Get Mystery Box with random crypto!

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ባካሄደው የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ | Skyline media

ምርጫ ቦርድ በደቡብ ክልል በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ባካሄደው የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ የጸደቁ ውጤቶችን ይፋ በማድረግ ላይ ነው። ቦርዱ ትናንት የአማሮ ልዩ ወረዳ ውጤትን የጸደቀ ያሳወቀ ሲሆን፣ የልዩ ወረዳው ድምጽ ሰጪዎች በከፍተኛ ድምጽ "የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል" የሚሰኘውን አዲስ ክልል ለማቋቋም እንደወሰኑ ገልጧል። ቅዳሜ'ለት ይፋ በተደረገው የጸደቀ ውጤት፣ የደራሼ፣ አሌ፣ ባስኬቶና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች እና የኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በከፍተኛ ድምጽ አዲሱን ክልል ለማዋቀር መወሰናቸውን ቦርዱ አስታውቋል።