Get Mystery Box with random crypto!

ክብደት መቀነስ ክብደትን ለመቀነስ የሚሞክር ማንኛውም ሰው ክብደትን በፍጥነት ለመቀነስ መፈለግ ተ | St. Urael Internal Medicine Clinic

ክብደት መቀነስ

ክብደትን ለመቀነስ የሚሞክር ማንኛውም ሰው ክብደትን በፍጥነት ለመቀነስ መፈለግ ተፈጥሯዊ ነው። ነገር ግን ክብደታቸውን ቀስ በቀስና ያለማቋረጥ የሚቀንሱ ሰዎች (በሳምንት ከግማሽ እስከ 1 ኪሎ ግራም የሚቀንሱ) የሰዉነት ክብደታቸዉን በመጠበቅ ረገድ የበለጠ ስኬታማ ናቸው። ጤናማ ክብደት መቀነስ ስለ "አመጋገብ" ወይም ስለ ሆነ " ፕሮግራም" ጉዳይ ብቻ ማዉራት አይደለም። ጤናማ የአመጋገብ ዘይቤዎችንና መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚያካትት ቀጣይነት ያለዉ የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ነው እንጂ።

የሰዉነት ክብደትዎን ቀንሰዉ አንዴ ጤናማ የሰዉነት ክብደት ላይ ከደረሱ በኋላ ክብደትን ለረጅም ጊዜ እንደቀነሰ እንዲቆይ ለማገዝ ጤናማ አመጋገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ ያስፈልጋል።

አንድ ሰዉ መጠነኛ የሰዉነት ክብደት ቢቀንስ እንኳን ትልቅ ጥቅሞችን ሊያመጣ ይችላል።

ይህም አንድ ሰዉ ከጠቅላላው የሰውነት ክብደቱ ከ5 እስከ 10 በመቶ የሚሆነውን መጠነኛ ክብደት ቢቀነስ እንኳን እንደ የደም ግፊት፣ የደም የስብ መጠን (ኮሌስትሮል)ና የደም ስኳር መጠን መሻሻል ያሉ የጤና ጥቅሞችን ሊያስገኝለት ይችላል።

ለምሳሌ የአንድ ሰዉ የሰዉነት ክብደቱ 90 ኪሎግራም ቢሆንና ከዚህ ላይ 10 በመቶዉን ቢቀንስ ክብደቱ 81 ይደርሳል።ይሁንና ይህ ክብደቱ አሁንም "ከመጠን በላይ ክብደት" ወይም "ወፍራም" ክልል ውስጥ ሊሆን ቢችልም ይህ መጠነኛ ክብደት መቀነስ ከውፍረት ጋር በተያያዙ ሥር ለሰደዱ በሽታዎች የመጋለጥ እድሉን ይቀንስለታል ማለት ነዉ።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!