Get Mystery Box with random crypto!

ወቅቱ ክረምትና ብርድ ነዉ። ብርዱን ለመቀነስም ይሁን ሌሎች የቤት ዉስጥ ስራዎችን ለመከወን ከሰል | St. Urael Internal Medicine Clinic

ወቅቱ ክረምትና ብርድ ነዉ። ብርዱን ለመቀነስም ይሁን ሌሎች የቤት ዉስጥ ስራዎችን ለመከወን ከሰል አቀጣጠሎ መጠቀም በሀገራችን የተለመደ ነዉ። ከሰል፣ ኩበትም ይሁን ሌሎች በነዳጅ የሚሰሩ ምድጃዎች ጭስ አላቸዉ። ለመሆኑ ካርቦን ሞኖኦክሳይድ ምንድነዉ? ለምን አይነት ችግር ያጋልጣል? እንዴትስ መከላከልና ማከም ይቻላል?

በከሰል ጭስ መታፈን (Carbon monoxide poisoning)
የከሰል ጭስ (ካርቦንሞኖኦክሳይድ ) - የማይታይ ገዳይ!!!!

ክፍል አንድ
አንድ ሰዉ በካርቦን ሞኖኦክሳይድ የሚመረዘዉ በደሙ ዉስጥ ያለዉ የካርቦን ሞኖኦክሳይድ መጠን ከፍተኛ ሲሆን ነዉ።

በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ የህመም ምልክቶች
በጣም በብዛት ከሚታዩ የህመም ምልክቶች ዉስጥ

· የራስ ምታት
· መደካከም
· ማዞር/ማጥወልወል
· ማቅለሽለሽና ማስታወክ
· የደረት ህመም
· የትንፋሽ ማጠር
· ብዥ ማለት

በተለይ በተኙበት ወይም መጠጥ ወስደዉ ሰክርዉ ከሆነ በካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ አደገኛ ነዉ።

ለካርቦን ሞኖኦክሳይድ መመረዝ በይበልጥ ተጋላጭ እነማናቸዉ
ሁሉም ሰዉ ለካርቦን ሞኖኦክሳይድ መርዝ ተጋላጭ ነዉ። ሕፃናት ፣ አዛውንቶች ፣ ሥር የሰደደ የልብ በሽታ ፣ የደም ማነስ ወይም የመተንፈስ ችግር ያለባቸው ሰዎች በካርቦን ሞኖኦክሳይድ የመመረዝና የህመም ምልክቶች የማሳየት እድላቸዉ ከፍተኛ ነው።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!