Get Mystery Box with random crypto!

ሄላዝ ቢውቲ ከሀመር በተገኘ አፈር የውበት መጠበቂ ምርቱን አስተዋወቀ። የሄላዝ ቢውቲ ምርቶችን በ | ጣፋጭ ህይወት/Tafach hiwot

ሄላዝ ቢውቲ ከሀመር በተገኘ አፈር የውበት መጠበቂ ምርቱን አስተዋወቀ።

የሄላዝ ቢውቲ ምርቶችን በኢትዮጵያዉያን ቆዳ ላይ ተስማሚነታቸው በስነ-ውበት ባለሙያዎች ተረጋግጦ በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ ገበያ የቀረበ መሆኑን የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሄለን የማና ዛሬ አራት ኪሎ በሚገኘው አምባሳደር ሞል የድርጅቱ የመሸጫ ስፍራ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች አሳውቀዋል።

ሄላዝ ቢውቲ በኢትዮጵያ ደቡባዊ ክፍል ከሀመር ምድር ላይ በስነ-ውበት ባለሙያዎች በተደረገ ጥናት እና ምርምር የሀመር አፈርን ከሌሎች የተፈጥሮ ግብዓቶች ጋር በማዋሀድ የፊት ውበት መጠበቂያ ባደረጉ የስነ-ውበት ባለሙያዎች ጥናት እና ምርምር ሲደረግበት ቆይቶ በተገኝው ውጤት የፊት ውበትን ለመጠበቅ የሚያስችል ሆኖ በመገኘቱ ከመጪው 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ውስጥ ተመርቶ ለተጠቃሚዎች የሚቀርብ ሲሆን ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ ዓለም አቀፍ ደርጃውን በጠበቀ ሁኔታ በማምረት ሀገራችንን በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተመራጭ የሆነ የውበት መጠበቂያ አምራች ሀገር ለመድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ወይዘሮ ሄለን የማና ገልጸዋል።

በርቺ ፣ ደፋር ፣ ውቢት እና ጀግኒት የተሰኙ ሀገራዊ ስያሜ ያለው የውበት መጠበቂያ ምርቶችን ከዚህ ቀደም ያስተዋወቀው ሄላዝ ቢውቲ በአሁኑ ሰዓት ከ 70 በላይ የተለያዩ የዉበት መጠበቂያ ምርቶችን ለደንበኞቹ እያቀረበ ይገኛል።

ሄላዝ ቢውቲ በአዲስ አበባ መገናኛ ዘፍመሽ ህንጻ ፣ ሜክሲኮ ደብረወርቅ የገቢያ ማዕከል ፣ አራት ኪሎ አምባሳደር ሞል ፣ በገርጂ አልፎዝ ህንጻ እንዲሁም በሐዋሳ ከተማ የመሸጫ ሱቆችን ከፎቶ ለደንበኞቹ ምርቶችን እያቀረበ ይገኛል።
(ጌች ሐበሻ)