Get Mystery Box with random crypto!

መቼ? (ሱመያ ሱልጣን) አየሁ ልበል ከፈገግታሽ፡ ተስፋ መቁረጥ፣ ሰማሁ ልበል፡ ከሳቅሽ ውስጥ፣ የሲ | Sumeya sultan

መቼ?
(ሱመያ ሱልጣን)
አየሁ ልበል ከፈገግታሽ፡ ተስፋ መቁረጥ፣
ሰማሁ ልበል፡ ከሳቅሽ ውስጥ፣ የሲቃ ምጥ?
ቆይ ቆይ..
ቆይ መቼ ነው ፡በፊትሽ ላይ ፡መስመር ነገር
                                               የተሳለ?
ምን ቀን ነበር፡ ያ ጉልበትሽ ፡ከ አቅሙ የጎደለ?
በየቱ ሌት፡ የራስ ቅልሽ፡ ነጭ ሞላው?
ያንን ዞማ ያንን ጥቁር፡ በምን ፍጥነት አባረረው?
አርጅተሽ ነው?? በቃ ደክሞሽ??
አንቺ እናቴ ፡ለካ ማርጀት፡ ላንቺም አለሽ።
@sumeyasu