Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ግንቦት 4/2015 ዓ.ም (ኢሳት): ሀላፊው በቢሯቸው ውስጥ ተገደሉ የቂርቆስ ክፈለ ከተማ | Skyline media

ሰበር
ግንቦት 4/2015 ዓ.ም (ኢሳት): ሀላፊው በቢሯቸው ውስጥ ተገደሉ

የቂርቆስ ክፈለ ከተማ ወረዳ ሰምንት ዋና ስራ አሰፈጻሚ በቢሯቸው ውስጥ መገደላቸው ተገለፀ፡፡

ዋና ስራ አሰፈጻሚ አቶ አለባቸው አሞኘን በመግደል የተጠረጠረው የአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ባልደረባ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል ሲል ኢሳት ዘግቧል፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለባቸው አሞኘ በጥይት ተመተው ዘውዲቱ ሆስፒታል መግባታቸውና ህይወታቸውንም ማትረፍ አለመቻሉን መረጃ አመልክቷል።

ተጠርጣሪው ሀላፊውን በሽጉጥ ከገደለ በኋላ ከአንድ ግብረአበሩ ጋር እንደተያዙም ታውቋል።