Get Mystery Box with random crypto!

ጣፋጭ ህይወት/Tafach hiwot

የቴሌግራም ቻናል አርማ tafachhiwotradio — ጣፋጭ ህይወት/Tafach hiwot
የቴሌግራም ቻናል አርማ tafachhiwotradio — ጣፋጭ ህይወት/Tafach hiwot
የሰርጥ አድራሻ: @tafachhiwotradio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 883
የሰርጥ መግለጫ

ለህይወት ማጣፈጫ
መረጃዎች
ቁምነገሮች
ታሪኮችን በኤፍ ኤም አዲስ 97.1 አርብከ10-12

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 15:20:16
ሄላዝ ቢውቲ ከሀመር በተገኘ አፈር የውበት መጠበቂ ምርቱን አስተዋወቀ።

የሄላዝ ቢውቲ ምርቶችን በኢትዮጵያዉያን ቆዳ ላይ ተስማሚነታቸው በስነ-ውበት ባለሙያዎች ተረጋግጦ በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ገበያ የቀረበ መሆኑን የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሄለን የማና ዛሬ አራት ኪሎ በሚገኘው አምባሳደር ሞል የድርጅቱ የመሸጫ ስፍራ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አሳውቀዋል።

ሄላዝ ቢውቲ በኢትዮጵያ ደቡባዊ ክፍል ከሀመር ምድር ላይ በስነ-ውበት ባለሙያዎች በተደረገ ጥናት እና ምርምር የሀመር አፈርን ከሌሎች የተፈጥሮ ግብዓቶች ጋር በማዋሀድ የፊት ውበት መጠበቂያ ባደረጉ የስነ-ውበት ባለሙያዎች ጥናት እና ምርምር ሲደረግበት ቆይቶ በተገኝው ውጤት የፊት ውበትን ለመጠበቅ የሚያስችል ሆኖ በመገኘቱ ከመጪው 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ውስጥ ተመርቶ ለተጠቃሚዎች የሚቀርብ ሲሆን ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ደርጃውን በጠበቀ ሁኔታ በማምረት ሀገራችንን በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተመራጭ የሆነ የውበት መጠበቂያ አምራች ሀገር ለመድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ወይዘሮ ሄለን የማና ገልጸዋል።

በርቺ ፣ ደፋር ፣ ውቢት እና ጀግኒት የተሰኙ ሀገራዊ ስያሜ ያለው የውበት መጠበቂያ ምርቶችን ከዚህ ቀደም ያስተዋወቀው ሄላዝ ቢውቲ በአሁኑ ሰዓት ከ 70 በላይ የተለያዩ የዉበት መጠበቂያ ምርቶችን ለደንበኞቹ እያቀረበ ይገኛል።

ሄላዝ ቢውቲ በአዲስ አበባ መገናኛ ዘፍመሽ ህንጻ ፣ ሜክሲኮ ደብረወርቅ የገቢያ ማዕከል ፣ አራት ኪሎ አምባሳደር ሞል ፣ በገርጂ አልፎዝ ህንጻ እንዲሁም በሐዋሳ ከተማ የመሸጫ ሱቆችን ከፎቶ ለደንበኞቹ ምርቶችን እያቀረበ ይገኛል።
(ጌች ሐበሻ)
372 viewsAnteneh Tesfaye, 12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:59:48
ነሐሴ 24 /2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያውን ዙር "የባለድርሻ አካላት ሚና ምቹ የስራ ፈጠራ እና የኢኖቬሽን ስነምህርዳር ለመገንባት" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መድረክ በዘርፉ ውስጥ ያሉ ባለድርሻ አካላትን በአንድ መድረክ ላይ በማገናኘት በረቂቅ ደረጃ የሚገኘውን የስታርት አፕ እና ኢኖቬሽን ፈንድ ፖሊሲን በተመለከተ ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር፣ ከፋይናንስ ተቋማት እና በኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ ካሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የስራ ፈጠራ እና ኢኖቬሽን ስነምህዳር ላይ በጋራ አብሮ በመስራት በፖሊስ ማእቀፍ እና ተያየቀዥ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ዘለላ የተሰኘ የትስስር ፕሮግራም ይፋ የተደረገ ሲሆን ዘለላ ስራ ፈጣሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትን ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና ጠቃሚ መረጃን እና የገበያ ትስስር አማራጮችን የሚያገኙበት የትስስር ፕሮግራም ነው።

እኔ ዘለላ ነኝ በሚል መሪ ቃል ሁሉም ተሳታፊዎች በኢትዮጵያ ለስራ ፈጠራ እና ለኢኖቬሽን እድገት እኔ አንድ ባለድርሻ ነኝ በማለት ፕሮግራሙን እንዲቀላቀሉ እና የማህበሩ ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ በጋራ የአብረን እንስራ ጥሪ ቀርቧል፡፡
419 viewsAnteneh Tesfaye, 03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 00:08:23
የጀማሪ፣ የንግድና ብሔራዊ የኢኖቬሽን ረቂቅ አዋጅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ያበረታታል ተባለ
አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በሥራ ፈጠራና የኢኖቬሽን ሥነ-ምኅዳር ላይ ባተኮረና፣ ማክሰኞ፣ ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ቀርቧል፡፡
ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሕግ ጉዳዮች ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አያልነህ ለማ ናቸው፡፡
በካፒታል ሆቴል በተካሄደው ውይይት ላይ ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡት አቶ አያልነህ እንደተናገሩት አዋጁ ሲፀድቅ ሌሎች ዘርፎችን ቢደግፍም በይበልጥ ግን ቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረቱትን ጀማሪ ድርጅቶችን (ስታርትአፕስ) እንደሚደግፍ ይፋ አድርገዋል፡፡
ጀማሪ ድርጅቶችን የሚመለከት ህጋዊ ማዕቀፍ አለመኖሩና የፋይናንስ አቅርቦት አለመኖር ለረቂቅ አዋጁ መነሻነት እንደግብዓት መወሰዳቸውንም አንስተዋል፡፡
በረቂቅ አዋጁ መሰረት ጀማሪ ድርጅቶች ለስታርትአፕ የንግድ ድርጅቶች የተሰጡ መለያዎችን እስከ አምስት አመታት ድረስ የመጠቀም መብት ሲኖራቸው፣ የኢኖቬቲቭ የንግድ ድርጅቶች ደግሞ በአዋጁ የተሰጡ መለያዎችን እስከ ሶስት አመታት የመጠቀም መብት አላቸው፡፡
ማንኛቸውም ጀማሪ ሥራ ፈጣሪ እስከ 3 አመት የሚደርስ ስኮላርሺፕ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችልና፤ ለዚህ አገልግሎት የሚውለው ገንዘብም ከብሔራዊ የኢኖቬሽን ፈንድ እንደሚመደብ አቶ አያልነህ ገልፀዋል፡፡
(ኢትዮ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)
43 viewsAnteneh Tesfaye, 21:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:04:41
የዛሬው አዲስ ቀን በራሱ ብዙ እድሎችን ይዞ መቷል በጎውንም መጥፎውንም ለቀኑ የተዘጋጀን መሆን በማስተዋል የተሞላ ቀን ይሁንልን።
389 viewsAnteneh Tesfaye, edited  05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:00:04
በኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር የተዘጋጀው የምክክር መድረክ ማክሰኞ ነሀሴ 24 ከ 9:00 ጀምሮ በካፒታል ሆቴል ይካሄዳል
428 viewsAnteneh Tesfaye, edited  19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:25:02
ሴፍ ላይት ኢኒሼቲቭ በትላንትናው እለት የዓመቱ ትልቅ የሆነውን "የአመራርነት ኮንፍረንስ እና ውድድር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ድምፅ" በሚል መሪ ቃል በይፋ ጀምሯል። በዝግጅቱም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ: የCOFAR ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ላውሊ ኮል፣በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ አምባሳደር ኢንክ ጃን ቤከር እና ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጥሪያችንን አክብረው የተገኙ የክብር እንግዶቻችንን ናቸው።

ታዳሚዎች፣ተወዳዳሪዎች እንዲሁም መላው የሴፍ ላይት ቤተሰቦች ጠቃሚ ሀሳቦችን የገበዩበት ፣ ከእንግዶች ጋር ትውውቅ ያካሄዱበት ፣ በዲፕሎማቲክ ራት ቆይታቸው ገንቢ ልምዶችን የቀሰሙበት ግሩም ምሽት ነበረ፡፡

ሴፍ ላይት ለተጋባዥ እንግዶቹ የከበረ ምስጋናውን እያቀረበ መጪው ዘመን በተለያዩ መሰል እና ትውልድ ገንቢ ስራዎቻችን ላይ አብሮነታችሁ አይለየን እያልን ለመላው ተሳታፊዎችና ተወዳዳሪዎች መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
604 viewsAnteneh Tesfaye, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:27:41 ተመስገን ማለት ስጀምር ያለኝ በረከተ።
ለማመስገን ከዛሬ እና ከአሁን የትሻለ ጊዜ አይመጣምና ስለ ሁሉም ነገር ተመስገን።
690 viewsAnteneh Tesfaye, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:40:18
ባለራዕዮች በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጭላንጭል ብርሀን ላይ የሚያተኩሩት ናቸው።
ጣፋጭ ቀን ለሁላችን።
865 viewsAnteneh Tesfaye, 05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 09:18:42
እንኳን ተወለድሽልን።
መልካም ልደት ቀሪ ዘመንሽ ጥፍጥ ያለ እንዲሆን ምኞታችን ነው።HBD
907 viewsAnteneh Tesfaye, 06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 09:57:20
የጃፓን ወጣቶች ከወላጆቻቸው ያነሰ የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ ሆነዋል፤ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ጃፓን ወጣቶቿ እንዲጠጡ ጠይቃለች

በጃፓን ወጣቱ ትውልድ ከወላጆቹ ያነሰ አልኮል ይጠጣል፤ ይህም ደግሞ መንግስት ማግኘት ያለበትን ገቢ እያስቀረና እየጎዳ መሆኑ ተነግሯል።የጃፓን የብሔራዊ የታክስ ኤጀንሲ ይህንን አካሄድ ለመቀልበስ አዳዲስ አሰራር ጀምሯል።

ቪቫ በተሰኘው አዲስ ዘመቻ መጠጥን የበለጠ ማራኪ ለማድረግ እና ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ እቅድ ተነድፏል። እድሜያቸው ከ20 እስከ 39 ዓመት ያሉ ሰዎች ሾቹ ፣ ውስኪ ፣ ቢራ ወይም ወይን ያሉ መጠጥን ከእኩዮቻቸው ጋር እንዲጠጡ የሚያስችል እቅድ ተነድፏል።

የታክስ ኤጀንሲ በቅርብ ያዋጣው አኃዛዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ በ2020 ጥቅም ላይ ያዋለው አልኮል እ. ኤ.አ በ1995 ከነበረው ያነሳ ነው።ከአልኮል መንግስት የሚያገኘው የግብር ገቢም ባለፉት ዓመታት ቀንሷል። እንደ ጃፓን ታይምስ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. በ1980 ከጠቅላላ ገቢው 5 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2020 ግን ወደ 1.7 በመቶ ቀንሷል።

Via ዳጉ ጆርናል
1.3K viewsAnteneh Tesfaye, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ