Get Mystery Box with random crypto!

ጤናማ ያልሆነ ውፍረትን(Obesity) ለመከላከል ወይም ለመቀነስ የሚረዱ የአመጋገብ ዘዴዎች አብዛ | St. Urael Internal Medicine Clinic

ጤናማ ያልሆነ ውፍረትን(Obesity) ለመከላከል ወይም ለመቀነስ የሚረዱ የአመጋገብ ዘዴዎች

አብዛኛውን ጊዜ የአንድን ሰው ውፍረት ጤናማነት የሚለካው የሰውነት ክብደቱ ከቁመቱ ጋር በማነፃፀር ነው፡፡ አሁን በተለይ በከተሞቻችን ጤነኛ ያልሆነ የሰውነት ክብደት መጨመር (መወፈር) ያላቸው ሰዎች ቁጥር እየበዛ ነው፡፡ ጤናማ ያልሆነ ውፍረት ለተለያዩ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያጋልጥ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

1. የምንመገባቸው አትክልትና_ፍራፍሬ መጠን ላይ ትኩረት ማድረግ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬዎች ከፍተኛ የሆነ የሚሟሟ አሰር (Soluble dietary fiber) ይዘት አላቸው፡፡

· አንድ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ዘይትሁን፣ ወይም ሌላ ተመሳሳይ መጠን ያለው ፍራፍሬ
· ግማሽ አቮካዶ
· አንድ ትልቅ የሀብሀብ(ብርጭቅ) ወይም የፓይን አፕል ቁርጥ

2. ሰው_ሰራሽ_ስኳር ላይ መጠንቀቅ፡፡ ይህ ስኳር በለስላሳ መጠጦች፣ የታሸጉ ምግቦች፣ ኬኮች፣ እንዲሁም ለሻይ የምንጠቀመውን ስኳር የሚያጠቃልል ሲሆን ጥቅሙም ለሰውነታችን ኃይል ማቅረብ ብቻ (Empty Calorie) ነው፡፡

3. ቅባት ወይም ዘይት ላይ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡ አንድ ጤነኛ ክብደት ላይ ያለ/ች ሰው በቀን ከምግብ ከሚያገኘው ኃይል ዉስጥ ከ30-35% በታች የሚሆነዉን ከቅባት ማግኘት አለበት/ባት፡፡

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!