Get Mystery Box with random crypto!

መልካም እንቅልፍ ለመተኛት የሚመከሩ ምክሮች ጭንቀትና | St. Urael Internal Medicine Clinic

መልካም እንቅልፍ ለመተኛት የሚመከሩ ምክሮች

ጭንቀትና ህመምን ጨምሮ ጥሩ እንቅልፍ እንዳይተኙ የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉ። መልካም እንቅልፍ አንዳይኖርዎ የሚያደርጉ ወይም ጣልቃ የሚገቡትን ነገሮች መቆጣጠር ላይችሉ ይችላሉ። እነዚህን ልምዶች ለማዳበር የሚከተሉትን ቀለል ያሉ መንገዶችን ይተግብሩ

1. እንቅልፍ የሚተኙበትን መደበኛ ሰዓት አለማሳለፍ፦ በቀን ከስምንት ስዓታት ያልበለጠ የእንቅልፍ ሰዓታትት ሊኖርዎ ይገባል።

2. ለሚመገቡት ነገሮች (ለሚበሉም ሆነ ለሚጠጡ) ነገሮች አትኩርዎት ያድርጉ፦ ከመጠን በላይ ጠግበዉ አሊያም ተርበዉ አይተኙ።ምቾት ማጣት እንቅልፍ ሊከለክልዎ ስለሚችል በተለይም ከመተኛትዎ በፊት ባሉት የተወሰኑ ሰዓታት ውስጥ ከባድ ምግቦችን ወይም ከመጠን በላይ መመገብን ያስወግዱ።

3. የመኝታ ቦታዎችን ምቹ ማድረግ፦ የመኝታ ክፍልዎ ቀዝቀዝ፣ ፀጥና ደብዘዝ ያለ እንዲሆን ማድረግ። ቦግ ያለ ብርሃን ያለዉ ክፍል እንቅልፍ እንዳይተኙ ያደርጋል።

4. የቀን እንቅልፍ ወይም ናፕ መቀነስ ወይም መገደብ፦ ቀን ለረጅም ሰዓታት መተኛት ሌሊት እንቅልፍ እንዳይተኙ ሊያደርግዎ ይችላል።

5. በየቀኑ በሚያከናዉኑት የተለመዱ ክንዉንዎ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጨመር፦ በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ መልካም እንቅልፍ እንዲኖርዎ ሊያግዝዎ ይችላል።

6. ጭንቀትን መቀነስ፦ ከመተኛዎ በፊት ጭንቀትዎን መቀነስ ወይም ለመፍታት መሞከር ያስፈልጋል። በአዕምሮዎ ዉስጥ የሚመላለሱ ነገሮችን ይፃፉና ለሚቀጥለዉ ቀን ( ለነገ) ያስተላልፉት ።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!