Get Mystery Box with random crypto!

'ለዘንድሮ ስኬታችን የፅ/ቤት ሰራተኞች የከፈላችሁት መስዋዕትነት የሚዘነጋ አይደለም' አቶ አብነት | ST.GEORGE FC™🇪🇹

"ለዘንድሮ ስኬታችን የፅ/ቤት ሰራተኞች የከፈላችሁት መስዋዕትነት የሚዘነጋ አይደለም"
አቶ አብነት ገብረመስቀል
====//////=====/////====
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የፅ/ቤት ሰራተኞች የ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን መጠናቀቅን ምክኒያት በማድረግ በክለቡ መዝናኛ ማእከል የሠራተኞች  የጋራ የደስታ ፕሮግራም አሠናድተዋል።
በፕሮግራሙም ሰራተኞች የዚህ አመት የጉዞ ትዝታዎቻቸውንና ያልተነገሩ ገጠመኞችን በማውሳት ከአመራሩና አጠቃላይ የጊዮርጊስ ቤተሰቦች ጋር በጋራ የተሰራው ስራ ለዋንጫ ድል እንዳበቃን ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ መሀል የክለባችን ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረመስቀል በስልክ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን " የፅ/ ቤት ሰራተኞች የሚያጋጥሙ ችግሮችን በትዕግሥት እና በፅናት በማለፍ ለምታከናውኑት ተግባር ክብር አለኝ ፤ ብዙውን ነገር ችላችሁና ታግሳችሁ ለውጤታማነታችን የሠራችሁት ጊዮርጊሳዊ ማንነት ስላላችሁ ነው፤ አሁንም ከፊት ያለው ይበረታልና በትዕግሥት ታላቁን ጊዮርጊስ አይታችሁ በአብሮነትና በህብረት እንድትቀጥሉ አደራ እላለሁ፤ በራሳችሁ ወጪ ደስታችሁን በጋራ ማክበራችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል " ብለዋል።
በምሽቱም ፕሮግራም ሰራተኛው በአርአያነታቸው የጎሉ ግለሰቦችን አመስግኗል።


@St_Georgefc
@St_Georgefc

የቅዱስ ጊዮርጊሳውያን ድምፅ
THE VOICE OF ST.GEORGE FANS