Get Mystery Box with random crypto!

ነሐሴ 24 /2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያውን ዙር 'የ | ጣፋጭ ህይወት/Tafach hiwot

ነሐሴ 24 /2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያውን ዙር "የባለድርሻ አካላት ሚና ምቹ የስራ ፈጠራ እና የኢኖቬሽን ስነምህርዳር ለመገንባት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መድረክ በዘርፉ ውስጥ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በአንድ መድረክ ላይ በማገናኘት በረቂቅ ደረጃ የሚገኘውን የስታርት አፕ እና ኢኖቬሽን ፈንድ ፖሊሲን በተመለከተ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር፣ ከፋይናንስ ተቋማት እና በኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ ካሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የስራ ፈጠራ እና ኢኖቬሽን ስነምህዳር ላይ በጋራ አብሮ በመስራት በፖሊስ ማእቀፍ እና ተያየቀዥ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ዘለላ የተሰኘ የትስስር ፕሮግራም ይፋ የተደረገ ሲሆን ዘለላ ስራ ፈጣሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትን ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና ጠቃሚ መረጃን እና የገበያ ትስስር አማራጮችን የሚያገኙበት የትስስር ፕሮግራም ነው።

እኔ ዘለላ ነኝ በሚል መሪ ቃል ሁሉም ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ለስራ ፈጠራ እና ለኢኖቬሽን እድገት እኔ አንድ ባለድርሻ ነኝ በማለት ፕሮግራሙን እንዲቀላቀሉ እና የማህበሩ ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ በጋራ የአብረን እንስራ ጥሪ ቀርቧል፡፡