Get Mystery Box with random crypto!

ድንገተኛ የጉበት መድከም ክፍል ሁለት ድንገተኛ የጉበት መድከም ሊያመጣዉ የሚችለዉ የጎንዮሽ ጉዳት | St. Urael Internal Medicine Clinic

ድንገተኛ የጉበት መድከም

ክፍል ሁለት
ድንገተኛ የጉበት መድከም ሊያመጣዉ የሚችለዉ የጎንዮሽ ጉዳት

የአንጎል አብጠ( በአንጎል ዉስጥ ፈሳሽ መጨመር)፦ በጣም ብዙ ፈሳሽ በአእምሮዎ ውስጥ ግፊት እንዲጨምር ያደርጋል። ይህም ወደ ግራ መጋባት፣ ከፍተኛ የአእምሮ ግራ መጋባት ፣መቀባዠርና እንደሚጥል ህመም ማንቀጥቀጥ ያስከትላል።

ኢንፌክሽን፦ ድንገተኛ የጉባት መድከም የጋጠማቸዉ ሰዎች ለመተንፈሻ፣ ለደምና ለሽንት መተላለፊያ ስርዓት ኢንፈክሽኖች ይበልጥ ተጋላጭ ነዉ።

የኩላሊት መድከም፦ በተለይ አሴታሚኖፌን ከመጠን በላይ የወሰዱ ሰዎች ከጉበት መድከም በኃላ የኩላሊት መድከም ያጋጥማቸዋል።

የጉበት መድከምን መከላከል
ጉበትዎን በመንከባከብ ከድንገተኛ የጉበት መጎዳት እራስዎን ይጠብቁ።
በመድሃኒት ሲወስዱ የአወሳሰድ መመሪያዎችን ይከተሉ፦ አሲታሚኖፌንም ይሁን ሌሎች መድሃኒቶችን ሲወስዱ ምን ያህል ለመዉሰድ እንደሚመከር ያረጋግጡ። ከሚመከረዉ በላይ አይውሰዱ።

የሚወሰዱት መድሃኒቶች ካሉ የህክምና ባለሙያዎ ጋ ሲቀርቡ ይናገሩ

አልኮሆል ከመጠጣት ይቆጠቡ፦ አልኮሆል ከመጠጣት ይቆጠቡ። አልኮሆል የሚጠጡ ከሆን ግን ምጥነዉ ምሆን አለበት።

ክትባት ይዉሰዱ፦ ስር የሰደደ የጉበት ችግር ካልዎ ወይም ለግዩብተ ኢንፌክሽን ተጋላጭ ከሆኑ የጉበት ቫይረስ ክትበቶችን ይወሰዱ።

የሌሎች ሰዎችን የሰዉነት ፈሳሽና ደም ከመንካት ይቆጠቡ፦ ድንገተኛ በመርፌ መወጋት አሊያም በአግባቡ የልፀዱ የሰዉነት ፈሳሾችን መንካት የጉበት ቫይረሶች እንዲተላለፉ ወይም እንዲሰራጩ ያደርጋል።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!