2022-08-29 10:09:59
† ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ †
† ቅዱስ ጊዮርጊስ ታማኝ የክርስቶስ አገልጋይ ነው።†
★ሼር በማድረግ የቅዱሳንን ክብር እንመስክር ★
መ/ር ታሪኩ አበራ
★ Saint George The Martyer★
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክርስቲያን ቤተሰብ የተገኘ ወጣት ነው። በሕይወት ዘመኑ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘ፣ የወጣትነት ዘመኑን እግዚአብሔር እንዲከብርበት በቅድስና የኖረ፣ ከባድ የሰማዕትነትን ተጋድሎ በጽናት የፈጸመ ታማኝ የክርስቶስ ጃንደረባ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍቅርን፣ትህትናን፣ሰብአዊ ርኅራኄንና በጎነትን ወላጅ እናቱ ከቅዱሳት መጻሕፍት በሚገባ ታስተምረው ስለነበር ለሰዎች ሁሉ እጅግ መልካምና ቀና አሳቢ ወጣት ሆኖ አደገ። የነበረውን መልካም ባህሪና በጎ አስተሳሰብ ተመልክተውም በሀገሩ ላይ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂነት አድርገው ለሹመት እንዳበቁት የወጣትነት ዘመን ታሪኩ በሰፊው ይገልጻል።ቅዱስ ጊዮርጊስ ገና በወጣትነቱ የክርስቶስ ፍቅር በልቡ የተሳለበት፣ የመስቀሉ ውለታ በኅሊናው የታተመበት ጠንካራ ክርስቲያን ነበር።በዚህ ዘመን በዘር ፣በብሔር ተከፋፍለን በዓለም ርኩሰት ውስጥ ለወደቅን ወጣቶች ብዙ ቁም ነገር ሕይወቱ ያስተምረናልና ጽሑፋን በጥንቃቄ እናንብ።
#Early life
George was born in Cappadocia, an area which is now in Turkey, in the 3rd century; that his parents were Christians; and that when his father died, George's mother returned to her native Palestine, taking George with her. George became a soldier in the Roman army and rose to the rank of Tribune.
ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥንትዋ ካፓዶቂያ በአሁኗ ቱርክ በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቲያን ቤተሰቦች ተወለደ።አባቱ በሞት ሲያልፍ እናቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዛ ወደ ትውልድ ሀገሯ ወደ ፍልስጠኤም ምድር ተመለሰች።ጊዮርጊስም በዚያው አደገ ኋላም የሮም ወታደር ሆኖ ሳለ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂነት ማዕረግ ተሾመ።
#Persecution of Christians
The Emperor of the day, Diocletian (245-313 AD), began a campaign against Christians at the very beginning of the 4th century. In about 303 AD George is said to have objected to this persecution and resigned his military post in protest.
በወቅቱ የሮም ግዛት ንጉሥ የነበረው ዲዮቅልጢያኖስ ክርስቲያኖችን ለማሳደድ ከፍተኛ ዘመቻ ጀመረ። በ303 ዓ.ም ቅዱስ ጊዮርጊስ ንጉሡ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጽመውን ማሳደድ እንዲያቆም አጥብቆ ይቃወመ ስለነበር የነበረውን ስልጣን በተቃውሞ ለቀቀ።
እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን ንጉሡ ሮም ታስተዳድራቸው በነበሩ ሀገራት ሁሉ ላይ ክርስቲያኖችን ያስጨንቅ ያነበረው ጣዖት አምላኪ በመሆኑ ነው።በግዛቱ ላይ ታላቅ አምባገነናዊ አዋጅ አውጆም ነበር «አብያተ ክርስቲያን ይትሃጸዋ አብያተ ጣዖታት ይትርሃዋ»« አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ አብያታ ጣዖታት ይከፈቱ» የሚል መመሪያ በየሀገሩ አስተላለፈ ይህንን የተቃወሙ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወታደሮች ይዘው በግፍ እያሰቃዩ እንዲገድሏቸው፣ሰውነታቸውን ሰም እየለቀለቁ በአደባባይ እንደ ጧፍ እንዲያቀልጧቸው፣ከአንበሶች ጋር እያታገሉ ሰባብረው እንዲበሏቸው ያደርግ ነበርና ቅዱስ ጊዮርጊስ ይህንን ክፉ የአጋንንት ሥራ አጥብቆ ተቃወመ።
ክርስቲያኖች ልብ በሉ ክርስትና እኛ ዘመን የደረሰው አልጋ በአልጋ ሆኖ አይደለም በብዙ መከራና ስቃይ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዋጋ እየተከፈለበት ነው።፣የክርስቶስን ጌትነትና አዳኝነት ሳይፈሩና ሳያፍሩ በነገሥታትና በአሕዛብ ፊት ወንጌልን በሰበኩ እውነተኛ አማኞች ታላቅ ተጋድሎ ዛሬ በክብር የምንጠራበት ክርስትና የጨለማውን ዘመን በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ሥልጣን ተሻግሮ በብርሃን ሰረገላ የክብሩን ወንጌል ለእኛ አድርሷል።የቀደሙ ክርስቲያኖች ወንጌልን በአፍ ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸው የኖሩ፣ በደሙ የዋጃቸውን ጌታ በደማቸው ያከበሩ ታላቅ የእምነት አርበኞች ናቸው።
#Torture and martyrdom
George tore up the Emperor's order against Christians. This infuriated Diocletian, and George was imprisoned and tortured - but he refused to deny his faith.
ቅዱስ ጊዮርጊስ በክርስቲያኖች ላይ የወጣውን የንጉሡን ትህዛዝ ቀዶ ስለጣለው ይህ ድርጊት ንጉሥ ዲዮቅልጢያኖስ አጅግ አናደደው ጊዮርጊስ እስር ቤት ውስጥ እንዲጣልና በዚያም ከፍተኛ ስቃይ እንዲፈጸምበት አደረገ፤ ሰማዕቱ ግን እምነቱን ፈጽሞ አልካደም።
In the stories George have been tortured in a number of gruesome and hideous ways. He was forced to swallow poison; crushed between two spiked wheels; boiled in a cauldron of molten lead. None of these attempts killed him and his wounds were healed in the night by Christ himself.
በታሪክ እንደተመዘገበው ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አሰቃቂና አስከፊ በሆነ መንገድ በርካታ ስቃዮችን ተቀብሏል።መርዝ እንዲጠጣ አስገድደውታል፣ሁለት የሾለ ብረት ባለው መንኮራኩር መሐል አስገብተው ሰባብረውታል፣በትልቅ ድስት ውስጥ የቀለጠ ብረት አፍልተው ጊዮርጊስን እዛ ውስጥ ጨምረው አሰቃይተውታል።ሰማዕቱን ለመግደል ያልሞከሩት ሙከራ አልነበረም፤ነገር ግን በድንቅ ተአምር ሌሊት ቁስሉን ክርስቶስ ራሱ ይፈውሰው ነበር።
George was told his life would be spared if he would offer sacrifice to the Roman gods. The people assembled to see him do so but instead George prayed to the Christian God.
ሰማዕቱ ለጣዖት መስዋዕት እንዲያቀርብ በንጉሡ በተገደደ ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ለሮም ጣዖታት መስዋዕትን ከማቀረብ ይልቅ ሕይወቴ ቢያልፍ እመርጣለሁ ብሎ ተናገረ። ሕዝቡም በእርሱ ላይ የሚሆነውን ለማየት ተሰብስበው ሲመለከቱ ፤ጊዮርጊስ ግን የክርስቲያኖች አምላክ ወደ ሚሆን ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር።
Immediately, fire came down from heaven, an earthquake shook the ground, and priests, idols, and the temple buildings were destroyed. However, by this time it was God's will that St. George should die for his faith, and he was beheaded without further trouble
እየጸለየም ሳለ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወደቀ፣ታላቅ የምድር መናወጥም ሆነ፣የጣዖት ካህናቱ፣ጣዖታቱና የጣዖታቱ መቅደሶቹ ሁሉ ወደሙ።ሆኖም እግዚአብሔር ሰማዕቱ ከዚህ በላይ እንዲሰቃይ አልፈለገምና ስለ እምነቱ ጽናት በሰማዕትነት ክብር እንዲያልፍ ሆነ።
1.0K views07:09