Get Mystery Box with random crypto!

በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሪው ዲከንስ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል | Skyline media

በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሪው ዲከንስ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ ቀጥታ በረራ መጀመሩን ምክንያት በማድረግ በረራው የሁለቱን ከተሞች እና የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የሚያጠናክር ፤ ወደ ከተማችን የሚመጡ ቱሪስቶችን ቁጥር ከፍ ማድረግ የሚያስችል ስለሆነ በትብብር ለመስራት ተስማምተናል።

አዲስአበባ ዓለም አቀፍ ከተሞችን እና ተቋማትን መሳብ የጀመረችና በማበብ ላይ ያለች ታላቅ የዲፕሎማሲና የቢዝነስ ማዕከል እንደመሆኗ የተሻሉ ልምዶችን መካፈል የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር በማድረግ ለከተማችን እድገት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ