Get Mystery Box with random crypto!

አለርጂን መከላከል ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ የተነሳ ቅዝቃዜና መጥፎ ጠረን ወይም ሽታ ሊኖር ይችላል። | St. Urael Internal Medicine Clinic

አለርጂን መከላከል

ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ የተነሳ ቅዝቃዜና መጥፎ ጠረን ወይም ሽታ ሊኖር ይችላል። ይህም አለርጂ ላላቸዉ ሰዎች ፈተና ሊሆንባቸዉ ይችላል። ስለሆነም መሰል ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ምን ማድረግ እንችላለን?

የቤት ዉስጥ ብናኞችና ነፍሳቶች

የአለርጂን መነሻ ከሚባሉት ትላልቅ መንስኤዎች መካከል አንዱ ከቤት ከሚነሱ አቧራ ውስጥ የሚገኙት ጥቃቅን ነፍሳትና የአቧራ ብናኝ ናቸው።

በቤትዎ ውስጥ ያሉትን ብናኞችና ጥቃቅን ነፍሳቶችን ቁጥር ለመገደብ

· የቤትዎ ወለል ከስጋጃ ምንጣፍ ይልቅ ከእንጨት ወይም ከታይልስ እንዲሆን ማድረግ

የቤት ዉስጥ የሚቆዩ እንስሳት

አለርጂን የሚያመጣው የቤት እንስሳ ፀጉር አይደለም። ይልቁንም የሞተ ቆዳቸው ቡናኝ፣ ምራቃቸዉና ከደረቀ ሽንታቸው የሚነሱ ቅንጣቶች ናቸው።

· የቤት እንስሳትን በተቻለ መጠን ከቤት ውጭ ማቆየት ወይም በአንድ የተወሰነ የቤቱ አካባቢ መገደብ፣ በተለይም ምንጣፍ በሌለበት ቦታ ላይ አንዲሆኑ ይመከራል።
የሻጋታ ቡናኞች

ከግድግዳም ይሁን ከሌሎች እርጥበት ካላቸዉ ነገሮች የሚነሱ የሻጋታ ጥቃቅን ቅንጣቶች በአንዳንድ ሰዎች ላይ የአለርጂ ምላሽ ሊያስከትሉ ይችላሉ። ሰለሆነም

· የቤትዎ ግድግዳዎችና ሌሎች ነገሮች እርጥበት የሌላቸዉ ደርቅና አየር በቀላሉ የሚዘዋወርባቸዉ እንዲሆን ማድረግ

· ማንኛውንም የቤት ክፍል ውስጥ በእቃ የተተከሉ እፅዋትን ከቤትዎ ዉጪ ማድረግ

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!