Get Mystery Box with random crypto!

አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች ********************* | Skyline media

አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
*********************

አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ባደረባት ሕመም በ83 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ድምፃዊቷ ወደ ሙዚቃው ዓለም በ1949 ዓ.ም እንደገባች እና ረጅም የሙዚቃ ጊዜዋን በፖሊስ ሠራዊት ኦርኬስትራ እንዳሳለፈች የሕይወት ታሪኳ ያስረዳል።

ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ጥቂት ስመጥር ሴት ድምፃዊያን መካከል አንዷ እና ተወዳጇ የሆነችው ሂሩት በቀለ፣ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎቿም በሕዝብ ዘንድ እጅግ የተወደዱ እና ለበርካታ ሴት ድምፃዊያንም መነሻ የሆኑ ናቸው።