Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ 'በቅርቡ' በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚንስ | Skyline media

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ "በቅርቡ" በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የብሄራዊ ደኅንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።

ዶር ዐቢይና ፕ/ር ኢሳያስ ካይሮ ላይ በኹለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቀሱት አቶ ሬድዋን፣ ፕ/ር ኢሳያስ በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝት ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ እንደተስማሙ ገልጸዋል።

ፕ/ር ኢሳያስ ጉብኝቱን ካካሄዱ፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕወሃት መካከል የግጭት ማቆም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ ጉብኝቱ የመጀመሪያቸው ይኾናል።