Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ሹመት የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ለተለያዮ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጠ፡፡ ››››››››› | Skyline media

ዜና ሹመት
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ለተለያዮ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጠ፡፡
›››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››››
ጉባኤው ዛሬ ሃምሌ 05 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት አቅራቢነት ለቀረቡ ለተለያዮ የስራ ሃላፊዎች ሹመት ሰጥቷል፡፡በዚህም መሰረት
1ኛ) አቶ አንቢኮ ጃርሳን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ኮርት ማናጀር
2ኛ) አቶ ኡቦንግ ኡጁሉ ጊሎን የጠቅላይ ፍርድ ቤት የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
3ኛ) አቶ አጃማ ጋዲሳን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አድርጎ ሾሟል፡፡
በሌላ በኩል በአንድ ረዳት ዳኛ ላይ በቀረበ የዲሲፕሊን ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የአንድ ወር ደመወዝ እንዲቀጡ ወስኗል፡፡
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤትም አዲስ ለተሾሙት የስራ ሃላፊዎች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ይመኛል::