Get Mystery Box with random crypto!

የሸራው ላይ ምስሌ (ሱመያ ሱልጣን) ያ የኔ ጎረቤት፣ ያ ምስኪን ሰዓሊ ፣                 | Sumeya sultan

የሸራው ላይ ምስሌ
(ሱመያ ሱልጣን)
ያ የኔ ጎረቤት፣ ያ ምስኪን ሰዓሊ ፣
                     ሸራውን ወጥሮ፣
የበዙ ቀለምን ፣ከስሩ ደርድሮ፤
ይሞነጫጭራል።
ልብን የሚመስል፥ ትንሽዬ አካል፣
                       በጥቁር አቅልሞል።
ወዲያ በዚያ ደግሞ፥ በጫማ ምስል ስር ፣
                                 የወደቀ አእምሮ፣
አቧራ ቀብቶ፡ ከጭቃ ጋር አስሮ ፣
ከእድፍ ከምሮ።
ደግሞ ባንደኛው ጥግ፡ እጆች ይታያሉ፣
የተንጠለጠሉ፤
የሆነ ብልጭልጭ፡ ሊያወርዱ 'ሚመስሉ።
ያ የኔ ጎረቤት፣ ያ ምስኪን ሰዓሊ፣
                            ፈግጎ ይስላል፣
ደግሞ ይኮሳተራል።
ጥያቄዬን እንደታቀፍኩ ፣አስተዋልኩት
ያንን ሙንጭርጭር፣
ለምን ራሴን አየሁት? ቀድምውንስ እዛ ነበር??
ፊቴን ነው እንጂ ያልሳለው፣
ስእሉማ የኔ እኮ ነው።
የ እጆቼን መዳረሻ፡ ያዛን ልቤን አጠቋቆር፣
በብሩሹ ሳለብኝ፣
የአመታት አኗኗሬን፡ በሸራው ላይ ለጠፈብኝ፤
ይፋ አወጣኝ።
ፊቴን ነው እንጂ የቀረው፣
ምስሉማ የኔ እኮ ነው።
@sumeyasu