Get Mystery Box with random crypto!

✥✥✥ ቅድስት አርሴማ ✥✥✥ ጥር 6 ልደቷ፣ መስከረም 29 እረፍቷ፣ ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ይታ | ጥበብ በእርስው

✥✥✥ ቅድስት አርሴማ ✥✥✥

ጥር 6 ልደቷ፣ መስከረም 29 እረፍቷ፣ ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ይታሰባል

✥     “  ድንግል እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው ። መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና ።" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል ። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት ። ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት ። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት ። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት ። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት ። ” ( ገድለ ቅድስት አርሴማ )

✥   “ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት ኣርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው)  /ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን/

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነት፤ ቃል ኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን።