Get Mystery Box with random crypto!

          የ እለት ወይዘሮ (ሱመያ ሱልጣን) ይንጠባጠባል፥ የ ዝናብ ውሃ፥ ከጭንቅላቱ፣ ምን | Sumeya sultan

          የ እለት ወይዘሮ (ሱመያ ሱልጣን)
ይንጠባጠባል፥ የ ዝናብ ውሃ፥ ከጭንቅላቱ፣
ምን ሻተ ጀሊል? በሱ ላይ ብቻ የማካፋቱ፤
ይገረማሉ፣ ይጠይቃሉ፣
በዙሪያው ያሉ፥ አስሃቦች ሁሉ።
ነቢ ቢሰሙ፥ ስለ ክስተቱ፣
ለ 1 ሸሂድ፥ የሰማይ በሮች፥ የመከፈቱ፤
መልክት ላኩ፥ ወደ ጀሚላ፣
ምን ሰርቶ እንደሆን፥የ 1ሌት ባሏ፤
ትናገራለች፥በሞቱ ዋዜማ፥ ስላገባችው፣
ያ ወጣት ባሏ፥ የፍቅሩን ጣእም፥ ያልተደለችው፤
ባገባት እለት፥ ሌቱን እሷ ዘንድ፣
             ማልዶም ወደ ኡሁድ፤
ጊዜ እንዳጠረው፥ ጀናባ ሊያወርድ።
ለጌታው መሞት፥ እንደናፈቀው፣
በሙሽሪኮች ሰይፍ፥ ዱንያን ራቀው፤
ታጥቦ መምጣቱን፥ ጀሊል ቢሻለት፥
             መላይካ ልኮ፥ ትጥበቱን ሞላው።
"ታውቆኝ ነበር፥ ህልም አልሚያለው፣
ባሌ እንደሚሞት፥ ቀድሜ አውቃለው።
ግን የኔ ምኞት፥ የሸሂድን ልጅ፥ በሆዴ መያዝ፣
               እንደ ሃንዘላ፥ጀግና ልጅ ማርገዝ።"
ትናገራለች፥ በሰርግ ማግስት፥ኢዳ ቁጭ ብላ፣
የ እለት ወይዘሮ፣የ ሃንዘላ ውድ፣ እመት ጀሚላ።
አወይ እድልሽ፥ደረጃሽ ቀና፣
ልጁ ከሆድሽ፥ባልሽ ከጀና፤
ሸሂድ ሃንዘላ፥አዲስ ሙሽራ፣
ባገባ ማግስት፥ጀነት ተጠራ።
   @sumeyasu