Get Mystery Box with random crypto!

ተረስቶህ ነው? (ሱመያ ሱልጣን) ያ ሁሉ ሃዘኔ፥ እንባና ልመና፣ .............በቃ ቀረ መና | Sumeya sultan

ተረስቶህ ነው?
(ሱመያ ሱልጣን)
ያ ሁሉ ሃዘኔ፥ እንባና ልመና፣
.............በቃ ቀረ መና??
ያሁሉ የኔ ለቅሶ፣
ያ'ዘን ቋቱን ጥሶ፣
የንባዬ ዘለላ ፥ጉንጮቼን አዳርሶ፤
የጠየኩህን ግን፥ ረሳህ ጨርሶ??
እኮ ተማጽኖዬ፥ ከወዴት ደረሰ?
ምድርን ያረጠበው፣ የአይኔ ፍሳሹ፣
የሰማይን ደጃፍ፥ እንዴት አላራሰ?
  ...................ካንተ ያልደረሰ??
እኮ የኔ ጭንቀት፤ የሃዘኔ መብዛት፣
ለውስጥ ቁስለቴ፥ ፈውስን የማጣት፤
ላንተ ምንህም ነው???
ብዬ ያማረርኩት፥ ከ ጸሎቴ በላይ፣
ካንተ የሚቀርበኝ፤ ባጣ አይደለ ምስካይ?
ከሰጠኸኝ በላይ፥ "ጉደለቴ" የተሰማኝ፣
                      እንደው ግን ምን ነካኝ?
እኮ በምን ስሌት፣
የኔ ለኔ ምኞት፣
የኔ ለኔ ማሰብ፣
ካንተ ከአዛኙ የተወዳደረ?
ኧረ እንዴት ደፈረ?
እኮ እንዴት ሲደረግ?
አንተን ለማማረረ፥ ምላሴ ፈቀደ?
ኧረ እንዴት አቀደ?
እና ጌትየዋ......
በእዝነትህ ሚዛን፥ ውለታህ ተቀምጦ፣
የሰጠኸኝ ደፍቷል፥ ከጠየቅኩህ በልጦ።
እሰይ ክበርልኝ!!!!
ልገዛህ ላምልክህ፥ ያ አዚዝ ያ ገፋር፣
ባይገባኝ ነው እንጂ፥ ላንተ ባሪያ መሆን፣
                                   ለኔ በቂ ነበር።
@sumeyasu