገኑ፡፡
☞አባ እንጦንስም ሥጋ ወደሙን ከወዴት እንደሚቀበሉ አባ ጳውሊን
ሲጠይቋቸዎ በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ መልአክ እያመጣ ሥጋ ወደሙን
እንደሚያቀብላቸው ነገሯቸው፡፡
☞ከዚህም በኃላ አባ አንጦስ ይህን አሰኬማ በምድር ላይ ይበዛ እንደሆነ ወይም
አለመብዛቱ ትነግረኝ ዘንድ እሻለሁ አላቸው፡፡ አባ ጳውሊ ወደ ፊት ሰለሚመጡ
መነኮሳት በመጸለይ ወደ ሰማይ ካዩ በኃላ በመጀመሪያ ፈገግ አሉ፡፡ አባ እንጦስ
ምን አየህ ቢላቸው አባ ጳውሊ ነጫጭ ርግቦች በጠፈር መልተው አንተ
እየመራሃቸው ተከትለውህ ሲሄዱ አየሁ አላቸው፡፡
☞ይህስ ምንድነው ቢላቸው እነዚህማ በዚህ ቆብ የምትወልዳቸው ንጹሐን
ጻድቃን ልጆችህ ናቸው፡፡
☞ሁለተኛም አመልክትልኝ አሏቸው፡፡ ጳውሊም ካመለከቱ በኀላ አዝነውና
ተከፍተው ተመለከቷቸው፡፡ ምነው ቢሏቸው በክንፋቸው ጥቁር ተቀላቅሎባቸው
አየሁ አሉ ምንድን ናቸው ቢሏቸው ጽድቅና ኃጢአት እየቀላቀሉ የሚሠሩ ልጆችህ
ናቸው አላቸው፡፡
☞ሦስተኛም አመልክትልኝ አሏቸው አባ ጳውሊ በድንጋጤ ቃላቸውን ከፍ
አድርገው ጮኹ አባ እንጦስም ምንድነው ቢሏቸው አባ ጳውሊ እንዲህ አሉ ነገር
ግን በመጨረሻ ዘመን የሚነሡት እንደ ቁራ ጠቁረው አየሁዋ ምንድናቸው?
ሹመት ፈላጊዎች ፤ገንዘብ የሚወዱ በፍጻሜ ዘመን የሚነሡ ኅጥአን ልጆችህ
ናቸው አሏቸው፡፡
☞ከዚያም አባ እንጦስም አባ ጳውሊ የተሰወረውን ሁሉ በማወቃቸው አደነቁ፡፡
ዳግመኛ አባ ጳውሊ ቆቡ አባ እንጦስን እንግዲህ ይህን ከራስህ ያደረግኸውን
ለእኔ ስጠኝ ላንተ ሌላ ስሠርተህ አድርግ አላቸው፡፡
☞አባ እንጦስም ይህን እንዳልሰጥህ ከባለቤቱ ተቀብያለሁ፡፡ነገር ግን ሥራውን
ለምጄዋለሁ እና ሌላ ሠርቼ ላምጣልት አላቸው፡፡
☞አባ እንጦስም የ2 ሰአት መንገድ ወደ በዓተቸው ሄደው ቆቡን ሠርተው ይዘው
ሲመጡ አባ ጳዉሊ ዐርፈው ነፍሳቸውን መላእከተ ብርሃን ይዘዋት ሲያርጉ
ተመለከቱ፡፡
☞መላዕክቱም አባ ጳውሊ ዐርፏል ሄደህ ቅበረው አሏቸው፡፡ ይህንስ የያዝኩትን
ቆብ ልተወውን ቢሏቸው አትተው አድርግለት ብለ መለሱላቸው፡፡
]አባ እንጦስም ቢሄዱ አባ ጳውሊ መጽሐፋቸውን ታቅፈው አጽፋቸውን ተጎናጽፈው
ከበዓታቸው ዐርፈው አገኟቸው፡፡
☞እርሳቸውም የአባ ጳውሊን ሥጋ በልብስ ሸፍነው በጸሎታቸው እንዲያስቧቸው
እየተማጸኑ አለቀሱ፡፡ የሥጋቸውን መቃብር ጉዳይ እንዳልተማከሩ አባ እንጦስ
እያሰቡ ሳሉ የታዘዙ አንበሶች መጥተው እጅ ነስተው እግራቸውን ከላሱ በኃላ አባ
እንጦስ የአባ ጳውሊን ሥጋ የሚቀበሩበት ቦታ አሳይተዋቸውአንበሶቹ ቆፎረው
ሰጨርሱ ወጥተው ሰግደውላቸው ሄዱ፡፡
☞አባ እንጦስ በክብር ከቀበሯቸው በኃላ ወደ እስክንድርያ ሄደው ለአባ
አትናቴዎስ የሆነውን ሁሉ ከነገሯቸው በኃላ የሰሌን አጽፋቸውን ሰጧቸው፡፡
☞የከበረ ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ ያችን የአባ ጳውሊን አጽፍ በክብር
አስቀምጠው ሦስት ጊዜ ብቻ ማለትም በልደት፤ በጥምቀትና በትንሣኤ በዓል
ብቻ ይለብሷት ነበር፡፡ በሞትም ሰው ላይ ጥለዋት ሙት አሰነሥተውባታል፡፡
የአባታች የአጳውሊ በዓለ ዕረፍታቸው የካቲት 2 ሲሆን ወር በገባ በ16 ደግሞ
ወርሀዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡
☞(መዝገበ ቅዱሳን መጻሐፍ ገጽ516-517)
☞የአባ ጳውሊ የአባ እንጦስ የጸሎታቸው በረከት በሁላች ላይ ይደር
58 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 04:43:25
42 views01:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ