2022-08-30 10:27:27
ሼር_ፖስት!
ለአማራ ክልል መንግሥት ግልፅና አጭር መልዕክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፤ በአስቸኳይ የታሰሩ ፋኖዎችንና ወታደራዊ አመራሮችን መፍታት አለበት፤ እንዲሁም እፈልጋቸዋለሁ ብሎ የሚያሳድዳቸውን ፋኖዎች ማሳደዱን አቁሞ ወይንም በእርቅ ነገሩን ጨርሶ ይህን መከረኛ ህዝብ ከዳግም እልቂት በሁሉአቀፍ ትብብር ልንታደገው ይገባል። ምክንያቱም ለዚህ ዘመቻ ሁሉም በአንድ ልብ ያልቆመው በፋኖዎች መታሰርና መሳደድ ምክንያት ይመስለኛል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ለዐማራ ህዝብ ዳግም ፍጅትና ውድመት ከህወሓት እኩል ተጠያቂው የክልሉ መንግሥት ነው።
እርስበርሳችን አለን የምንለው ቅሬታ እንደ ዳይኖሰር ግዙፍ ከሆነው ጠላት አንጻር ከመጤፍ ነው። እየመጣ ያለው ማዕበላዊ ጥፋት፣ ሁለተናዊ ውድመት፣ ትውልድ ጨራሽ ፍጅት ነው። ይህን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ፋኖዎችን መፍታት፣ ሌላውንም ጉዳይ በእርቅና በይቅርታ መዝጋት ለነገ የሚባል አይደለም።
እንደምታውቁት ከትናንት በፊት በቆቦና በአካባቢው ስለነበረው እንቅስቃሴ መረጃ ሰጥቼ ነበር። መረጃውን የተለዋወጥኩት ከአንድ ሻለቃ ጋር ነው። እያጠቁና ወደ ቆቦ ከተማ እየገቡ እንደሆነ፣ የደቡብ ቆቦ አካባቢዎችን ማለትም ጎብዬና ሮቢትን እንዳስለቀቁ፣ ጠላት ወደ ዋጃ እየሸሸ እንደሆነ ነበር መረጃውን ያደረሰኝ። ትናንት ማለዳ ላይ ከአንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ጋር ስናወራ ደግሞ ሻለቃው የሰጠኝ መረጃ ክፍተት ነበረበት፤ ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ የመረጃ ክፍተት ያለበት መረጃ አጋርቼ አላውቅም፤ ወደፊትም በመረጃ ሰጪው ካልተሳሳትኩ በቀር እርግጠኛ ያልሆንኩትን መረጃ አልሰጥም። ሆነ ብዬም አላደረግሁትም!
በሚያስገርም ሁኔታ ህወሓት ከትናት ወዲያ አካባቢውን ለቆ የወጣ በመምሰል ዋጃ አካባቢ ስተራቴጂካው ቦታ ይዞ እንደገና በመሰባሰብ፣ ከኋላ ተጨማሪ ኃይል በማምጣት ሰፊ ጥቃት ከፍቶ ነው የዋለው። እንደነገርኳችሁ ከትናት ወዲያ የሰጠሁት መረጃ ዕለታዊ ነበር። ወደኋላ ማፈግፈግ፣ እንደገና መልሶ ማጥቃት፣ በሌላ አቅጣጫ በቆረጣ ማጥቃት....የጦርነት ባህሪ ነው። ለዚህም ነው መረጃዎች ተለዋዋጭ የሚሆኑት።
የትናቱንና የዛሬውን Update ላድርጋችሁ፣ በጥንቃቄ ስከታተል ነበር የዋልኩት፣ ለፋኖዎችም ሎጂስቲክ እንዳይቸግራቸው በሂሳብ ቁጥራቸው ከውጭ ከሚኖሩ ዲያስፖራዎች ጋር ተነጋግረን የተወሰነ ሳንቲም ለማስላክ ሞክሬያለሁ። ወደፊትም እንደከዚህ ቀደሙ ለማገዝና ለማስተባበር ዝግጁ ነኝ። እናም የቀኑ ውሎ እንደነገርኳችሁ ከዋጃ ስትራቴጂካዊ ቦታ ይዘው ተጨማሪ ኃይል በማስገባት ወያኔ ጥቃት መፈፀሙን ቀጥሎበታል። ትናንት በራማ ኪዳነምህረት፣ በጎብዬ፣ በላጎ እና በቃሊም ከፍተኛ ውጊያ ነበር።
ወያኔ እንደከዚህ በፊቱ በቆረጣ ወደ ወልድያ ተጠግቶ ህዝቡን ለማፈናቀልና በከተማዋ መሽገው በሚገኙ የህወሓት ሰርጎገቦች አማካኝነት ከተማዋን በማሸበር ለመቆጣጠር ጎብዬ ላይ እየተወጋ፣ የተወሰነው ኃይል ደግሞ ከዚሁ ከጎብዬ
ተነስቶ በደቡብ ምዕራብ በኩል አድርጎ ወደ ዱርለበስ ነው የሄደው። ምክንያቱም የአላውሃን ወንዝ ተሻግሮ በማመጫ ደጎ ኢየሱስ አድርጎ ወደ ወልዲያ ለመግባትና ዋሻውን ለመቆጣጠር ነው። የዛሬ ዓመትም ወደ ወልዲያ የገባው በዚህ መስመር ነው።
አሁን ጦርነቱ ከወልዲያ በቅርብ ርቀት በሚገኙ አካባቢዎችና ትንንሽ ከተሞች ላይ ሆኗል። ህወሓት በንፁሃን ላላይ በቀሉን ጀምሯል። በዚህ በሰሜን የዐማራ ህዝቡ እየተጨፈጨፈ
በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወደ ሰሜን መጓዙን ጠብቆ ኦነግ ደግሞ በወለጋ በሚኖሩ ዐማሮች ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል።
ዐማራ አንድ ሁን የምለው ወድጄ አይደለም፤ እንደ አንድ ዐማራ ወንድማችሁ የዚህ ህዝብ ህልውና፣ ዕጣ ፈንታ ስለሚያሳስብኝ፥ ስለሚያጨቀኝ ነው። ብርጋዲየር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ እንኳን "አንድ ሁኑ" በሚለው ታሪካዊ ንግግሩ ነው የምናውቀው። አሁንም የራያን ተራራ ተንደርድሮ የሚመጣውን የወያኔ ህዝባዊ ጎርፍ መመከት የሚቻለው በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው። አራቱም ኃያላን ክፍለሀገሮች ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ ይህን ጥቃት መመከት አለበት። መንግሥት የታሰሩ ፋኖዎችን ይፍታ፣ የሚፈለጉ ፋኖዎች ነጻና ይቅርታ ያድርግ፣ ቀጥሎ ለሁሉም ፋኖዎች የክተት ጥሪ ይደረግ፣ ለህዝቡም የክተት አዋጅ ይታወጅ። እኛም እርስበርስ ከመወቃቀስና ከምንካሰስ ቅስቀሳ እናድርግ፤ ዐማራዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ! ቢያንስ ትንሿን ትብብር አድርጉ።
@tadeletibebu @TanaMedia2
@TanaMedia2
@TanaMedia2
436 views07:27