2022-08-31 20:59:50
"ሀዋን ማን ገደላት"
( አብዲ ኢኸላስ)
ክፍል አስር(10)
እትዬ መርየም እና ኻሊድ የሀዋ ስልክ ላይ የተመለከቱትን ነገር በፍጹም አላመኑም።ከተመለከቱት ረጅም ሰአታት ቢቆጠርም እኩለ ለሊት ቢያልፍም እንኳን እንቅልፍ አልወስድ ብሏቸዋል።ግና የሆነውን ሳያጣሩ በመደዋወል ብቻ አይታመንም እና ምንም ማወቅ አልቻሉም።ለሀዋ የተደወለላት የመጨረሻ ቁጥር የሙና በመሆኑ ግራ ተጋብተዋል። ለሀዋ የተደወለላት ቁጥር ነው እንጂ የመጨረሻ እሷ ግን ከሙና ቀጥሎ ለሰሚር ደውላለት ነበር ግና ምንም የተመዘገበ ደቂቃ የለም ምክንያቱም የዛን ቀን የሰሚር ስልክ ዝግ ነበርና። እትዬ መርየም ይበልጥ ውስጣቸውን እየበላቸው እና እያስጨነቃቸው ያለው ነገር ሙና ልጃቸው ነች።ነገ ፖሊሱ ሲመጣ ለፖሊስ ግርማ ምን ብለው ነው ጥርጣሬያቸውን ሚነግሩት።የሀዋ ስልክ ቤት እንዳለ ከነገሩት ተቀብሎ ምን አልባትም ይሄ የግድያ ወንጀል ስለሆነ እስከ ቴሌ ድረስ ሄዶ የተነጋገሯቸውን ንግግሮች ለማጣራት ቢሞክር ምን አልባት ሙና በዚ ጉዳይ ወንጀለኛ ብትሆን ግራ ገባቸው።
እሳቸው የእንጀራ እናት በመሆናቸው በፍጹም በመሀል የመከፋፈል የመለያየት ስሜት የላቸውም።ነገር ግን ለአንደኛዋ ልጃቸው ብለው ሌላኛዋ ልጃቸውን ማስቀጣት አይፈልጉም ግን ኻሊድ ይህን ተመልክቷል ።ኻሊድን ዝም ማስባል በጣም ከባድ ነው እናቱ የት እንዳለች አያውቅም አባቱ ሆስፒታል ተኝቷል በዚህ ጭንቀት ውስጥ ሆኖ ከፖሊስ ያየኸውንም ሆነ የሰማኸውን ደብቅ ቢባል ነገሮች ከባድ ይሆናሉ ።ብቻ በራሳችን መንገድ እስከምናጣራ ድረስ ለሰሚር አጠገቡ መሆን ያለባት ልክ እንደዛሬው እየሄደች የምታድር አንዲት ሴት ሙና ብቻ ነችና እሷንም ካሰሩብን ችግር ይፈጠራል ብለውት ለጥቂት ቀናት ዝም እንዲል አሳመኑት።በዚህ ተስማምተው የነገን ነገ ያውቃል አላህ ያለውን እንቀበላለን ሲሉ ወደ መኝታቸው ተጓዙ።
ጠዋት ነግቶ ወፎች መንጫጫት ከጀመሩ ሰአታት ተቆጥረዋል።ሙና ከተኛችበት ነቃች እሷ ሳትሆን ሰሚር አስታማሚ ይመስል ከፍተኛ እንቅልፍ ውስጥ ተኝታ ለሊት እንኳን ምን ተፈጠረ ብትባል በማታውቅበት ሁኔታ ጭልጥ ብላ ከገባችበት እንቅልፍ ስትነቃ ሆስፒታል ውስጥ እራሷን ስታገኘው ማታ የነበረውን ሁሉ አስታወሰች ትንሽ ግር ብሏት ነበር። ካለችበት ክፍል ውጪ ብዙ ድምፆች አሉ።
የተለያዩ ዶክተሮች አስታማሚዎች ታማሚዎች እና ነርሶች እንዲሁም ሌሎች ሁሉ የሚጮሁት ጩኸት በደንብ ይሰማል።ሆስፒታሉ ብዙ ሰው የሚጨናነቅበት ነውና ገበያ መስሏል።ይህ ሁሉ ጩኸት ባለበት ለሽ ብላ መተኛቷ ለራሷም ገረማት።ወደ ሰሚር ተጠጋች "እንዴት አደርክ?" አለችው መልስ አይሰጣትም ይህን ታውቃለች ነገር ግን መልስ እንደተሰጠው ሰው "አልሃምዱሊላህ እኔም ደና አድሬያለሁ ካንተ ጋ" አለችው ።
ሀፍረት ቢሷ ሙና ከሱ ጋር እንዳደረ ሰው ለራሷ አሳመነች በጀግንነትም ፈገግ አለች።ግን እኳ ሙና የከፋ ቅናት ቢኖርሳትም ሰውኛ ማንነቷ አይለቃትም።ሰው እንደመሆኗ መጠን የዚህን ያህል ጨካኝ ናት ብሎ ማሰብ እጅጉን ከባድ ነው።ምን አልባት በ ሀዋ ላይ እጆን ሰንዝራ ይሁን እንዴ የሚለው ግራ ያጋባል።ምክንያቱም ብትፈልግስ በምን አቅሟ በምን ሁኔታዋ እንደዛ በተጠና መልኩ ከበድ ያለ ወንጀል ለመፈፀም እንዴት ትችላለች። ሀዋ ከቤት ከራቀች ቡሃላ ሙና ለአንድም ቅፅበት የተለየ ስልክ አላወራችም ወደ ደጅም አልወጣችም ምን አድርጋስ ይሁን !!እንዴትስ አልፈራችም?! በፖሊስ ግርማ መምጣትም እንዴት አልተደናበረችም?!ግራ ያጋባል።
ግን አንድ ነገር አቅዳለች ሙና ቤተሰቡን አሳምና ለሰሚር ቅርብ መሆን ሰሚር ሰሚር ከህመሙ ነቅቶ ሲመለስ የመጀመሪያ የሚመለከተው ፊት የሷን እንዲሆን በእጅጉ ተመኝታለች።እሷን እንዳያት አጠገቡ ሆና ልትንከባከበው ባለ ውለታው ሆና ወደራሷ ልታመጣው ልቡን ልታሻፍት ክፉ እቅድ አቅዳለታለች። ነገር ግን ለዚ እቅዷ እንዲስማሙ ቤተሰቦቿ ማመን አለባቸው አለበለዚያ ሊከሽፍ ይችላል።ከጥቂት ቆይታ ቡሀላ ሱመያ ኻሊድ እና እትዬ መርየም ተከታትለው ገቡ። ከነሱ በፊት አንድ ነርስ እና የሰሚርን ጉዳይ የያዘው ዶክተር ሰሚርን መርፌ ሰተውት ሁኔታውን ተመልክተው ወተዋል።እትዬ መርየም ሙናን ሲመለከቷት የፍርሀት ስሜት ውርር አደረጋቸው። ምን አልባት ያ ክፉ ቅናቷ የዚህን ያህል ክፉ ስራ እንድትሰራ ሸይጣናዊ ግፊት ገፍቷት ይሁን እንዴ ሲሉ ተጨነቁ።ከዛም አልፈው ምን አልባት ሰሚር ላይ ጉዳት አድርሳ መጥፎ ነገር ፈፅማ ይሁን እንዴ በማለት ወደ ሰሚር ጠጋ ብለው ትንፋሹን አስተዋሉ ደህና መሆኑን ሲመለከቱ በእርጋታ ተንፍሰው ከወንበሩ ላይ ተቀመጡ።
ሙና የእትዬ መርየምን ወደ ውጪ መውጣት አብዝታ ትጠብቃለች ምክንያቱም ከሳቸው በፊት ኻሊድን እና ሱመያን በእኩይ አላማዋ ልታሳምናቸው የምትላቸውን አዘጋጅታ ቆርጣ እየጠበቀች ነው።ሙና እኮ መጥፎ ምኞት ተመኘች እንጂ ሰሚር በምንም ተአምር ምድር ብትገለበጥ ድጋሜ ቢፈጠር ታሪክ እንዳልነበር ቢሆን ተአምር ቢወርድ ሀዋን ጠልቶ የሙና ሊሆን አይችልም።እንኳን ሀዋን ጠልቶ ሀዋ በሌለችበት ስለ እሷ እያሰበ ይኖራል ሂወቱን አቶ ይሞትላታል እንጂ ሌላ ገላ ማቀፍ ሌላ ሴት ማፍቀር ሌላ ትዳር ማሰብ የማይሆን ነገር ነው። ሰሚር "ሀዋ ለኔ የተሰራችው ልክ በልኬ እንደሚያምርብኝ ሱፍ ውበቴ ናት ይላል"። "የልጆቼ እናት እኔ ከሷ ውጪ ምንም አልፈልግም አንዳች አይጨመርልኝ ምንምም አይቀነስብኝ ሌላ ደስታ ሌላ ምኞት የለኝም" ይላል።ሰሚር ሀዋን የሚወዳት ከልቡ አብዝቶ ከልቡ ነው ለሷ ሲል የትኛውን አይነት የህይወት መሰዋእትነት ለመክፈል ሁሌም ዝግጁ ነው። ዝምብ እንኳን ላይዋ ላይ እንድታርፍ አይፈልግም የሷን ደስታ የሷን ሳቅ የሷን ፍቅር አብዝቶ ይናፍቃል።ሰሚር ከሀዋ ውጪ ሴት አያውቅም ከሷ ውጪ ማንንም ምንንም እንደ ምንም አይቆጥርም።ሌላ ሴት ፍቅርን ምትችል ሌላ ሴት ትዳር የምታውቅ ሌላ ሴት የምትወደደው መስሎ አይሰማውም።ለሱ ሀዋ ልክ እንደ አደም ለሱ ሀዋው ነች ሌላ ሴት አያውቅም ሌላ ፍጥረት ለሱ የሌለች ያህል የብቸኝነት ይወዳታል ያፈቅራታል ይንከባከባታል።
በርግጥ ሙና ይሄንን ሳታውቅ ቀርታ ነው ወይ ለማለት በእጅጉ ያዳግታል ምክንያቱም የሀዋ እና የሰሚር ፍቅር ግልፅ ነው አይደለም እቤት አይደለም ቤተሰብ መስሪያ ቤት እንኳን አምልጧቸው ይወጣል።ከአናት እንዳለ ኮፍያ ከየትኛውም ርቀት የሚታየው ፍቅራቸው ለማንም ያስቀናል። ከአይን ያውጣቸው የሚባለውን ውዴታቸውን የማያውቅ እነሱን የማያውቅ እንጂ አንድ ቀን የሚያውቃቸው ሰው የነሱን ፍቅር ሳይመለከት ሳይቀና ፈገግ ሳይልና ሳይገረም አያልፍም።ትናንሽ ህፃናቶች ተዋደው እየተራራጡ እንጂ የልጆች እናት እና አባት እንኳን አይመስሉም። ይሄን ፍቅር ለመቀማት ጓግታ ለራሷ ለማድረግ ሙና በሞኝነቷ ተመኝታለች ።ሁሉም በጭንቀት እና በስስት ሰሚርን ይመለከታሉ። ዶክተር በር አንኳክቶ ገባ ከመካከላቸው አንድን ሰው ማናገር እንደሚፈልግ ነግሯቸው እትዬ መርየምን ይዞ ወደራሱ ክፍል ሄደ።ይሄኔ ሙና ምትፈልገው ተሳካላት ሱመያ እና ኻሊድን በብቸኝነት በግላጭ አገኘቻቸው።እነሱን ልታወራ ሀሳቧን ልታሳምን ጉሮሮዋን በመጠራረግ ላይ ሳለች ድንገት ሰሚር ነቃ ሁሉም ደነገጡ ከተቀመጡበት ቆም አሉና ወደ ዶክተር መሯሯጥ ያዙ ዶክተር ዶክተር ሰሚር ነቅቷል።
ክፍል አስራ አንድ (11) ይቀጥላል .....
#ልዩ_ምስጋና ZU23 እና ለሰኪና ራህመቶ
@Strong_iman
1.3K views𝐒̧𝐔𝐃€𝐘𝐒, 17:59