Get Mystery Box with random crypto!

የጀማሪ፣ የንግድና ብሔራዊ የኢኖቬሽን ረቂቅ አዋጅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ያበረታታል ተባለ አዲሱ | ጣፋጭ ህይወት/Tafach hiwot

የጀማሪ፣ የንግድና ብሔራዊ የኢኖቬሽን ረቂቅ አዋጅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ያበረታታል ተባለ
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በሥራ ፈጠራና የኢኖቬሽን ሥነ-ምኅዳር ላይ ባተኮረና፣ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ቀርቧል፡፡
ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያልነህ ለማ ናቸው፡፡
በካፒታል ሆቴል በተካሄደው ውይይት ላይ ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡት አቶ አያልነህ እንደተናገሩት አዋጁ ሲፀድቅ ሌሎች ዘርፎችን ቢደግፍም በይበልጥ ግን ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱትን ጀማሪ ድርጅቶችን (ስታርትአፕስ) እንደሚደግፍ ይፋ አድርገዋል፡፡
ጀማሪ ድርጅቶችን የሚመለከት ህጋዊ ማዕቀፍ አለመኖሩና የፋይናንስ አቅርቦት አለመኖር ለረቂቅ አዋጁ መነሻነት እንደግብዓት መወሰዳቸውንም አንስተዋል፡፡
በረቂቅ አዋጁ መሰረት ጀማሪ ድርጅቶች ለስታርትአፕ የንግድ ድርጅቶች የተሰጡ መለያዎችን እስከ አምስት አመታት ድረስ የመጠቀም መብት ሲኖራቸው፣ የኢኖቬቲቭ የንግድ ድርጅቶች ደግሞ በአዋጁ የተሰጡ መለያዎችን እስከ ሶስት አመታት የመጠቀም መብት አላቸው፡፡
ማንኛቸውም ጀማሪ ሥራ ፈጣሪ እስከ 3 አመት የሚደርስ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችልና፤ ለዚህ አገልግሎት የሚውለው ገንዘብም ከብሔራዊ የኢኖቬሽን ፈንድ እንደሚመደብ አቶ አያልነህ ገልፀዋል፡፡
(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)