Get Mystery Box with random crypto!

ጉድፍ (Chickenpox) ጉድፍ በጣም ተላልፊ የሆነ በሽታ ሲሆን ቫሪሴላ ዞስተር በሚባል ቫይረስ | St. Urael Internal Medicine Clinic

ጉድፍ (Chickenpox)

ጉድፍ በጣም ተላልፊ የሆነ በሽታ ሲሆን ቫሪሴላ ዞስተር በሚባል ቫይረስ ይከሰታል። ህመሙ በአብዛኛዉ በልጆች ላይ የሚከሰት ሲሆን አዋቂዎችም ላይም ይከሰታል። ጉድፍ በተለይ በህጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችና በሽታ የመከላከል ስርዓታቸው በተዳከመ ሰዎች ላይ ከባድና ለሕይወት አስጊ ሊሆን ይችላል።

አንድ ሰዉ ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ከተገናኘ በኋላ የህመም ምልክቶቹ ከ10 እስከ 21 ቀናት ውስጥ ሊታይበት ይችላል።

የህመም ምልክቶች

የጉድፍ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ ከ 4 እስከ 7 ቀናት ይቆያል። ነገር ግን ብዙ ሰዎች በ2 ሳምንታት ውስጥ ያገግማሉ።
· ትኩሳት
· መደካከም

· ሽፍታ፦ ሰዉነት ላይ ሽፍታ ይከሰታል ፤ ከዚያም ሽፍታዉ የሚያሳክክ፣ ዉሃ የቋጠረ እየሆነ ይሄዳል። ሽፍታው በመጀመሪያ በደረት ፣ ጀርባ እና ፊት ላይ ይታያል ፣ ከዚያም በአፍ ዉስጥ፣ አይንና ብልት አካባቢን ጨምሮ በመላው ሰውነት ላይ ይሰራጫል።

ተጋላጭ እነማናቸዉ?

· ከዚህ በፊት ለቫይረሱ ተጋላጭ ያልነበሩ
· ለጉድፍ ቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ
· በትምህርት ቤት ወይም የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት የሚሰሩ ሰዎች

እንዴት ይሰራጫል

ጉድፍ በቀላሉ ከሰዉ ወደ ሰዉ የሚዛመት ነዉ
· ዉሃ ከቋጠረዉ ሽፍታ የሚወጡ ቅንጣቶችን ወደ ሳንባችን በመተንፈስ
· ቅርብ ለቅርብ በሆነ ቀጥተኛ ኒክኪ መኖር( ከሽፍታዉና ከፈነዱ ሽፍታ ፈሳሾች ጋር ንከኪ መኖር)

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!